August 30, 2017 10:12

በተለይም አክራሪ ኦሮሞዎች እኛ በምንጽፈው ጽሁፍ ይናደዳሉ። የሚናደዱት የነርሱን ዘረኝነት አጉልተን ስለምናወጣውና ሳንፈራና ሳንሸማቀቅ ስለምንቃወማቸው ነው። እንጅ እነርሱ ለኦሮሞ ቆመናል እያሉ ከሚያደርጉትና ከሚናገሩት የበለጠ እኛ የምናቀርባቸዉን ሐሳቦች ለኦሮሞ ማህብረሰብ የበለጠ ሳይጠቅሙ ቀርተው አይደለም።

ኢትዮጵያ ዉስጥ አሁን ያለው የጎሳ/ዘር ፌዴራሊዝም መለወጥ እንዳለበት አጥብቄ አምናለሁ። የጸና አቋሜ ነው። አዲስ አበባን ያካተተ ሸዋ የሚባል ክልል መኖር አለበት ብዬ እሟገታለሁ።

ሆኖም ግን በ #OromoProtests ጊዜ አንዳንድ ሁኔታቸው ባይመቹኝም (በተለይም የብዙ ወገኖች ደም ያለበት የዘረኛዉን ኦነግ ድርጅት ባንዲራ ይዘው ሲሰለፉ) መሰረታዊ ጥያቄያቸው ገበሬዉ ከመሬቱ እንዳይፈናቀልና በሕወሃት አገዛዝ የሚፈጸምባቸው ሰቆቃ እንዲቆም በመሆኑ፣ የኦሮሞ ወጣቶችን ትግል ደግፊያለሁ። የ #OromoProtests አድማሱን እንዲያሰፋና ሌሎች ማህብረሰቦችም የ#OromoProtests ን እንዲቀላቀሉ፣ የ #OromoProtests ወደ #EthiopiaProtestsእንዲለወጥ የኦሮሞ ማህበረሰብ ጥያቄ ከሌሎች ማህበረሰብ ጥያቄዎች ጋር በማጣጣም ፣ ትግሉን ሊያሰባስብ የሚችል ባለ አምስት ነጥብ ሀሳብ፣ ከአንድ አመት ተኩል በፊት (ማርች 2016) አቅርቤ ነበር።

የሚከተለውን ነበር የጻፍኩት ፡

====================
መከራከር፣ መለያየት ቀላል ነው። ያሉ ልዩነቶችን ማስፋት ቀላል ነው። መፍትሄዎችን ግን ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው ችግሮች በመዘርዘርና በማስፋት ሳይሆን ሁሉም አሸናፊ ሊሆኑበት የሚያደርግን የመፍትሄ ሐሳቦች በማቅረብ ነው። የተለያዩ ወገኖችን በመፍትሄ ሀሳብ ዙሪያ ለማቀራረብ የሚከተሉት ባለ አምስት በጥቦች ተዘርዝረዋል።

1. በፌዴራል አወቃቀር ዙሪያ የተለያዩ ልዩነቶችና አለመስማማቶች አሉ። ሆኖም ወደፊት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ተገንብቶ፣ ፓርቲዎች ያሏቸውን አቋም በግልጽና ያለፍርሃት ለሕዝብ አስተዋዉቀው፣ ሕዝብ ከፈለገ የአስተዳደር መዋቅሩእንዲቀጥል ማድረግም ሆነ መቀየር መብቱ እንደሆነ በማረጋገጥ በጊዜያዊነት ግን አሁን ያለችው የኦሮሚያ ክልል እንዳለች ብትቀጥል፤ ለአስተዳደር አመችነት እንዲኖር ለዞኖች የበለጠ ስልጣን ቢሰጥ ጥሩ ነው።

2. አዲስ አበባ ለብቻዋ የፌዴራል ክልል መሆኗ ቀርቶ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉትን አካባቢዎች በማካተት ወይንም ከምስራቅ ሸዋ ወይንም ሰሜን ሸዋ ዞን ጋር በመቀላቀል የራሷ ዞን ሆና፣ ሙሉ በሙሉ በኦሮሚያ ክልል ሥር እንድትሆን ቢደረግና ጥሩ ነው። አዲስ አበባን ያካተተው ዞን የፊንፊኔ ዞን ተብሎ ሊጠራ ይችላል።

3. ማንም ኢትዮጵያዊ በማንኛው የአገሪቷ ክፍል የመኖር፣ የመነገድ፣ ኢንቨስት የማድረግ፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ ሙሉ መብት አለው። ማንም ኢትዮጵያዊ በሃይማኖቱ፣ በጾታው፣ በብሄር ብሄረሰብ ማንነቱ አድሎና ልዩነት አይደረግበትም።በመሆኑም ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ሳይሆን የክልሉ ነዋሪዎች ነው የምትሆነው። የኦሮሚያ ነዋሪ እስክሆኑ ድረስ ቶላ፣ ሃጎስ፣ ሸምሹ፣ ሸዋንግዛው፣ ኦኬሎ፣ ቤርሳሞ …..ሁሉም እኩል ናቸው።

