September 2, 2017

 

በዛሬው ጦማር የቀረቡት ማስረጃዎች ባለ አምስት ኮከቡ የኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት የሆነው የአቶ ገምሹ በየነና የአስር ኮንስትራክሽን ባለቤት የሆነው የአቶ የማነ አብርሃ ጉዳይ ነው። (አቶ ገምሹ በየነም የትልቅ ኮንስትራክሽን ባለቤት ናቸው።)
ኢትዮጵያ ፈርስት የተሰኘው አፍቃሬ ኢሕ ዴግ ድረገጽ ከፍርድቤት አካባቢ አገኘሁት ብሎ የለቀቀው ማስረጃ እንደሚያሳየው ሁለቱም ግለሰቦች ተራ የመንግስት ተቀጣሪ ሰራተኞች የነበሩ ሲሆን፤ ልክ ስራቸውን ለቀው ሲወጡ በአንድ ለሊት ሚልዮን ብሮች ያሏቸው ድርጅቶች ባለቤት መሆናቸውን ነው።
የአስር ኮንስትራክሽን ባለቤት የሆኑት አቶ የማነ አብርሃ
በአ/አበባ መንገዶች ባለስልጣን እስከ ሚያዝያ 1996 ዓም ድረስ ወርሃዊ ደሞዛቸው ብር 3,083 ብቻ ነበር።
ይህኚው ግለሰብ ሀምሌ 30/2000 ዓም ላይ ከአ/አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት ስራቸው ሲያቆሙ ወርሃዊ ደሞዛቸው ብር 3,946 ነበር።

ይህኝው ግለሰብ ግን ከአራት ወራት ቆይታ በሁዋላ በ 14 ሚልዮን ብር የግል ድርጅታቸውን መሰረቱ። ዛሬ ላይ የግለሰቡ ንብረት ከ 300 ሚልዮን ብር በላይ መሆኑ ይታወቃል።
የገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ድርጅትና ባለ አምስት ኮከቡ የኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ገምሹ በየነ
በኢትዮጵያ መንገዶች ኮንስትራክሽን መስሪያ ቤት ከሚያዚያ 2/1987 – መጋቢት 30/1988 በጉልበት ሰራተኛነት ወርሃዊ ደሞዝ 50.00 ብር ይከፈላቸው የነበሩ ናቸው። ይህኚ ግለሰብ መስሪያ ቤቱን በገዛ ፈቃዳቸው እ.አ.አ. መስከረም 1/1999 ሲለቁ የማሽን ኦፕሬተር በመሆን ወርሃዊ ደሞዛቸው 472.00 ብር ብቻ ነበር።
ግለሰቡ ስራ ካቆሙ ሶስት አመት ልዩነት ውስጥ በ 741,987.875.00 ብር የግላቸው ድርጅትን መመስረታቸውን ሰነዶች ያሳያሉ። በአሁኑ ወቅት የግለሰቡ ሀብት በቢልየኖች የሚገመት ነው።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Source: ኢትዮጵያ ፈርስት