August 27, 2017 11:37

ሚክይ ዓምሃራ

ጎንደር ላይ ቅማንንትና አማራ ብሎ ለመሰንጠቅ እየተካሄደ ያለዉ አካሄድ መጨረሻ ሁለቱንም ህዝቦች የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም ነገር እንደሌለዉ ልናሰምርበት ይገባል፡፡ ሁለቱ ህዝቦች ተቀላቅለዉ የኖሩ ተጋብተዉና ልጅ ወልደዉ አንድ ሁነዉ የሚኖሩ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የጊዜዉ ፖለቲካ ያነሆለላቸዉ ሰወች ከህወሃት የስራ አስፈጻሚዎች ጋር በመሆን የደንበር አጥር ለማጠር ዝግጅታቸዉን ጨርሰዋል፡፡ ተወዳጁ የቅማንንት ማህበረሰብ ይሄን ሴራ ከእህቱና ወንድሙ አማራ ጋር ሁኖ ማክሸፍ አለበት፡፡ ደንበር ማጠሩ እጅግ አላስፈላጊ የሆነና የህወሃት ትግሬ ፍላጎት መሆኑ ሁላችንም እናዉቀዋለን፡፡ የማንነት ጥያቄዉ እንዳለ ሆኖ አብዛኛዉ የቅማንንት ማህበረሰብ ግን እንዲህ አይነት የደንበር ማካለል መኖር እንደሌለበት ነገር ግን ማንነቱን፤ባህሉንና ትዉፊቱን እያሳደገ ከአማራዉ ወንድሙ ጋር እንዲኖር ነዉ የሚፈልገዉ፡፡አማራ ሁኖ ቅማንንት፤ቅማንንት ሆኖ አማራ ያልሆነ እስኪ ጎንደር ዉስጥ የት ይገኛል፡፡ ይሄ ሲራ የራሱን የቅማንንት ሃብትና ንብረት የሆነዉን የወልቃይትና ጠገዴን ጥያቄ ህወሃት ለማድበስበስ የሚጠቀምበት ስልት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡

መፍትሄዉስ ምን ይሁን

1. ቅማንንት የሚለዉ የማንነት ጥያቄ በቅማንንት ብቻ ሳይሆን በሌላዉ ማህበረሰብ ተቀባይነት አግኝቶ የቅማንንት ባህልና ወግ ቋንቋና የመሳሰሉት መገለጫዎች እንዲያድጉ ርብርብ ማድረግና ባህሉና ማንነቱ የሁላችን ስለሆነ እንዲሁም ሃብታችን ስለሆነ ተንከባክበነዉ የአንድነታችን ገመድ እንዲሆን መስራት፡፡ ይሄን ስናደርግ በተለይም ከሁለቱ ማህበረሰብ የተወለዱ በሽወች የሚቆጠሩ ህጻናት የማንነት ቀዉስ (Identity crisis) ዉስጥ እንዳይገቡ ያደርጋል፡፡ በማንነት ቀዉስ ዉስጥ የሚያድጉ ህጻናት የትምህርት ቅቡልነት፤ፈጣሪና ተመራማሪ የመሆን እድላቸዉ ያነሰ ነዉ፡፡ የዘመናት አብሮነታችንም ያጠናክራል፡፡

2. ደንበር ማካለልን ማስወገድ፡፡ በሁለቱ ህዝቦች መካከል አጥር ማጠር ኪሳራዉ ለሁለቱም በተለይም ለገበሬዉ ነዉ፡፡ በሁለቱም በኩል ያሉት ገበሬወች ተንቀሳቅሰዉ በተለይም ወደ ቆላማዉ አካባቢ ባለዉ በሰሊጥና ማሽላ እርሻ አርሰዉ የሚጠቀሙና ሀብት የሚያፈሩ ናቸዉ፡፡ የራስ አስተዳደር ብለን ደንበር በምናጥርበት ጊዜ ግን ይህን እንቅስቃሴ ሊጎዳ የሚችል ሲሆን በተለይም አካባቢዉ በግብርና ከመተዳደሩ አንጻር ገበሬወች ከፍተኛ ችግር ዉስጥ ይወድቃሉ፡፡ ለሁለቱም የሚጠቅመዉ አማራጭ ልዩ ወረዳ ሳይሆን አንድ ላይ ሆኖ የቅማንንትን ማንነት ተቀብሎና አክብሮ መኖር ጠቃሚ ነዉ፡፡

