September 3, 2017 –

 ቆንጅት ስጦታው

ግንቦት7 ስብሰባውን [ጉባኤውን] በኤርትራ አፋቤት በሚባለው ቦታ እንደሚያደርግ ታወቀ

አፍዓቤት የኢትዮጵያውያን የደም መሬት ነው፡፡ አፍዓቤት የኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበርና የባህር በሮችዋን ለማስጠበቅ የተሰማራው “ናደው ዕዝ” የተባለው ግዙፍ የኢትዮጵያ ሰራዊት በሻዕቢያ የተደመሰሰበት ቦታ እንደሆነ በርካታ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አሁንም ድረስ በቁጭት የሚያስታውሱት ነው፡፡ ሻዕቢያም ኤርትራን ከእናት ሃገርዋ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ባካሄደው ረጅም ትግል “የናደው እዝ” መደምሰስ ወሳኝ የውጊያ ምዕራፍ ነበር በሚል በየአመቱ በዳንኪራ የሚያከብረው በዓል መሆኑ ይታወቃል፡፡ አሁንም በርካታ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት የሚታሰሩት እዚሁ አፍዓቤት “ሻባይ” በተባለው መንደር ውስጥ ነው፡፡ የግንቦት 7 ህሊና ቢስ መሪዎች ለሃገራቸው አንድነት ሲሉ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች አጥንታቸውን በከሰከሰቡት በዚህ የደም መሬት ላይ ተቀምጠው ጉባኤ ለማካሄድ ሲወስኑ እውነትም ከሃዲዎች መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡

አፍአቤትየደም መሬቱ ጉባዔተኞች!!

በኢትዮጵያ ህዝቦች አርበኞች ግንባር “መቃብር” ላይ እንዲካሄድ የታሰበው የግንቦት 7ቱ ጉባኤ እ.ኤአ ከመስከረም 6/2017 (ጳጉሜ 1/2009) ..አ እስከ መስከረም 12/2017 (መስከረም 2/2010) የሚካሄድ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ሐሬና በረሃ ለማካሄድ ታስቦ የነበረው የጉባኤው ቦታ ወደ አፍዓቤት እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ ባለቀ ሰዓት የጉባኤው ቦታ እንዲቀየር የተደረገው መረጃው በተከታታይ መውጣት ከጀመረ በኋላ ወያኔ ሐሬናን በውጊያ አውሮላኖቹን ሊደበድብ ይችላል የሚል ስጋት በመፈጠሩና በሻዕቢያና በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ክህደት የተበሳጩት የአርበኞች ግንባር አባላትም ጉባኤውን ለማደናቀፍ እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ የሚለው ፍራቻ እያየለ በመሄዱ ነው፡፡

የግንቦት 7 ጉባኤ እንዲካሄድበት የተመረጠው አፍዓቤት የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሌለው በመሆኑ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎች የበላይ ሃላፊ እንደሆነ የሚነገርለት ብርጋዴር ጠአመ ወይም “መቀሌ” በሚል ስም የሚታወቀው የሻዕቢያ የደህንነት ባለስልጣን በዶ/ር ብርሃኑ ጥያቄ 220 ኪሎዋት አቅም ያለው ጄኔሬተር ወደ አፍዓበት እንዲላክ አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለጉባኤተኞቹ በርካታ ምግብ፣ መጠጥና ሲጋራ ወደ አፍዓቤት እየተጓጓዘ ነው፡፡

መቀሌ” የተባለው ይኸው የኤርትራ የደህንነት ባለስልጣን በቅርቡ የአርበኞች ግንባር መሪዎች ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር በፈጠሩት አለመግባባት ከመሬት በታች በተቆፈረ ጉድጓድ እንዲታሰሩ ትእዛዝ የሰጠ ሰው ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህን ጨምሮ ኤርትራ ውስጥ ደብዛቸው ጠፍተው የቀሩ በርካታ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎችን ያስገደለ መሆኑ ይታወቃል፡፡

አፍዓቤት የኢትዮጵያውያን የደም መሬት ነው፡፡ አፍዓቤት የኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበርና የባህር በሮችዋን ለማስጠበቅ የተሰማራው “ናደው ዕዝ” የተባለው ግዙፍ የኢትዮጵያ ሰራዊት በሻዕቢያ የተደመሰሰበት ቦታ እንደሆነ በርካታ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አሁንም ድረስ በቁጭት የሚያስታውሱት ነው፡፡ ሻዕቢያም ኤርትራን ከእናት ሃገርዋ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ባካሄደው ረጅም ትግል “የናደው እዝ” መደምሰስ ወሳኝ የውጊያ ምዕራፍ ነበር በሚል በየአመቱ በዳንኪራ የሚያከብረው በዓል መሆኑ ይታወቃል፡፡ አሁንም በርካታ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት የሚታሰሩት እዚሁ አፍዓቤት “ሻባይ” በተባለው መንደር ውስጥ ነው፡፡

የግንቦት 7 ህሊና ቢስ መሪዎች ለሃገራቸው አንድነት ሲሉ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች አጥንታቸውን በከሰከሰቡት በዚህ የደም መሬት ላይ ተቀምጠው ጉባኤ ለማካሄድ ሲወስኑ እውነትም ከሃዲዎች መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጥሪ የተላለፈላቸው ተጨማሪ የግንቦት 7 አመራር አባላት ቀጥለው የተዘረዘሩት ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል ቁጥራቸው አስር ከማይበልጡ አባላት በቀር አብዛኞዎቹ ወደ ኤርትራ ለመሄድ ፈቃደኛ ስለመሆናቸው ለድርጅቱ እስካሁን ሰዓት ድረስ ምንም አይነት ማረጋገጫ አልሰጡም፡፡ እነዚህ ኤርትራ ውስጥ ይቆያሉ የተባሉት የድርጅቱ አመራሮችና የተሰጣቸው የስራ ድርሻ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1.
/ር አዚዝ መሃመድ (ማይክ አብርሃ) በሶሻል ሚድያ የሚካሄደውን ፀረወያኔ ትግል እንዲመራና እንዲያስተባብር እንዲሁም ለሻዕቢያ ሙያዊ የሚዲያ ድጋፍ እንዲሰጥ፣

2.ሙሉነህ እዮኤል (አባዳሜ) ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ህጋዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተገናኘ ፀረወያኔ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያስተባብር፣

3.አበበ ቦጋለ (ካሌብ) ኤርትራ ውስጥ የሚገኙ የወያኔ ተቃዋሚዎችን እንዲያሰለጥንና ድጋፍ እንዲሰጥ፣

4.ነዓምን ዘለቀ (መንግስቱ) የአገር ውስጥ እምቢተኝነት ትግሉን እንዲመራና እንዲያስተባብር፣

5.ብዙነህ ፅጌ (ውቤ የአንዳርጋቸው ፅጌ ታናሽ ወንድም) ለጊዜው ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ኤርትራ ውስጥ እንዲቆይ ስላልተፈለገ ከጉባኤው በኋላ ወደ እንግሊዝ ይመለሳል የሚባል ወሬ አለ፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪ ሌሎችንም አሳምኖ ኤርትራ ወስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የማግባባት ጥረቱን የቀጠለ መሆኑ ቢታወቅም ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑ ታውቋል፡፡

http://www.mereja.com/amharic/544640