August 22, 2017 19:08

 

አዲስ አበባ የኛ ናት ስለሚሉ አዲስ አበባን ጨምሬ በኦሮሚያ በሚሏት ዉስጥ ወደ 20 ዞኖች አሉ። እንግዲህ ቄሮ የሚባሉት ከነገ ረእቡ ጀመሮ እስከ እሁድ ድረ የሥራ/ንግድ/ትምህርት ማቆም አድማ ጠርተዋል። በኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ በስፋት፣ በኢሳት ደግሞ በተወሰነ ደረጃ እየተዘገበ ነው። በኦ.ሜ/ኔትዎርክ ድህረ ገጽችና ፌስ ቡክ ገጾች (በነ ጃዋር) ማስታወቂያዎችና ማስጠንቀቂያዎችም እየተሰሙ ነው። አድማዉን ተላልፎ በሚገኝ ዜጋ ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንድሚችል ነው እየገለጹ ያሉት።
“ከነገ ሮቡዕ ጀምሮ እስከ እሁድ በኦሮሚያ ውስጥ ቤት የመዋል እና ስራ የማቆም አድማ እንደሚካሄድ ቀደም ብለን ማስታወቃችን ይታወሳል። ይህም ከማክሰኞ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተፈጻሚነቱን ለማረጋገጥ በቄሮው በኩል ቁጥጥር ይካሄዳል። ለዚህ አድማ ቀደም ብሎ የአንድ ሳምንት የዝግጅት ጊዜ መሰጠቱም የሚታወስ ነው። በተጠቀሱት ቀናት አምስቱም የፊንፊኔ ከተማ መግቢያ መንገዶች ዝግ ይሆናሉ። ስለሆነም ከሌሎች ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችም ወደ ከተማው መግባት ስለማይችሉ በተጠቀሱት ጊዚያት ለማድረግ ያቀዱትን ጉዞዎች ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፉ በድጋሚ እናሳስባለን” ይላል አንድ ማስታወቂያ።
“ከደቡብ ክልል አቅጣጫ ወደ መሃል ሀገር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች በሙል ዛሬ ከእኩለ ሌሊት ጀምር ምንም አይነት ትሸከርካሪ በሻሸመኔ መንገድ ማለፍ አይፈቀድለት። እገዳውን ጥሶ ለተንቀሳቀሰ ለሚደርስበት ችግር ሀላፊነነቱን የራሱ መሆኑን ከዚሁ ማስታወቅ እንወዳለን” ይላል ሌላ ደግሞ።
ማንኛውም ህዝባዊ እንቅስቃሴ የሕዝብ መሰረት ከሌለው ውጤት አያመጣም። ቄሮዎች (የቁቤ ተትዉልድ ወጣቶች) በሶሻል ሜዲያው መረብ እንዳላቸው ይታወቃል። በመሆኑን ከነገ ጀመሮ የተጠራው ሰልፍ በተለይም በአንዳንድ ቦታዎች ለአንድ ለሁለት ቀንም ቢሆን ዜና መፍጠሩ አይቀርም። በተለይም ከ20 ዞኖች በአሥሩ ( ምእራብ ሸዋ፣ አራቱ የወለጋ ዞኖች፣ ምእራብ አርሲ፣ ሁለቱ የሃረርጌ ዞኖች ባሌና የተወሰነው የደቡብ ምእርብ ሸዋ ዞን) እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ ይችላልሉ ብዬ እጠብቃለሁ። በተለይም አምቦ በዶር መራራ መታሰር የተቆጣ ህዝብ እንደመሆኑ ለአገዛዙ ራስ ምታት የሆነ ሕዝብ ነው። በአማራው ክልል እንዳለችዋ ጎንደር ማለት ነው። ለዚህም ነው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአምቦ አገዛዙ ከዛሬ ጀመሮ መብራት ሙሉ ለሙሉ እንዲጠፋ ያደረገው።
በሌሎቺ ዞኖች (በአዲስ አበባ፣ በአድማ ልዩ፣ በጂማ ልዩ፣ በቡራዩ፣ በአርሲ ዞን (አሰላ)፣ በኢሊባቡር፣ በጉጁ፣ በቦረና፣ በሰሜን እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች ብዙም የሚፈጠር ነገር ይኖራል ብዬ አላስብም። በነዚህ ቦታዎች የሚኖረው ህዝብ አገዛዙን ደግፎ ሳይሆን፣ እነ ጃዋርን የማይቀበል ማህበረሰብ በመሆኑ ነው። በብዛት ሕብረ ብሄራዊ የሆነ፣ ያለዉን ደግሞ የኦሮሞ ማህበረሰብ በነዚህ ቦታዎች ከማንም ባልተናነሰ በኢትዮጵያ አንድነትና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ በመሆኑ፣ የነ ጃውዋርና የኦሮሞ አክራሪዎችን ፖለቲካ ይጸየፋል።
በኦሮሚያ ካሉ ትላልቅ ከተሞች (አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂማ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ ነቀምቴ፣ አሰላ፣ ቡራዩ፣ ሰበታ፣ወሊሶ ናቸው ከአንድ እስክ አሥር ያሉት) በነቀምቴ፣ ምን አልባትም በሻሸመኔ በተወሰኑ ቀበሌዎችና በወሊሶ የአድማው ጥሪ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል። ከዚያ ዉጭ በአዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጂማ በመሳሰሉት በሌሎቹ ግን እንቅስቃሴ ይኖራል ብዬ አልጠብቅም።
ወደ አዲስ አበባ የሚወስዱ መንገዶችን በተመለከተ ቀደም ሲል እንዳልኩት በአምቦ መስመር ካለው መንገድ ዉጭ ሌሎች ወደ አዲስ አበባ የሚወስዱ መንገዶች ይዘጋሉ ብዬ አላስብም።
ይሄን ስጽፍ ግን ሁለት ነገሮችን ግልጽ ላደርግ፡