3. ሰሜን ጎንደር አጠቃላይ በህወሃት ከ26 አመት ጀምሮ እንዲጠፋና ለአካባቢዉ የሚሆነዉን የእርሻ መሬት ወደ ትግራይ በመከለል የቅማንንትና የአማራ ህዝብ በድህነት እንዲኖር ሲያደርግ የቆየ ነዉ፡፡ አሁንም የቀረችዉን ትንሽ ሪሶርስ ለምሳሌ አንደ መተማና ሰሜን ተራራን አካባቢ ወደ ራሱ ለመዉስድ ሲል የጎንደርን ህዝብ ከፋፍሎ ለማናከስ እየጣረ ነዉ፡፡ የሰሜን ተራራ ሃብት የቅማንንት ነዉ የአማራም ነዉ፡፡ መተማ የቅማንነት ነዉ የአማራም ነዉ፡፡ ስለዚህም የሁለቱ ህዝቦች እጣ ፋንታ እጅና ጓንት ሁነዉ ሃብታቸዉን ማስመለስና ገበሬዎች እንዲጠቀሙ ማድረግ ነዉ፡፡በባለፉት 26 አመት ትግሬ ወያኔ ሲገለንና ሲያቆስለንና፤ ሲያሳድደን የኖረዉ ቅማንንትና አማራ እያለ ሳየሆን በጅምላ ነዉ፡፡ ስለዚህም ወደፊትም ቢሆን የተለየ እጣ ፋንታ አይኖረንም፡፡

4. አማራና ቅማንንት አጥር በመካከላቸዉ ሳያጥሩ ከዚህ በፊት ተዋደዉና ተከባብረዉ በኖሩበት አካባቢ ህወሃት መስመር እንዲያሰምርልን መፍቀድ የለብንም፡፡ ነገር ግን የቅማንነትና አማራ ገበሬ ሊጠቀምበት የሚችለዉን የሰሜን ጎንደር ቆላማ አካባቢ በተለይም ሰሊጥና ማሽላ አብቃይ የሆነዉን የመተማ፤ቋራና ታች አርማጭሆ 95 % የሚሆነዉ የእርሻ መሬት የተያዘዉ በትግሬዎች ነዉ፡፡ ይሄን ተባብረን አስለቅቀን ለሰሜን ጎንደር ወጣቶችና ገበሬወች ማከፋፈልና ሀብትና ንብረት ማፍራት ያስፈልጋል፡፡ለምሳሌ አንኳን ብናይ በባለፉት ሁለት አመታት አማራና ቅማንንት ብሎ ሰወችን በማቃቃር የቅማንንት ባለሃብቶችና ገበሬወች በነዚህ አካባቢዎች ወርደዉ እንዳያርሱ አድርጓል፡፡ ባንጻሩ ግን የትግራይ ተወላጆ በባለፉት ሁለት አመታት ሰፋፊ የእርሻ መሬት በመዉስድ በስፋት እያመረቱ ይገኛሉ፡፡

5. የጎንደር ታሪክ የቅማንንትና የአማራ ታሪክ ነዉ፡፡ አሁን ቅማንንትን ልዩ አስተዳደር በማለት ከራሱ ታሪክ ጋር ለመለያየት ህወሃት ሌት ከቀን እየሰራ መሆኑን መገንዘብ አለብን፡፡

