8/23/2017

ፋሽስት (አረመኔው) ጣልያን በ1933.. መልካም አጋጣሚ ተፈጥሮልን የወቅቱ አውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች እርስ በእርስ በመጋጨታቸው የእንግሊዝን ድጋፍ አስችሮን በአርበኞቻችን ከባድ መሥዋዕትነትና በእንግሊዝ ድጋፍ ድል ተመትቶ ተባሮ እንዲወጣ ሲደረግ ከሀገራችን የዘረፈውን ሀብት ከየብሱ ኢትዮጵያ ውስጥና ከባሕር ከመርከቦቹ ቀይ ባሕር ላይ እንግሊዝ በምርኮ ትወስድብኛለች!” ብሎ ስለፈራ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በኮንክሪት ግንብ (በጥፍር ግንብ, ጥፍር ሲነበብ ፍ ትጠብቃለች) እየቀበረ የቀበረበትን ካርታ (ንድፈ ምድር) እየያዘ ነበር ጥሎ የወጣው፡፡ ጣሊያን 1928.. ሀገራችንን እንደወረረ በቅርብ በግላጭ ያገኛቸውን ዘርፎ ወደ ሀገሩ ከመላኩ በስተቀር በቆይታ በተለያየ መንገድ የሰበሰበውን ግን ሳይወስደው ነበር ችግር የገጠመው፡፡

እነዚህ ጣሊያን የቀበራቸው የወርቅ የብርና የዕንቁ ሀብቶች የተመዘበሩት ከአብያተክርስቲያናት በንዋየ ቅድሳትና እንደ ዘውድ በመሳሰሉ ቅርሶች መልክ ተሠርተው የተቀመጡ በዕንቁና በሌሎች የከበሩ ማእድናት የተንቆጠቆጡ ከወርቅና ከንጹህ ብር የተሠሩ ከሽዎች ዓመታት በፊት ጀምሮ በየ አብያተክርስቲያናት በየአብያተመንግሥታት በየግምጃቤቱ በየዋሻው ተከማችተው የቆዩ ንዋየ ቅድሳት፣ ቅርሶችና የሀገር ሀብት ናቸው፡፡ ከፊሎቹን እየጨፈለቀ ከፊሎቹን በቁመናቸው ነው አከማችቶ የቀበራቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ጠገራ ብርም አለበት፡፡ ከከርሰ ምድር ያወጣውም አለበት፡፡

ይሄንን የሀገር ሀብት ጣሊያን በአምስት ዓመታቱ የወረራ ጊዜ ከያሉበት ፈልፍሎ እያወጣ በማከማቸት ላይ እያለ ነው ሳያስበው ድንገት በተፈጠረው መልካም አጋጣሚ የአርበኞችና የእንግሊዝ ጦር ጥምረት ለመፍጠር አስቻላቸውና የደረሰበት ጥቃት የወረራ ጊዜውን እንዲያከትምለት ስላደረገው በጥድፊያ በየቦታው እየቀበረው የወጣው፡፡ ጣሊያን ተሸናፊ ስለነበረ ንብረቱን ሁሉ እንግሊዝ ምርኮ አድርጋ እንደምትወስድበት ስላወቀ ነው ይሄንን ሀብት ተማርኮ ከመወሰድ ለማዳን በሌላ ጊዜ መጥቸ እወስደዋለሁ!” ብሎ በማሰብ ነበር ቀብሮ ባዶ እጁን እያጨበጨበ በተሸናፊነት የወጣው፡፡

እነዚህ የወርቅ የብርና የተለያዩ ውድ ሀብቶችና ማርትሬዛ ብሮች የተቀበሩባቸው ግንቦች ብዙዎቹ በየተቀበሩበት አካባቢ ባሉ ነዋሪዎች የሚታወቁ ናቸው፡፡ ራቅ ራቅና ሰወር ሰወር ካሉ ስፍራዎች ከተቀበረው በስተቀር ብዙዎቹ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ወያኔ አሁን በቅርቡ ጣሪያውን እንዳለ አንሥቶ ሲያበቃ በከፈተው ጣሪያ በኩል እያወጣ እውስጡ የነበረውን የሀገር ሀብት አውጥቶ እየጫነ የወሰደውን ጎንደር ከተማ ወጣ ብሎ ወደ ወለቃ መስመር የሚገኘውን የግንብ አዳራሽ ደርግም ያውቀውና በወታደርም ሲያስጠብቀው የነበረ ቦታ ነው፡፡ እጅግ በጣም የሚገርመኝ ነገር ያ ደንቆሮ፣ ከብት ደርግ ይሄ የሚያስጠብቀው ግንብ ቤት ሀብት እንዳለበት እያወቀ ያውም ተቸግሮ እያለ አውጥቸ ለሀገር ልጠቀምበት ሳይል መቅረቱ ነው፡፡ እጅግ እኮ በጣም የሚገርም የሚደንቅ ነገር እኮ ነው፡፡ አሁን ደርግን የሚያህል ደንቆሮና ከብት በዚህች ዓለም ላይ ይገኛል?

