ከጌታቸው ሽፈራው

ኢቢሲ በሰራው አንድ ፕሮግራም ትግራይን እስከ ቤንሻንጊል የምትዘልቅበትን ካርታ አሳይቷል። ይህ ካርታ የትህነግ ታሳቢ ካርታ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን ሲነጋገሩበት የቆዩት ጉዳይ ነው። ሰሞኑን ቅማንት ይኖርባቸዋል የተባሉ ወረዳዎች ላይ ህዝበ ውሳኔ ሊደረግ ነው ተብሏል። የወልቃይት ማንነት ጉዳይ ሽብር ሆኖ በርካቶችን ሲያሳስርና ሲያስገድል ትህነግ (ህዋሃት) ህዝብን ለመከፋፈል የፈጠረው የቅማንት ፕሮጀክት ስኬታማ እየሆነለት ይመስላል። ከወልቃይት እና ሌሎች ጉዳዮችን ለማስረሳትና ህዝብን ለመወጠር ከመጠቀሙም ባሻገር ጠላት ያለውን ህዝብ ለመለፋፈል፣ ለማጥቃት ከዚህም አልፎ በኢቢሲ የታየችውን ካርታ እውን ለማድረግ እንደ አማራጭ ሊጠቀምበት እንደሚችል መገመት ይቻላል።

ትህነግ ወደ ስልጣን እንደወጣ ወልቃይትን ወደ ትግራይ ሲከልል ተቃውሞ እንደነበር ከታሪክ የምንረዳው ሀቅ ነው። በብአዴን ካድሬዎችና በትህነግ አዛዦቻቸው መካከል ወልቃይትን አስመልክቶ መጠነኛ አለመግባባት እንደነበር የካድሬው ማስታወሻ የተሰኘ መፅሃፍ ላይ ተገልፆአል። በየጊዜው ትህነግ የእብደት እርምጃ ሲወስድ መጠነኛ ማጉረምረም ውጭ የረባ ተቃውሞ የማያሰማው ብአዴን አሁንም የቅማንት ጉዳይ ወደየት ሊያመራ እንደሚችል እያወቀ ተባባሪ ከመሆን አላለፈም። በትህነግ እሳቤ ቅማንት ይኖርባቸዋል የተባሉት ወረዳዎች ትግራይን ወደ ቤንሻንጉል የሚያሻግሩ ናቸው። ቢያንስ በሂደት ሌሎቹን አካባቢዎች እያፈናቀሉም ሆነ “ቅማንት ናቸው!” ብለው ይህን ድልድይ ከመስራት ወደሁዋላ የሚሉ አይመስለኝም።

 

በሌላ በኩል ለሱዳን የተሰጠው መሬት የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሁንም አምነው አልተቀበሉም። የሚያግዛቸው አላገኙም እንጅ። ሱዳናውያን የተሰጣቸውን መሬት አንድ ቀን ለኢትዮጵያውያን መልሰው እንደሚሰጡ እሰከማመን ደርሰዋል። አብዛኛዎቹ ከኢትዮጵያ ገበሬዎች የሚደርስባቸውን ጥቃት በመፍራት ለኢትዮጵያውያን እያከራዩ ነው። ከተከራይ ባለሀብቶች መካከልም ይዞታቸውን ለማስፋት ጊዜ የሰጣቸው የትህነግ ባለሀብቶች ይገኙበታል። እነዚህ ባለሀብቶች በመተማና በቋራ በጣም ሰፋፊ መሬት አላቸው። ትህነግ በድርጅቶቹ ስም ማንም ያልያዘውን የሰሊጥ እርሻም በእጁ አስገብቷል። በአጭሩ ትግራይ ተብሎ ባይከለልም በአብዛኛው በእነሱ እጅ ነው። ለሱዳን ከተሰጠውና ትህነግ ባለሀባቶች ከተከራዩት ጋር ሲደመር በመተማና አካባቢው በትህነግ ይዞታ ስር የሆነው መሬት ትግራይን ወደ ቤንሻንጉል ለማሸጋገር አንድ ገመድ ነው።

የኢትዮጵያ ገበሬዎች ይህን መሬት መቼም አምነው እንደማይቀበሉ የሱዳን መንግስትም ይረዳዋል። ትህነግም በተመሳሳይ ይህን መሬት ከኢትዮጵያውያን አእምሮ መፋቅ እንደማይችል በተግባር አይቷል። በመሆኑም ባለሀብቶቹ እንዲከራዩት በማድረግ፣ በድርጅቶቹ በኩል በመያዝ ከሱዳን ጋር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚችል ጥርጥር የለውም። ሰፊ መሬት ያላት ሱዳን ወትሮውንም “አንቺ ጋር ይቀመጥልኝ” ተብላ ካልሆነ ይህን መሬት በተለየ ትፈልገዋለች ብሎ ለማሰብ ይከብዳል። ከዚህ መሬት ጥቅም ተካፋይ ነች ብትባል እንኳ ፍላጎቱ የመጣው ” እሰጥሽና ታካፍይኛለሽ” ሊላት ከሚችለው ትህነግ ሊሆን እንደሚችል ፍንጮቹ ይበልጥ እየጎሉ ነው። ሱዳን የተሰጣትን መሬት ትህነግ በቅኝ ከያዘው ኡትዮጵያ የፈለገችውን ጥቅም እስካገኘች ድረስ መልሳ የምታስረክበው ነው።

ትናንት ኢቢሲ ላይ በተላለፈው ፕሮግራም የታየው ካርታ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ትህነግ ለረዥም ጊዜ ሲያስብበት የቆየው ጉዳይ ነው። በኢቢሲ ላይ የተለቀቀው ካርታ በስህተት ነው ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ከአሁን ቀደም ዳሸን ተራራን ትግራይ ክልል እንደሚገኝ አድርገው መማርያ መፅሃፍ ላይ አትመዋል። ይህ ሆን ተብሎ የህዝብ ሙቀት ለመለካት እና የነገ እቅዳቸውን ለማለማመድ የሚያደርጉት እንጅ በስህተት የሚለቀቅ መረጃ አይደለም። ኢቢሲ አልተሳሳተም። ትህነግ ሆን ብሎ ዘራዕይ አስግዶም ድርጅቱ ውስጥ በሰገሰጋቸው ካድሬዎች በኩል የተሰራ የሴራ ፕሮግራም ነው። በዚህ ፕሮግራም ምላሻችን መስማት ይፈልጋሉ። ሌላ ጊዜም መሰል መረጃ እየለቀቁ ቀስ አድርገው አለማምደው ወደ ፕሮጀክታቸው ይጠጋሉ። ለምሳሌ ኢቢሲ በፌስቡክ ያስተላለፈውን የይቅርታ መልዕክት በዜና እንዲሰራው የሚጠይቁ ፌስቡከኞች ተመልክቻለሁ። ትህነግ የሚፈልገው ይሄን ነው። ፕሮጀክቱን ሳይሆን የኢቢሲ ስህተት መሆኑን አመንን ማለት ነው። ነገም ደግመውት ይቅርታ ይጠይቃሉ። ፕሮግራም ሲሰሩ፣ ይቅርታ ሲሰሩም የምናስታውሰው ስለ ታላቋ ትግራይ ነው። ስለ ታላቋ ትግራይ ማስታወቂያ እየሰሩ መሆኑን አልተረዳንም።

