Wednesday, 30 August 2017 12:48

በ  ፋኑኤል ክንፉ

የክልሉ መንግስት ካቢኔ በ05/12/09 .ም ባካሄደው መደበኛ የካቢኔ ስብሰባ ባሳለፈው ውሳኔ በ2006 .ም የመሬት ኪራይ ውል ፈርመው የእፎይታ ጊዜያቸውን ያላጠናቀቁ ባለሀብቶች የተቋረጠባቸው የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰረዝ እና የመሬት ውል፣ ውላቸው እዲቀጥል ከክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት በቁጥር መ2/376/3/13 08/12/2009 .ም የተጻፈ ደብዳቤ ለኢንቨስትመንት ኤጀንሲው መድረሱ ታውቋል፡፡

የጋምቤላ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ም/ዳሬክተር ያንግዶግ ጋትሉዋክ ፓት ለባለሃብቶቹ በግል በፃፉት ደብዳቤ ላይ እንዳሰፈሩት፣ “በደረጃ አፈጻጸም (F) ያገኙ 269 ባለሀብቶች ላይ ከተወሰደው ውል ማቋረጥ እርምጃ ጋር ተያይዞ ከባለሀብቶች በተነሱ ቅሬታዎች ላይ የጋራ የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ ከፌዴራልና ከክልሉ መንግስታት በተደረሰው ስምምነት መሠረት በተቋቋመው የቅሬታ አቤቱታ አጣሪ ቡድን ቅሬታዎችን ተቀብሎ አጣርቶ ጉዳያቸው እንገደና ተጣርቶ እንዲቀርብ በተባለው መሠረት፣ የክልሉ መንግስት ካቢኔ በ05/12/09 ባካሄደው መደበኛ የካቢኔ ስብሰባ ባሳለፈው ውሳኔ በ2006 .ም የመሬት ኪራይ ውል ፈርመው የእፎይታ ጊዜያቸውን ያላጠናቀቁ ባለሀብቶች የተቋረጠው ውላቸው እንዲቀጥል እንዲደረግ ከክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት በቁጥር መ2/376/3/13 08/12/2009 .ም የተጻፈ ደብዳቤ ደርሶናል፡፡” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳሬክተሩ አያይዘውም፣ የመሬት ኪራይ ውል ፈርመው የእፎይታ ጊዜዛቸውን ያላጠናቁ ባለሃብቶች በአስቸኳይ ወደ ሥራ በመግባት የጀመሩትን የልማት ሥራ እንዲቀጥሉ መመሪያ አሳልፈዋል፡፡ በዚህ በተሰጠው የእፎይታ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ የማይገባ ባለሃብት ውሉን እንዳላከበረ እንደሚቆጠር በደብዳቢያቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

ባለሃብቶቹ መሬታቸው በተነጠቀ ጊዜ መከፈል ለነበረበት የመሬት ግብር ክፍያ ታሳቢ እንደሚደረግላቸው መጠየቃቸውን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በፊት ልማት ባንክ ለባለሃብቶቹ ለሥራማስኪጃ የተፈቀደው 200 ሚሊዮን ብር ባለመልቀቁ በግርና ኢንቨስትመንቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ማሕበሩ ለሰንደቅ ገልጻል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኛ በዚህ ጉዳይ ላይ ውሳኔ እንዲሰጧቸው ቀጥተኛ ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡

ስንደቅ