ከግልና ከቡድን ጥቅም ይልቅ ለሀገርና ለሕዝቧ ጥቅም ማሰብ፣ ለሀገርና ለሕዝቧ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት እርም የሆነበት፣ ከራሱ በስተቀር ምንም ነገር የማይታየው፣ የ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” የአህያነቱ አስተሳሰብ ባፍ ጢሙ ሊደፋው እያንደፋደፈው ያለው ወያኔ ህልውናው እያከተመ መሆኑን ተረዳ መሰለኝ ሳልወስደው ልቀር!” በሚል ቁጭት ሕዝባዊ ዐመፅ ከተነሣበት ጊዜ ወዲህ እነኝህን ጣሊያን ወርቅ ዕንቁና ጠገራ ብር እንዲሁም ሌሎች ውድ የሀገር ሀብቶች የቀበረባቸውን ሥፍራዎች እያነፈነፈ እየደረመሰ እያወጣ ወደ ትግራይ በማጋዝ የተጣደፈ ዘመቻ ላይ ይገኛል፡፡

ወያኔ ይሄንን ንብረት ሲወስድ ምን ያህል ንብረት እንዳገኘና ለትግራይ ሳይሆን ለኢትዮጵያ፣ ለሕወሃት ሳይሆን ለኢትዮጵያ መንግሥት (የኢትዮጵያ መንግሥት የለም እንጅ) ገቢ ማድረጉን እስከአሁን በየትኛውም መንገድ ቢሆን ለሕዝብ አላስታወቀም፡፡ ይሄም ማለት ለግሉ ዘርፎ ወስዶታል ማለት ነው፡፡ ወያኔ ማለት እንኳንና ጥሬ ወርቅ ዕንቁና ብር ተራ የቧንቧ (የቀሰም) ብረት እንኳ ሳይቀር (መተከል) እየነቀለ ወደትግራይ የኛነ ተራ የዘራፊ የወንበዴ ቡድን እንደመሆኑ ይሄንን አስጎምጅ የሀገር ሀብት ይምራል ብሎ ማሰብ እጅግ ሲበዛ ቂልነት ነው የሚሆነው፡፡ ወያኔ ከተለያዩ ቦታዎች ይሄንን ሀብት ሲያወጣ ነጮችም አብረው የታዩ በመሆናቸው በክፍፍሉ ከጣሊያን ጋር ተስማምቶ ዘረፋውን እንደተያያዙት ይገመታል፡፡

እኔ እራሴ እንኳ የሰማሁትና አንዳንዱንም ደርምሶ ከወሰደው በኋላ ያየሁት ከስድስት ስፍራዎች ላይ የነበረውን የተቀበረ አስጎምጅ የሀገር ሀብት ከተለያዩ አካባቢዎች በተሳካ ሁኔታ አውጥቶ እየጫነ ወደ ትግራይ መውሰዱን አውቃለሁ፡፡ እንደኔ ሁሉ ወያኔ በዚህ የተጣደፈ የዝርፊያ ዘመቻው በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ የተቀበሩ ሀብቶችን ደርምሶ መውሰዱን የምታውቁ እንደምትኖሩ እገምታለሁ፡፡ ኧረ እንደምን አድርገን እናስቀረው ወገን? ውልቃችንን እኮ አስቀሩን!