– ይሄ ግምት ነው። የገመትኩትም ሙሉ ለሙሉ ፉርሽ ሊሆን ይችላል።
– ዜጎች ለጥቂቶች ኤጎ ማርኪያ በሚል ውጤት በማያመጣ ነገር ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ ነው። እነ ጃዋር እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ከተወሰኑ አካባቢዎችና ከተወሰኑ ወገኖች በቀር በመላው የኦሮሚያ ህዝብ የማይደገፍ መሆኑን ለማሳየት ነው። እስቲ አስቡት ኦሮሚያ ፣ ኦሮሚያ እያሉ የኦሮሚያ ትላልቅ ከተሞችን አሳምነው ማንቀሳቀስ ካልቻሉ ምን ዋጋ አላቸው ?
ከዚህ በታችያለው ካርታ ኦሮሚያን የሚያሳይ ነው። በቀይ በተከበቡት አካባቢዎች እንቅስቃሴ ይኖራል ብዬ የማልጠብቅባቸው አካባቢዎች ናቸው። እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ የሚኖርባቸውና በኢኮኖሚ በጣም ክፍ ያሉ አካባቢዎች። ከአንድ እስከ አሥር የጠቅስኳቸው ከተሞች ከአንዱ በስተቀር ሁሉም በዚህ አካብቢ ነው ያሉት።፡ለሚቀጥለው አምስት ቅናት የሚሆነውን እናይና፤ ካርታዉን አሻሽለን፣ ትክክል መሆናችንን እንና አለመሆናችንን ለማሳየት እንሞክራለን።

ኦሮሚያ ዉስጥ ያሉ ዞኖች አሉ።

1. አዲስ አበባ (አዲስ አበባ)
2. አዳማ ልዩ(አዳማ)
3. ጂማ ልዩ (ጂማ)
4. ቡራዩ ሊዩ (ቡራዩ)
5. ምስራቅ ሸዋ ዞን ( አዳማ)
6. ሰሜን ሽዋ ዞን (ፍቼ)
7. ደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን (ወሊሶ)
8. አርሲ ዞን (አሰላ)
9. ምእራብ አርሲ (ሻሸመኔ)
10. ጂማ ዞን (ጂማ)
11. ኢሊባቡር ዞን (መቱ)
12. ሆሩ ጉድሩ ዞን
13. ምስራቅ ወለጋ ዞን (ነቀምቴ)
14. ምእራብ ወለጋ ዞን (ጊምቢ)
15. ቀለም ወለጋ ዞን (ደምቢ ደሎ)
16. ምእራብ ሃረርጌ( ጭሮ/አሰበ ተፈሪ)
17. ምስራቅ ሃረርጌ
18. ባሌ (ሮቢ)