እየከፋፈሉ ለአገዛዝ ይመቻቸው ዘንድ አልፎ ተርፎም ታላቋ ትግራይን የመመስረት ቅዠት ህልማቸውን ለማሳካት እርስ በርሱ ወልዶ እና ከብዶ የኖረውን ማህበረሰብ ያልነበረ ታሪክ እየፈጠሩ ለመለያየት የሚደረገውን ወንጀል እንቃወማለን፡፡ በተቀነባበረ መንገድ ሲያሻቸው የህዝብን የመገናኛ መንገድ እየተጠቀሙ አልያም ሆድ-አደር ግለሰቦችን መልምለው ያልነበረ እና የሌለ ታሪክ እንዲጽፉ እና እንዲያሳትሙ እያደረጉ የረጅም ጊዜ ጥላቻቸውን በአማራ ህዝብ ላይ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የተለያዩ የብሔረሰብ ስብጥሮች ያሉትን ያህል በአማራ ክልልም ተከባብረውና ተስማማተው የሚኖሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡

 

ነገር ግን አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዚህ ክልል ኗሪ ህብረተሰብ ላይ ሆን ብሎ ትንንሽ ልዩነቶችን አጉልቶ እያወጣ አላስፈላጊ የሆነ ቁርሾ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ጎንደርን ለማልማት በተለያዩ ዞኖች መክፈል ይኖርብኛል ብሎ ሌላ ድራማ በጎንደር ማህበረሰብ ላይ ለመስራት የተነሳው ይህ አስተዳደር ምን ያህል አማራን ለማጥፋት ቆርጦ መነሳቱን የሚያሳይ ነው፡፡ በሌላ መንገድ ደሞ የዛሬ አመት ስንት ንጹሃን ወገኖች የተሰውለትን የቅማንት አማራ የመሆን ጉዳይ የራስን እድል በራስ መወሰን የሚል ጨዋ ታ ፈጥሮ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ቅማንት ትግሬ ነው የሚለው መፈክር እንዳልሰራለት የተገነዘበው ይህ ያንድ ቡድን ስርዓት አሁን በጓሮ በር ሌላ አጀንዳ ፈጥሮ ራሳችሁን ትችሉ ዘንድ ውሳኔው የናንተ ነው በማለት የራሱን ሰዎች አሰማርቶ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የአማራን ህዝብ አዳክሞ ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ ለሰከንድ እንኳ እንቅልፍ ወስዶት ያማያውቀው ይህ ፈጽሞ ጨካኝ የሆነ ያንድ አካባቢ ቡድን ስብስብ በጎንደር እና በጎጃም በኩል ከሱዳን ጋር የተጋሩትን የድንበር መሬት ቀምቶ ለማመን በሚቸግር መንገድ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ተሌቪዥን የክልል አንዱ ምድር ሱዳንን እንዲያዋስነው ተደርጎ የተሰራ ካርታ አሳይቶናል፡፡ ባለግርማሞገሱን የራስ ደጀን ተራራ በትግራይ ክልል እንደሚገኝ አድርጎ በተማሪዎች የመማሪያ መጻህፍ ላይ አስፍሮ ለረዥም ግዜ ሲያስተምር እንደነበር እና በቅርቡም ይሄን የመሰለ እጅግ ከባድ የተጠና ህዝብን የውሸት ታሪክ የማለማመድ ሴራ በይስሙላ ይቅርታ እንዲታለፍ ሆኖ አይተናል፡፡ በሌላ መንገድም በትግራይ ለሚማሩ ተማሪዎች ላሊበላን የትግራይ ክፍል እንደሆነ ተደርጎ እየተማሩት እንደሚገኙ በተለያዩ ምንጮች ተገልጿል፡፡

የጎጃም ዓለምአቀፍ ትብብር በጎንደር ላይ እየተሰራ ያለውን ዘርፈ-ብዙ የተቀነባበረ ህዝብን የመለያየት ስራ እና የመሬት ዝርፊያ ወንጀል በጽኑ ያወግዛል፡፡ ይህ በመላ አገራችን ህልውና ላይ የተደቀነ ሴራ ባስቸኳይ ሊቆም ይገባል። ይህ ችግር በተለያዩ ያገራችን ክፍሎች ቢታይም በአማራ ህዝብ ላይ ግን ገዝፎ ይስተዋላል። ህወሃት ገና ከማለዳው የአማራን መሬት ማለትም፡ ወልቃይትን፣ መተከልን፣ራያና አዘቦን እና ሌሎችንም በመሳሪያ ቀምቶ ወስዷል። ይህ አልበቃ ብሎት ቅምያውን አሁንም ቀጥሎበታል። እኛ ኢትዮጵያውያን ዝም በማለታችን እና ባንድነት ባለመቆማችን ጎንደር ላይ የሚታየውና ልዩ ልዩ መሰሪ አገር አውዳሚ ድርጊቶች ተፈጽመዋል። ዛሬ ጎንደር ላይ የምናየው ነገ በሌሎች ያገራችን ክፍሎች እንደሚከሰት ጥርጥር የለውም፡፡ ‘’ባልንጀራህ ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ’’ እንዲል፡ ማንኛውም ያገባኛል የሚል አካል ሁሉ ይሄን የተጠና ወንጀል እንዲቃወም እና ከጎንደር ህዝብ ጎን እንዲቆም ስንል እንጠይቃለን፡፡

የጎጃም ዓለምአቀፍ ትብብርም በማንኛውም አስፈላጊ እርዳታ ሁሉ ከጎንደር ህብረት ጎን መሆኑን እና ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለነው እነደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

አንድነት ሃይል ነው!!
ጎጃም ዓለምአቀፍ ትብብር