(ይድነቃቸው ከበደ)

የዴሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም የነፃነትና የዴሞክራሲ ሃይሎች ይህን ነገር በቸልተኝነት ማለፍ የለባቸውም ብየ በጽኑ አምናለሁ። እንዲህ አይነቱ ነገር በአስቸኳይ ሊታረም ይገባል-የዚህ አይነቱ የክፋት መልእክት ውጤቱ ጥሩ አይደለምና። አቶ ጃዋር በአንድ ጎሣ/ብሔር ላይ ያነጣጠረ የእርስ በእርስ ግጭት እና መተላለቀ የሚያመጣ “ዘላለማዊ እርምጃ” (ጥሬ ትርጉሙ የዘር ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ጥሪ ማስተላለፋ ነዉና) በየትኛውም መስፈርት በምንም ዓይነት ምክንያት ትክክል ሊሆን አይችልም!! ይልቁንም ለአምባገነኑ ሥርዓት መደላድል የሚፈጥርና የነፃነት ትግሉን የጎንዮሽ በማድረግ በአገራችን የእርስ በእርስ ጦርነት ማወጅ ካልሆነ በስተቀር። ትላንት አንድን ሃይማኖት ብቻ መሰረት ያደረገ (ሌሎችን ሃይማኖቶች ያሳነሰና እዉቅና የነሳ) ጥሪ ተላለፈ (በአቶ ጃዋር)፤ በዚህም ምክንያት በተነሳው ተቃውሞ ቀኑ ተስተካከለ፤ አሁን ደግሞ በጉራጌ ቋንቋ ተናጋሪዎቹ ላይ ያነጣጠረ ጥሪ ተላለፈ (በዚሁ ‘ሰዉ’)።


እንዲህ አይነቱ ነገር አልበዛም ? ሃይ ባይ አላጣም?
ቢጫዉንም ቀዩንም መስመር አልዘለለም ? … ይሄ ነገር በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም ባይ ነኝ። አቶ ጃዋር እና ተከታዮች በአስቸኳይ በዚህ ጉዳይ ላይ ማሰተካከያ ሊሰጡ ይገባል እላለሁ። እኔ በግሌ ሃይማኖትን፣ ቋንቋን፣ ጎሣን ወይም ብሔርን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ድጋፍ ወይም ተቃውሞ ከዚህም በፊት አላደረኩም አሁንም ወደፊትም አላደርግም !! አቶ ጃዋር እየረጨ ያለውን የጥላች መርዝ መቃወም የኦሮም ሕዝብ ተቃውሞ እንቅስቃሴ መቃወም ማለት አይደለም፡፡ አቶ ጃዋር ከዚህ ቀደም በክርሰትና እምነት ተከታዮች ላይ በድፍረተ ያስተላለፈው የሐይማኖት ጥላች (ክርስትያኑን በሜንጫ) መቼም የሚረሣ አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ በግልፅ አንድን ጎሣ/ብሔር መሠረት አድርጎ እርምጃ ይወሰድባቸው በማላት ከመቼውም ጊዜ በላይ የዘር ጭፍጨፋ አዋጁን
ሲያውጅ ለምን ? በማለት መጠየቅ እና ድርጊቱን መኮነን የኦሮሞ ህዝብ ለመብቱ የሚያደርገውን ትግል መቃወም እንደሆ አድርጋችሁ የጉዳዮን አሳሳቢነት ከንቱ ለማድረግ የምትጥሩ የድርጊቱ ተባባሪና አስተባባሪ ከመሆን የሚለያቹሁ ነገር አይኖርም፡፡

በእንዲህ መልኩ የሚካሄድ የትኛውም አይነት ተቃውሞ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። መደባዊ ፣ ጎሳዊ፣ ሀይማኖታዊ ልዩነት የተደረገባቸው የትኛው የፖለቲካ ሕዝባዊ ተቃውሞ አላማቸውን ከማሳከት ይልቅ የመጨናገፍ እድላቸው ሰፊ እንደሆነ የግል ምልከታ አለኝ (በታሪክም የእንዲህ አይነት ተቃዉሞዎችን ስኬት አላነበብኩም) ። የአገዛዙ ሥርዓት ሃያ ስድት አመት ሙሉ ዘረኝነትን በአገራችን በማንሰራፋት ፣የኢትዮጵያን አንድነት በማናጋት እርስ በእርስ በጥርጣሬ እና ባለመተማመን ሕብረት እና አንድነት እንዲጠፋ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ ነው። ይህን እውነት በሚገባ በመረዳት ኢትዮጵያዊያን ሃይማኖት እና ቋንቋ ሳይገድባቸው እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ በአገራችን የሕዝቦች አንድነትን በማጠናከር ሁሉም በእኩልነትና በአንድነት የሚኖርባት ሃገርን ለማቆም ብዙዎች ሕይወታቸውን እየገበሩ፣ የተቀሩት አሰቃቂ የእስር ጊዜን እያሳለፉ በሚገኙበት ወቅት አቶ ጃዋር በጎንዮሽ የዘር ማጥፋት እና ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ጥሪ ማድረጉ ከስህተትም በላይ ነው ። ስለዚህም ስህተቱን ተገንዝቦ ማስተካከያ ካልሰጠ በታሪክ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ይኖራል ! እንዲህ አይነቱን ስህተት እንዲታረም ማድረግ የሕዝባዊና ሰላማዊ እምቢተኝነት ትግልን ማገዝ እንጂ ፈጽሞ ማደናቀፍ አይሆንም!

 

 

Like this: