September 1, 2017

በጣና ላይ የተከስተውን እምቦጭ የተሰኘ አደገኛ አረም ማስወገድ የሚያስችለው ማሽኑ የተሰራው መልካም ስብዕና እና የሙያ ተሰጦ ባለቤት በሆነውና የባህርዳር ከተማ ነዋሪ በሆነው በኢንጅነር ሙላት ባስዝነው ፈንቴ ነው። ኢንጅነር ሙላት ከልጅነት ጀምሮ በቶርኒዩና ማሽነሪ ስራ ለረጅም አመታት እያገለገለ በዚሁ ስራው የተለያዩ ለህዝብ ትራንስፓርት እና ለዓሳ ማስገር አገልግሎት የሚውሉ ጀልባዎችን በራሱ ዲዛይን በማድረግ በመስራት ለገበያ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።

በኢንጅነር ሙላት ባስዝነው ፈንቴ የተሰራው እምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን – ባህር ዳር

ይህው ወጣት ለጣና ገዳማትና አድባራት ለሚኙ ምዕመናን ና መነኮሳት ግልጋሎት የሚውሉ ጀልባዎችን ሲያበረክት እንደነበር የሀይማኖት አባቶች ምስክር ናቸው። በድርጅቱ ስራ ውስጥም በከተማው ያሉ በርካ ወጣቶችሽየስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል።
ዛሬ ደግሞ ለህዝብና ለመንግስት እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን በጣና ና አባይ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያስችል ማሽን (በውሃ ላይ የሚሳፈፍ ማሽን) በመስራት ከባህር ዳር ዪንቨርስቲ ጋር ውል ፈጽሞ ስራውንም አጠናቆ አስረክቦል።

በኢንጅነር ሙላት ባስዝነው ፈንቴ የተሰራው እምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን – ባህር ዳር

ይህንን ማሽን ለመስራት ወደ አሜሪካ ና አውሮፖ ተዘዋውሮ ማሽንኑን ከሚያመርተው ድርጅት በራሱ ወጭ በቂ የሙያ ልምድ ቀስሙል በተግባርም በመተግበር በጥረቱ ውጤታማ ሆኖዋል።
ለአገራችን በማሽነሪ ግዥ ሊያስወጣ የሚችለውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረትና አባይና ጣናን ለመታደግ ማሽኑን በመስራት ከኢትዮጵያ ዓዕምሮዊ ንብረት ጽ/ቤት የእውቅና ሰርተፍኬት አግኝቷል ተብሏል።
የባህር ዳር ዪንቨርስቲ የኢንጂነሪንግ ፋካሊቲ ትኩረት በመስጠት ሙያዊ እገዛ አድርጎለታል።

 

በኢንጅነር ሙላት ባስዝነው ፈንቴ የተሰራው እምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን – ባህር ዳር
ሁላችንም የኢንጅነር ሙላት ባሳዝነውን የሙያ ስኬት እና መልካምነት ለአማራ ወጣቶችም ይሁን ለአገራችን ወጣቶች በማስተላለፍ፣በማሳወቅና በመደገፍ የእርሱን ፈለግ በመከተል ውጤታማ እንሁን።

ጣና እና አባይን በህዝቦች የተባበረ ክንድ ከአደጋ እናድናቸዋለን!!!

Manufactured by Mulat industrial Engineering Plc

ምንጭ፦ አማራ ፕሬስ

የአማራ ሕዝብ የጣና ሃይቅን የወረረውን የእምቦጭ አረም በማስወግድ ስራ ላይ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የአማራ ሕዝብ ጣና ሃይቅ ላይ የእምቦጭ አረም በማስወገድ ስራ ላይ