August 23, 2017 

ግብዓተ መሬቱ እጅግ የተቃረበው ወያኔ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ከሚጠቀምባቸው መሰሪ ድርጊቶቹ አንዱ የሆነውን በቅርቡ ይፋ አድርጓል። ይኽውም ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከመላው የአገሪቱ ማዕዘናት የሚኖሩባትን አዲስ አበባ ከተማን “ልዩ ጥቅም” በሚል ስም ለኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ብቻ ሰጥቻለሁ በማለት እስከ ሶስትና አራት ትወልድ በከተማው የኖሩትን ዜጎች መብት ለመግፈፍና ለማበጣበጥ የጎነጎነውን ሸርና በዚህም ምክንያት ከሚፈጠረው ውዥንብር ተጠቃሚ ለመሆንና በህዝብ መካከል ደም ለማቃባት በመዶለት ላይ ስላለው ሴራ በርካታ አስተያየቶች በመሰጠት ላይ ናቸው።

በዚህም መሠረት አቶ ኃይሉ ኡርጌሳ አውስትራሊያ ውስጥ በሚሰራጨው SBS የአማርኛ መርኃ ግብር ላይ “መለያየትን ሳይሆን አብሮ የጋራ ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ አለብን” በሚል መሪ ሃሳብ ላይ ተመርኩዘው የሰጡትን

https://youtu.be/dhUOp5eo2r8በሳል ትንተናና አስተያየት አቅርበንላችኋል