ከዓመታት በፊት ጣሊያን እነኝህን ሀብቶች አውጥታ ከወያኔ ጋር ተካፍላ ለመውሰድ ድርድር ማድረጓ ተወርቶ ነበር፡፡ ያኔ በክፍፍሉ ድርሻ ላይ ባለመስማማታቸው ሊቀር እንደቻለ ነበር ጭምጭምታው የተሰማው፡፡ እዚህ ላይ ግን አንድ እንድትይዙልኝ የምፈልገው ጉዳይ ቢኖር ጣሊያን በቅኝ አገዛዟ ወቅት በሊቢያውያን ላይ ላደረሰችው ግፍ ለሊቢያ በርካታ ቢሊዮን (ብልፍ) ዶላር ካሳ መክፈሏ ይታወቃል፡፡ ፋሽስት ጣሊያን በሊቢያውያን የፈጸመው ግፍ በእኛ በኢትዮጵያውያን ላይ ከፈጸመው ግፍና እልቂት ኢምንቱን አያክልም፡፡ በዓለም ላይ ጥቅም ላይ እንዳይውል በተከለከለ የመርዝ ጭስ ያለበት ፈንጅ ነው በእኛ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠቀም እናት አባቶቻችንን ወይም በዚህ አደገኛ ጅምላ ጨራሽ መሣሪያ ሰለባ የሆኑትን በርካታ ወገኖቻችንን በአሰቃቂ ሁኔታ የፈጀበት፡፡ ሌሎች ሌሎች ዘግናኝ ግፎችንና ውድመትም የፈጸመብን፡፡

አሁን ጥያቄው ጣሊያን የቀበረው የሀገራችን ሀብት ለሊቢያ ካሳ ከከፈለው አንጻር በእኛ ላይ የፈጸመብን ግፍ የከፋ እንደመሆኑ ሊከፍለን የሚገባው ካሳ ለሊቢያ ከከፈለው ካሳ በእጅጉ የላቀ መሆኑ ግምት ውስጥ ገብቶ ቀብሮት የሔደው ሀብታችን ሊከፍለን ከሚችለው ወይም ከሚገባው ምን ያህል የላቀ ወይም የገዘፈ ሀብት ቢሆን ነው ሀብቱ የእኛው የራሳችን ቢሆንም ካሳ ይሁናቸው!” ብሎ ለመተው የተቸገረው? ብላቹህ አስባቹህታል? ይህ አስጎምጅ አማላይ የሀገር ሀብት ለሀገር ጥቅም ቢውል ኖሮ ድኅነትን ሊያሰናብትልን የሚችል እንደሆነስ አስባቹህታል? እውነቴን ነው የምላቹህ አንገብጋቢ ቁጭትና ከባድ ሐዘን ውስጥ ላይ ነኝ፡፡

ይህ በየቦታው ተቀብሮ ያለ ሀብት እግዚአብሔር ባወቀ ለዚህች ሀገር ለክፉ ቀን ያስቀመጠላት ሀብት ነው!” የሚል እምነት ነበረኝ እንጅ እንዲህ የወንበዴው የወያኔ ሲሳይ ሆኖ በወያኔ እየተዘረፈ ወደ ትግራይ ይጋዛል የሚል ግምት ፈጽሞ አልነበረኝም፡፡

እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ በሰዎች ፊት ራቁቴን የቆምኩ ያህል ነው አሸማቃቂ ስሜት የሚሰማኝ፡፡ እናት አባቶቻችን ሀገራቸውን ከራሳቸው በላይ በማየት ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው መሥዋዕት ሆነው ያወረሱንን የሀገር ሀብት መጠቀም ሳንችል ለወንበዴ አስበላነው፣ አወረስነው፣ ጠላት እንዲበለጽግበት፣ እንዲደልብበት፣ እንዲናጥጥበት አደረግነው፡፡ አሁን እኛ ሰዎች ነን? እንዲያው ምን ጉዶች ነን? እውነት እኛን የኢትዮጵያ ምድር አፈራች? እውነት እኛ የእነዚያ ቆራጥ ጀግና አናብስት እናት አባቶቻችን ልጆች ነን? “የእሳት ልጅ አመድ!” አሉ የአመድም ዋጋ ሲበዛብን ነው፡፡ እጅግ በጣም ያሳዝናል!