6. በባለፉት አመታት ባካባቢዉ ግጭት አንዲነሳ በማድረግ ተማሪዎች ተረጋግተዉ ትምህርታቸዉን እንዳይማሩ ብሎም ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናዉን አባዛኛዉ የሰሜን ጎንደር ተማሪዎች ማለፍ እያቃታቸዉና የወደፊቱ ትዉልድ እየሞተ ይገኛል፡፡ ባንጻሩ ትግራይ ክልል ዉስጥ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ በቀላሉ የሚገቡበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ፡፡ ስለዚህም ህወሃት ሁላችንም ይዞን ለመጥፋት እየሰራ መሆኑን ልናዉቅ ይገባል፡፡

7. በሶሻል ሚዲያ በማያታወቅ ስም አማራንና ቅማንንትን ሲሳደቡ የሚዉሉ ሰዎችም እያየን ነዉ፡፡ እኒህ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ትግሬወች ሲሆኑ ጎንደር ተወልዶ ያደገ ቅማንንትም ሆነ አማራ በሞራልና በስነ ምግባር ታንጾ ያደገ እንጅ አስነዋሪ ስድብ የመለዋወጥ ባህሪ የለዉም፡፡ ጎንደሬ ከከፋዉ ፊት ለፊት ሳይፈራ የሚጋፈጥ እንጅ ተደብቆ ድንጋይ የመወርወርና ህዝብን በስድብ የማንኳሰስ ባህሪ የትግሬ ባህሪ ነዉ፡፡ ስለዘህም በነዚህ የትገሬ ሰወች ሳንዘናጋና ሳንደናገር ሴራዉን አብረን ልናከሽፍ ይገባል፡፡

8. ሰሞኑን በኢትቪ ያየነዉ ካርታ አማራ ክልልን ሙሉ ለሙሉ ከሱዳን ጋር እንዳይዋሰን የሚያደርግ ነዉ፡፡ ይሄም የታሰበዉ በሁመራ በኩል አድርጎ የመተማ፤አለፍ ጣቁሳንና ቋራን ወደትግራይ በማካለል የአባይ ግድብ ድረስ ታላቋ ትግራይን መመስረት አላማዉ ነዉ፡፡ ይሄ ከፊሉ ለሱዳን ከፊሉ ለትግራይ ሊሰጥ የታሰበ መሬት የቅማንንትና የአማራ ሃብት ነዉ ስለዚህም አንድ በመሆን የሄን የሩቅ ጠላታችን ማንበርከክ ያስፈልገናል፡፡ ዞኑን ከፋፍለዉ ለመዉሰድ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለማስቆም ባንድነት መነሳት ያስፈልገናል፡፡

የመጨረሻዉና ዋናዉ ነገር፡፡ የቅማንንት ማንነት እንዲከበር እንዲያድግ ሁሉም ይረባረብ ነገር ግን ሁለቱ የማይሰነጠቁ ህዝቦችን የራስ አስተዳደር ወይም ሪፍረንደም በማለት ለመሰንጠቅ እየተካሄደ ያለዉን ሴራ ሽማግሌወች ልትፈቱት ይገባል፡፡ማንነትንና ባህልን ለማሳደግ አጥር ማጠርና መሬት መካፈል አይኖርብንም፡፡

የቅማንንት ማንነት የአማራ ሀብቱ እንዲሁም የአማራ ማንነት የቅማንንት ንብረቱ በመሆኑ በደንበርና በመሬት ተነጣጥለን የምናሳድገበት ሁኔታ አይኖርም ይልቁን ባንድነት ሁነን ተጋግዘን ወደ ብልጽግና የምናመራበት እንጅ፡፡

ከዚህ በታች የምናየዉ ካርታ ባለፉት አመታት ያለው የሰሜን ጎንደር ዞን ሲሆን አብዛኛዉ የቅማንንት ማህበረሰብ በላይ አርማጭሆና ከፊል ጭልጋ ይገኛል፡፡ ነገር ግን በዞኑ ዉስጥ በየትኛዉም አካባቢ ሁለቱም ህዝቦች ባንድ ላይ ተከባብረዉ የሚኖሩ ናቸዉ፡፡ ከካርታዉ እንደምንረዳዉ እጣ ፈንታችን አብሮነት እንጅ ልዩነት አለመሆኑን ያሳያል፡፡