September 7, 2017 – ቆንጅት ስጦታው

ወያኔ ለትግራይ ህዝብ የጠቀመ እየመሰለው የወልቃይትን፤ የአፋርን፣ የወሎን፣ የጋምቤላን፣ ሌሎችንም መሬቶችንም ቀስበቀስ የተቀራመታቸውንም ይሁን ለሱዳን የሸጣቸውን እነዚህ ሁሉ ህዝቦች መሬታቸውን ለማስለመስ ሀይለኛ ፍልሚያ ያደርጋሉ እንጂ ዝምብሎ መሬቱን ተቀምቶ እጁን አጣምሮ የሚቀመጥ ህዝብ የለም።

ምናልባትም ወያኔ የትግራይን ህዝብ የማይወጣው ዘላለማዊ ጦርነት ውስጥ እንዳይከተው የሚል ስጋት አለኝ….

በዛሬው ቀን የትግራይና አማራ ክልሎች ወሰን ማካለል ተግባር መከናወኑ የሁለቱም ክልሎች ሚድያዎች እየነገሩን ነው። መካለሉ ጥሩ ነው፤ ለአስተዳደር ይጠቅማልና። ከአማራና ከትግራይ በኩል የሚነገረን ግልፅ መሆን አለበት። ሁለቱም በየፊናቸው የፃፉት እነሆ።

Amhara Mass Media Agency

“ሰበር ዜና

በአማራ ክልል እና ትግራይ ክልል መካከል ሳይፈታ የቆየው የወሰን ጉዳይ በህዝብ ተሳፎ እና በስምምነት በዛሬው እለት ተፈታ ፡፡

በአማራ ክልል ጠገዴ እና በትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ መካከል የነበረው ለረጅም ዓመታት ሳይፈታ የቆየ የወሰን ጉዳይ በዛሬው እለት በጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ ላይ የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በተገኙበት በተደረሰ ስምምነት ተፈቷል ፡፡

በዚህም መሰረት ለረጅም ዓመታት ሲያወዛግቡ የነበሩት በግጨው በረሀ የሚገኙት የማይምቧ ፣ ሰላንዴ እና የአየር ማረፊያ ሰፋፊ የእርሻና ኢንቨስትመንት ቦታዎች ወደ አማራ ክልል ጠገዴ ወረዳ ተከልለዋል፡፡ እንዲሁም በግጨው እና በጎቤ የሚገኙ የትግሬኛ ተናጋሪዎች ያሉባቸው ሁለት የመኖሪያ መንደሮች ደግሞ ወደ ትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ ተከልለዋል፡፡ ወደ ትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ በተካለሉት ሁለት የመኖሪያ መንደሮች ዙሪያ የሚገኙ ሳፋፊ የእርሻ እና የኢንቨስትመንት ቦታዎች በአማራ ከልል ውስጥ እንዲካለሉ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ለረጅም ጊዜያት ሲያወዛግቡ የነበሩት ሳፋፊ የእርሻ እና የኢንቨስትመንት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ወደ አማራ ክልል የጠገዴ ወረደ እዲካለሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ወደ አማራ ክልል በተከለሉ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች የሚያከናውኗቸው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ በአማራ ክልል ህግ የሚተደዳዳረሩ መሆኑ በስምምነተት ላይ ተደርሷል፡፡”

Tigrai Communication Bureau

“ሰበር ዜና