በዳንኤል ጎበዜ

የምርጫ ቦርድ ተወካዮች ትናንት አይከል ከተማ ገብተዉ ህዝቡን ሰብስበዉ ስለምርጫዉስለ ድንበር መከለል ሲያነጋግሩ ያገኙት መልስ በጣም አስደንጋጭ ነበር ። የህዝቡ ምላሽ እኛ ባለፈዉ ዓመት ሁላችንም ተሰባስበን የወሰነዉ ከእንግዲህ መከፋፈልም ሆነ ቅማትና አማራ ብሎ ማካለል ያቁም በሚል እንደጥንቱ አብሮ ለመኖር ተስማምተናል፤ ለመካለል አልተስማማነም የሚል ምላሽ ሽማግሌ የነበሩም መልስ ሰጡ። የምርጫ ተወካዮጭም ተደናገጡ።

የምርጫ ቦርድ ተወካዮች ደግሞ ህዝብ ወስኖ የፈረመበት ሰነድ አለን ብለዉ ሲያቀርቡ። ህዝቡም ሽማግሌወችም ስህተት ነዉ ይህ ፊርማ እንደጥንቱ አብሮ ለመኖር ላለመከፋፈል ዓምና የፈረም ነዉ ብለዉ በማጋለጥ ተሟገቱ። በዚህ ሁኔታ ሽማግሌወች የተረዱት ወያኔወች ገለባብጠዉ ህዝቡ ለማካለል እንደተስማማ አድርገዉ ማዘጋጀታቸዉን ነዉ፤ አዛዉንቱም ወጣቱም ተቆጡ ፤ የመጀመሪያዉ ስብሰባ ተፋረሰ፤ ነገም ስብሰባ አለ።

አሁን ሚስጦሩ ሲወጣ ዋናዉ የኮማድ ፖስት ሥራ ሁኖ የቀየዉ ይህን ማመቻቸት እንደነበር ገሃድ ሁኔል። የጎንደር ህዝብና የአካባቢተወካዮች ባገለለ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ይህን በቅማንት ስም ወደትግራይ የማካለል ሴራ በጣት ከሚቆጠሩ የቅማንት የአንቀጽ 39 አቀንቃኝ ቡድኖች ጋር ተመሳጥረዉ ፍጻሜ ለማድረስ የኮማንድ ፖስቱ ዋናተልኮ እንደነበር ታዉቋል።
የሚገርመዉ ነገር ሰፊዉ የማካለል እቅድ በጣና /ደንቢያና እና በሱዳን በኩል ያሉትን መሬቶች በሙሉ በሰነዱ አጠቃለዉ አስቀምጠዋል። የአክራሪ የቅማንት ምንነት ኮሚቴ ከትግራ እስከ ጋምቤላ የተሰመረዉን የታላቋ ትግራይ ካርታ እዉቅና እንደሰጡ ሚስጥር እየወጣ ነዉ። አሁን ለቅማት የተባለዉ ካርታ ይፋ ቢሆን ህዝቡን በሙሉ ጦርነት የሚከት ነዉ። ይህ በአስቸኳይ መቆም አለበት።
ሌላዉ በምርጫ ቦርድ ከአዲስ አበባ ተወክለዉ የመጡ ሰወች አብዛኛወች አማረኛ አይናገሩም። ምናልባትም በቢሻንጉልና ከጋምቤላ ወያኔ ከተቆጣጠራቸዉ ክልል አካባቢ እንደመጡ ምንጮች ይናገራሉ። ሌላዉ በቋራ አካባቢ ያለዉ ህዝብ የምርጫ ካርዱን አንቀበልም ብሏል። የሰጡት ምክንያት እኛ አማራም ቅማንትም ነን አንከፋፈልም ነዉ። አገራዊ ምርጫ በጌጊዜዉ ተጭበርብሮ መቶ (100%) አሸነፍን እያላችሁ እኛ የናንተን ካርድ ተቀብለን እጃችን በእጃችን አንቆርጥም በማለት አሻፈረን ብለዋል።

በተሌጺዥን የሚያወሩት 12 ቀበሌ ነዉ ነገር ግን ከፋይል የያዙት ጉድ ብዙ ነዉ። ጎንደር ላይ እሳት እየለኮሱ ነዉ። ። የጎንደር ህዝብ በአንድነት ቁሞ ይህን እሳት ማጥፋት አለበት።
ዉድ ኢትዮጵያዊያን!! ወያኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ከስልጣን ለማዉረድ በመላ አገሪቱ ተባብረን በአንድነት በመቃወም አንፈልግም በቃን ብለን አደባባይ በመዉጣት ወይም በቤት ቁጭታ እንግለጽ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ይችን በራሪ መልክት ወደ ኢትዮጵያ አድርሱልኝ