4. የኢትዮጵያ ህዝብ ወይንም የክልል ሕዝቦች አሥር በመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን እንደ አንደኛ ቋንቋ የሚናገሯቸው ቋንቋዎች የኢትዮጵያ ፌዴራል የሥራ ቋንቋ ይሆናሉ። በዚህ መሰረት አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ የፌዴራል ቋንቋ ይሆናሉ ማለት ነው ። አማርኛ እና አፋን ኦሮሞ የኦሮሚያ ክልል የሥራ ቋንቋ ይሆናሉ። ወደፊት ኤርትራና ሶማሌላንድ ወድደ ኢትዮጵያ ከተቀላቅቀሉ ደግሞ ሶማሌኛና ትግሪኛም ሊጨመሩ ይችላሉ።ለምን ቁጥራቸው ጨምሮ ወደ 10% ሊደርሱ ስሚችሉ:
5. በኦሮሚያ (አዲስ አበባን ጨመሮ) አማርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ አፋን ኦሮሞ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ይሰጣል። በሌሎች ክልሎች ከእንግሊዘኛ እና ከአማርኝ በተጨማሪ ሌላ ሶስተኛ የኢትዮጵያ ቋንቋ በትምህርት ቤቶች ይሰጣል። በደቡብ፣ በሶማሌ፣ በአፋር በመሳሰሉ ክልሎች ኦሮምኛ ትምህርት ባይሰጥም፣ በአማራው ክልል ከዘጠና በላይ በሚሆኑት አካባቢዎች (በጎጃም፣ በአብዛኛው ወሎ፣ በሸዋ) አፋን ኦሮሞ ትምህርት ይሰጣል። በሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ምናልባት ትግሪኛ መማር ህዝቡ ሊመርጥ ይችላል።
====================
እንግዲህ አስቡት፣ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ስምምነት ለማግኘትና ትግሉን ማሰባሰብ ይቻል ዘንድ፣ ምን ያህል በግለሰብ ደረጃ ካለን አቋሟ ወጥተን ወደነርሱ እንደመጣን ። ሆኖም ግን ይሄ ሐሳብ በነርሱ ዘንድ ተቀባይነት አላገኝም። በኦሮሚያ አማርኛ ከአፋን ኦሮሞ ጋር የሥራ ቋንቋ እንዲሆ በጭራሽ አይፈልጉም። ኦሮሚያም የነዋሪዎችዋ ሳይሆን የኦሮሞ ነው ከሚለው ዘረኛ አመልካከታቸው ፍንክች ሊሉ አልቻሉም። እነርሱ የሚፈለጉት ይሄ ኦሮሚያ የሚሉትን ቦታ ሙሉ ለሙሉ de-amharized እንዲሆን ነው።፡እነርሱ የመሬቱ ባለቤት ሆነው ሌላው ማህበረሰብ ግን በአገሩ ባዳ ሆኖ እንዲቀጥል ነው።

እነርሱን ለማሳመን እና ለማግባባት ብዙ ሞከርን። መጨረሻው ግን በለንደን እና በአትላንታ እንዳየነው ፣ አብረን እንስራ ማለታችንን እንደ ድክመት ቆጥረውት “ኢትዮጳን መበታተን ነው” ብለውን አረፉት። እነርሱ ጠባብ ስለሆኑ ፣ ጠባብነት ደግሞ በባህሪው rationalize ማድረግን ስለማያስችል፣ ከነርሱ ጋር ለመስራት መሞከር በድንጋይ ላይ ዉሃ እንደማፍሰሰ እየሆነ ነው።

እነርሱ ላይ ጊዜ ከማጥፋት የነርሱ ፖለቲካ በማሸነፍ፣ የኦሮሞ ማህበረሰብ በነዚህ ሰዎች ሳይወናበድ፣ ለአንድነት ሃይሉ ጋር በመተባበር፣ ኦሮሞው፣ ሌላው ሁሉ እኩል የሆኑባት አገር፣ ሁሉም በሁሉም የአገሪቷ ክፍል በሰላም የሚኖርባትን ኢትዮጵያ እንዲገነባ ማስተማር፣ ማንቃትና ማደራጀት ያስፈለጋል። የኦሮሞ ማህበረሰብ በነዚህ ሰዎች ያገኘው ነገር ቢኖር፣ ከሌላው ማህበረሰብ ወንድሙ ጋር መጣላትንና በአገሪቷ ኢኮኖሚ ተጠቃሚ አለመሆንን ነው።

መሆኑ አርቆ አሳቢ ለሆኑ የኦሮሞ ወገኖቼ ጥሪ አቀርባለሁ።የናንተ ዝምታ ነው ለዘረኛዉን ለከፍፋፋዩ ክፍተት የፈጠረው። የኦሮሞ ማህበረሰብ ጥያቄ ይፈታ ዘንድ፣ ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ያሉ ልዩነቶችም ጠበው መቀራረቡ ይመጣ ዘንድ ተግተው እንዲሰሩ በአክብሮት እመክራለሁ።

ከአንድ አመት ተኩል በፊት ኦሮሚያ አሁን እንዳለችው ትቅጥል ያልኩት በጊዜያዊነት፣ ህዝብ እንደገና መክሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ብቻ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። በኔ እይታ አሁን ያለው የኦሮሚያ ክልል መቀጥል ያለበት ክልል አይደለም። ለአስተዳደር በጭራሽ አያመችም። አዲስ አበባን ያካተተ ሸዋ የሚባል ክልል መኖሩ በጣም አስፈላጊ ነው። ሆኖም ግን ይሄንን ሐሳብ ይዘን ሕዝብን ማሳመን ያስፈልጋል። እኛን የሚቃወሙም መብታችንን አክብረው እነርሱም የሚያምኑበት ያቅርቡ። ህዝብ እንዲወስን ይደረግ። እያንዳንዱ ወረዳና ዞን ድምጽ ይስጥበት። ያ እስኪሆን ድረስ ግን ፣ የሌላውን ማህበረሰብ መብት የሚያከብርና ጥያቄዎችን የሚመለስ ማሻሻያዎችን አድርጋ፣ በጊዜያዊነት አሁን ያልችዋ ኦሮሚያ መቀጥሏ ችግር አይኖረውም።