ይህ ዝርፊያ ከሕዝብ ዕይታ የተሰወረ እንዳልሆነ ሁሉ ተቃዋሚ ነን ከሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች (የእምነተ አሥተዳደር ቡድኖች) እና ከተለያዩ ሕዝባዊ ማኅበራት ዕይታም የተሠወረ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይሄንን ጉዳይ የሰሙና የሚያውቁ ከሆነ ታዲያ ይህ ሀገርን ከስር የሚነቅል፣ ቀፎዋን የሚያስቀር ዝርፊያና ውንብድና እንዴት ነው ሊያሳስባቸው ያልቻለውና ሊያወግዙ፣ የተዘረፈው አንዲት ሳትቀር ተቆጥራ ተመልሶ ወደሀገሪቱ ካዝና እንዲገባ፣ የቀረው እንዳይነካ ሊንቀሳቀሱ ያልቻሉት? ይህ ከፍተኛ የሀገር ሀብት ዝርፊያና ውንብድና ምን ማለት እንደሆነ አልገባቸውም ማለት ነው ወይስ ንቃት ቁርጠኝነት የሌላቸው ሆነው?

ይህ ሀብት በፋሽስት ጣልያን ከአብያተክርስቲያናትም የተዘረፈ እንደመሆኑ በዚህ ወቅት እግዚአብሔርን ሳይሆን ወያኔን እያገለገሉ ካሉ ምንደኛ ተኩላ ጭንጋፍ አባት ተብየዎች ውጭ ያሉ በቤተክርስቲያኗ የተለያዩ መዋቅሮች በኃላፊነት የተቀመጡ ጳጳሳትና ካህናት አባቶችም ሀብቱ በወያኔ እየተዘረፈ መወሰዱን ሊያወግዙ ይገባ ነበር፡፡ ነገር ግን ዛሬ እንደምታዩት ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ!” ማቴ. 1028 እያሉ የሚሰብኩ የሚያስተምሩ አባቶች ቤተክርስቲያን በዓይናቸው ስር ስንት ጉድና ግፍ እየተፈጸመባት ከእግዚአብሔር ይልቅ ወያኔን አለቅጥ በመፍራት ሁሉም ክርስቶስ የጣለባቸውን አደራ በልተው እረኝነታቸውን የማይወጡ፣ ዓይናቸው እያየ መንጋውን በተኩላት የሚያስበሉ የሚያስነጥቁ፣ ቤተክርስቲያንን የሚያስደፍሩ የሚያዘርፉ አደራ በላዎች ብቻ ሆነዋል፡፡

ዘወትር በጭንቅላቴ የሚያቃጭልብኝ አንድ ጥያቄ ቢኖር እነኝህ ጳጳሳትና ካህናት አባቶች በእግዚአብሔር የማያምኑ አስመሳዮች ቢሆኑ ነው እንጅ በእግዚአብሔር የሚያምኑ ቢሆኑና በዚህ ጥፋታቸው ነገ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው የሚጠየቁ፣ የሚከሰሱ፣ የሚወቀሱ፣ ቅጣታቸውንም የሚያገኙ መሆኑን የሚያውቁና የሚያምኑ ቢሆኑ ኖሮማ እንዴት ከእግዚአብሔር ይልቅ ወያኔን ፈርተው በቤተክርስቲያን ላይ እንዲህ ዓይነት ክህደት ይፈጽሙ፣ እምነት ያጎሉ፣ ከቤተክርስቲያን ጥቅም ተፃራሪ በሆነ ሁኔታ ከወያኔ ጋር ይተባበሩ ነበር???

አዳሜ አባቶች አሉን ትላለህ! ድንቄም አለ ያገሬ ሰው! አባቶች ያሉህ ይመስልሀል? “መንኮሰ ሞተ ነው! የሞተ ሰው ማንንም እንደማይፈራ ከእግዚአብሔር በቀር ማንንም አንፈራም! ለእግዚአብሔር ያደርን ነን! ሕይዎታችን የእግዚአብሔር ናት!” ብለው የበቃን ነን ይገባናል!” ብለው ተቀብተው እረኝነት ከተሾሙ በኋላ እያንዳንዱ ለሥጋው ፈርቶ ወያኔ በቤተክርስቲያን ላይ የሚያደርገውን ግፍና መከራ ዓይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ዝም ጭጭ ብሎ በእግዚአብሔር የተጣለበትን እምነትና አደራ እየበላ፣ እያጎደለ፣ እየጣለ በእግዚአብሔር አምናለሁ! ከማንም በላይ እግዚአብሔርን እፈራለሁ!” ቢለኝ ይሄንን ሰው እንዴት ነው ልሰማውና ላምነው የምችለው? እኔን መሸንገል ቢችል እግዚአብሔርን መሸንገል የሚችል ይመስለዋል ወይ?

በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ማለትም በነፍሴና በሥጋዬ ላይ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ አንዳችም ነገር ማንም ሊያደርስብኝ አይችልም! የጣለብኝን አደራ ለመወጣት ስጥር አላውያንንና መናፍቃንን አስቆጥቶ ለመከራ ሊዳርጉኝ ቢጋበዙና በስሙ መከራ ተቀብየ ለክብር እንድበቃ እሱ ያንን መከራ እንድቀበል ወዶና ፈቅዶ ካመጣብኝ ግን ያመጣውን መከራ በስሙ መቀበል ይኖርብኛል!” ብሎ የሚያምን ሰው ወያኔን ከእግዚአብሔር በላይ ሊፈራና እግዚአብሔርን ወይም ቤተክርስቲያንን ሊጎዳ ሊከዳ ወያኔን ሊጠቅም የሚችል ሥራ ሊሠራ እንዴት ይችላል? በፍጹም!

የቀድሞዎቹ ነቢያት፣ አበው፣ ሊቃውንት፣ መነኮሳት ለምሳሌ እነ ነቢዩ ኤልያስ፣ እነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፣ እነ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ እነ አቡነ ተክለሐዋርያት ሃይማኖታዊ ባልሆነ ጉዳይ ድሀ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ!” ብለው ብቻ ሠማዕትነትን ተቀብለው ለክብር ሲበቁ የዛሬዎቹ ቤተክርስቲያን እየፈረሰ፣ ዶግማ ቀኖና ሥርዓት እየተጣሰ፣ መንጋው እየታመሰ እየተወረሰ፣ የቤተክርስቲያን ጥቅም እየተገሠሠ ቅንጣት ታክል የማይሰማቸው ሆነዋል፡፡ እነኝህ ናቸው ታዲያ በእነኛ አባቶች እግር የተተኩ?

ዛሬ ተራ ምዕመናን እንኳ የዚህች ሀገረ እግዚአብሔር፣ የቅዱሳኑ የዐሥራት ሀገርና የቅድስት ቤተክርስቲያን ወይም የሃይማኖታቸው ነገር ገዷቸው የአማራንና የኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሰራራ አድርጌ ሰብሬያለሁ!” እያለ የሚፎክረውን አላዊውን የጉግማንጉግ መንጋ ወያኔን በመቃወም በመታገላቸው በወያኔ እስር ቤቶች ታጉረው ስንት ሰቆቃ እየተቀበሉና ስንት መሥዋዕትነት እየከፈሉ ባሉበት ዘመን ምሳሌ አርአያ መሆን የሚጠበቅባቸው እረኞች ነን!” የሚሉት ግን ከቶ እንዲያው ምንም እንዳልተፈጠረ ስቀው ይውላሉ፣ ሆዳቸውን ሞልተው ተኝተው ያድራሉ፣ እራሳቸውን ጠብቀው ይኖራሉ፡፡ አባቶቻችን ናቸው የምትሏቸው እንግዲህ እነኝህ ናቸው፡፡ በደላቸው ሃይማኖቱን ከካደ ሰው እጅግ የከፋ ነው፡፡

ፍካሬ ኢየሱስ በስምንተኛው ሽህ ካህን ይጠፋል!” ሲል ቆብ የደፋ፣ ቀሚስ ያጠለቀ፣ መስቀል የጨበጠ ይጠፋል!” ማለቱ ሳይሆን ለሃይማኖቱ ያደረ፣ ፈጣሪውን የሚፈራ፣ አደራውን የጠበቀ ካህን አይኖርም ማለቱ ነበረ። እንደምታዩት የሆነውም ይሄው ነው፡፡ ይህ ዘመን ለሆዱ ብቻ ያደረ፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ ምንደኛና ስመ ካህንማ እንደ አሸን የሚፈላበት ዘመን ነው፡፡ በመሆኑም እነኝህ አባቶችበዚህ ወያኔ እያደረገው ባለው የሀገርና የቤተክርስቲያንን ሀብት ንብረት ዘረፋ ጉዳይ ላይም የተዘረፈው የሀገር ሀብት እንዲመለስ፣ የቀረውም ባለበት እንዲቀመጥ የማይንቀሳቀሱና ምንም የማይሉ መሆኑን ሳስብ እጅግ ሐዘን ይሰማኛል፡፡