የተሳሳተው ኢቢሲ ሳይሆን እኛ ነን። በፌስቡከ የተሰጠችው ይቅርታ እንኳ ቀድማ የታሰበች መሆን አለባት። እኛ ተላላዎቹ በዜና ይቅርታ ሲባል ጩከታችን ይበርዳል። እነሱ ሌላ ማስታወቂያ እስኪለቁ ስራቸውን ይቀጥላሉ። ሌላ በትንሽ ይቅርታ የምንበርድባት ማስታወቂያ እስኪሰሩ እኛም ዝም እንላለን። እንዲህ እያልን ትህነግ በአሳላጭ መንገድ ወደ ቤንሻንጉል ለማቋረጥ የተዘጋጀበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

 

 

ታላቋ ትግራይን እንድለማመድ የተለቀቀው ካርታና የኢቢሲ ይቅርታ | ቬሮኒካ መላኩ

1~የEBC ን ውሃ የማያነሳ ማስተባበያና ይቅርታ አነበብኩት ። ፈረንጅ ሲተርት እንደዚህ ይላል “Fool me once, shame on you; Fool me twice, shame on me”…( አንድዬ ካታለልከኝ በአንተ አፍራለሁኝ ። ለሁለተኛ ጊዜ ካታለልከኝ ግን በራሴ ቂልነት አፍራለሁኝ ።) ይላል።


 

 

 

 

 

 

 

 

በእኔ በኩል EBC የሚያታልለው ንቃተ ህሊና ባለቤት ስላልሆንኩኝ “ይቅርታው ” ይለፈኝ።

 

በእኔ በኩል EBC የሚያታልለው ንቃተ ህሊና ባለቤት ስላልሆንኩኝ “ይቅርታው ” ይለፈኝ።

 

በሌላ በኩል EBC ን ማመስገን ይገባል እንደዚህ ያለ ስሜት ኮርኩሮ የሚያቃጥል ድብቅ ሴራ እያቀረበ የደነዘዙ አማሮችን ቀስቅሶ ወደ አማራነት ካምፕ እንድቀላቀሉ ስለአነቃልን መመስገን አለበት።

 

ለማንኛውም ስህተቱ የተሰራው በፌስቡክ ሳይሆን በቴሌቪዥን ስርጭት ላይ በመሆኑ ይቅርታውም መጠየቅ ያለበት በቴሌቪዥን እንጅ ከጠቅላላው ህዝብ 1% የማይሞላ ህዝብ በሚጠቀምበት በፌስቡክ አይደለም።

 

3~ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተተክሎ አማራ ህዝብ ውስጥ የሚቀበር የ Time bomb ፋብሪካ ቶሎ ካልመከነ አማራ በአገሩ Homeless መሆኑ የማይቀር ነው ።

 

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የመምህርነትና የሰራተኝነት ጭምብል አጠልቆ አዲስ የፖለቲካ መልክአ ምድር ለመፍጠር ፕሮጄክት ቀርፆ አማራን ከባድና ሊወጣው የሚያስቸግር አደጋ ከመደቀኑ በፊት እንደት ማስቀረት እንደሚቻል ማሰብ አለብን።

 

4 ~የዚህ Time bomb ፋብሪካው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የቦምቡ ማፈንጃ እና መቆጣጠሪያ ሪሞት ኮንትሮል ደሞ የሚመረተው መቀሌ ነው።

 

አማራ አፍንጫህ ስር መሽጎ “የቦምቦች ሁሉ እናት ” እያመረተ የሚቀብርብህን “መርስኔሪ ” ቶሎ መፍትሄ ካልሰጠህው ማለቅህ ነው። እኛ አሁንም ተኝተናል እነሱ ግን 7ቱንም ቀናት እና 24 ሰአታት አማራን ለማጥፋት እየሰሩ ነው።

 

5~ አማራ ሆይ በየአመቱ ፣ በየወሩ ፣ በየሳምንቱ በየቀኑ ፣ በየሰአቱ ፣ በየደቂቃው እና በየሰከንዱ እየተሰረቀ እና እየተዘረፈ ያለውን ማንነታችንን ፣ መሬታችንና ርስታችንንርስታችንን ለማስመለስ በአንድ ላይ ካልቆምን መጥፋታችን ነው።