ወያኔ ግን ይሄ እያጋዘው ያለው ሀብት አልበቃው ብሎ እናት አባቶቻችን ከጣሊያን ሠውረው ያተረፏቸውን አልፎ አልፎ በየአብያተክርስቲያናቱ ያሉ ከወርቅ ከብር የተሠሩ ንዋዬ ቅድሳትንና ዋጋ ያወጡልኛል!” ያላቸውን ቅርሶቻችንን ፍልፍል አድርጎ መዝግቦ ይዞ ቆይቶ አሁን አገልጋዮቹን ካህናት ተብየዎቹን በመጠቀም ጠራርጎ ሊወስድልህ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

አንዳንዶቹንማ እንዲያውም በሽሽግ እንደወሰዳቸው ይሰማል፡፡ እንግዲህ ምን ትሆነው? ለመሆኑ ይሰማሀልስ? ወኔውና ቁጭቱ ካለህ ወያኔ የአማራንና የኦርቶዶክስን አከርካሪ አንዳያንሰራራ አድርገን ሠብረናል!” እያለ በይፋ እየደነፋና ቤተክርስቲያንን እያጠፋ እያለ ለወያኔ እየሠሩ፣ ወያኔን እየደገፉ፣ ወያኔን እያገለገሉ ያሉ እነኝህን ምንደኛ፣ ከሀዲ፣ ተኩላ፣ ለሆዳቸው ብቻ ያደሩ እርኩስ ስመ ካህናትን በምትችለው መንገድ ሁሉ ያለምንም ርሕራሔ መንጥረህ አጥፋ!!! ይህ ተግባርህ ጽድቅ እንጅ አንዲትም ኃጢአት እንደሌለበት አረጋግጥልሀለሁ! ይሄንን ተግባር ብትፈጽም በእግዚአብሔር መንግሥት እጣ ክፍልህ እልፍ አረማውያንንና ከሀድያንን በሰይፍ እየቀሉ ከፈጁት ምሥራቃውያን ሠማዕታት ወይም ሮማውያን በመባል ከሚታወቁት ከነ ሠማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዮስ፣ ከነ ቅዱስ ፋሲለደስ፣ ከነ ቅዱስ ቴዎድሮስ፣ ከነ ቅዱስ ጊጋር ወዘተረፈ የቤተክርስቲያን ከዋክብት (በነገራችን ላይ እነኝህ ቅዱሳን ሠማዕታት ለካቶሊኮችም ቅዱሳን ናቸው) ጋር ይሆናል፡፡ በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና!” ሮሜ. 134

ልብ በሉ! ከገድሎቻቸው በግልጽ እንደምንረዳው ለሠማዕቱ ቅዱስ ቴዎድሮስ ቅዱስ ሚካኤል፣ ለሠማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዱስ ገብርኤል ሠይፍ ሰጥተዋቸው አረማውያንንና ከሀድያን ጠላቶቻቸውን እንዲፈጁ ከማድረጋቸው ከእነኝህ የቤተክርስቲያን ቅዱሳን ሠማዕታት ሕይዎት የምንማረው ቁምነገር ቢኖር ክርስትና አልፎ አይሔድም፣ በጉልበቱ የማንንም ሀብት አይነጥቅም፡፡ በግፍ ከመጡበት ግን እራሱን የመከላከል ነጻነት ያለው እንጅ እንደመሥዋዕት በግ በጅምላ እየተነዱ የሚፈጁበት የቂሎች መንገድ አለመሆኑን ነው! “ቀኝህን ሲመታህ ግራህን አዙርለት፣ መጎናጸፊያህን ቢወስድብህ እጀጠባብህን ጨምርለት፣ ጠላትህን ውደድ …!” የክርስትና ሕግጋት መቸ? የት? እና ለማን? ተብሎ ቦታና ጊዜ የሚመረጥላቸው ሕግጋት መሆናቸውን ጠንቅቀን ካላወቅን ክርስትና ፈጽሞ አልገባንም ብቻ ሳይሆን እራሳችንንም አብዝተን እየዋሸን መሆናችንን ልናውቅ ይገባል!!!

እንደወትሮየ ሁሉ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!” ብየ ጽሑፌን ለመቋጨትም ወኔ አጣሁ እኮ ወገኔ! አዝኛለሁ! እጅግ በጣም ከፍቶኛል!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com