September 8, 2017 13:48
ባጭሩ ፀረ-ኢትዯጵያ የሆኑ ጠባብና አክራሪ የጎሣ ፖለቲካ ደዋሪዎች ብቻ ናቸው::

ኢትዮጵያ የአንድ ጎሣ ንብረት አይደለችም::ሁሉም ጎሣ ደምና አጥንቱን ገብሮ ያቆያት ህያው ሐገርም ናት::ኢትዯጵያዊነት በሃገሪቱ የሚገኙ ህዝቦች ልዩ መለያ ነው::


<<ኢትዯጵያዊነት ከሽፏል>>የሚሉን የቀን ቅዠተኞች ህዝቡ በጫንቃው ላይ በተጣለበት የቋንቋ ፌደራሊዝም በአጥር ተገድቧልና ይህን አጋጣሚ በመጠቀም <<የራስን ዕድል በራስ መወሠን>> የሚለውን የጎሣ ፖለቲካ መርህ እንተረጉማለንም ባዯች ናቸው:: እነዚህን ሃይሎች በሁለት ከፍሎ ማየቱ ይበጃል::

1. ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን በማንቋሸሽ ሲዋጋ የነበረው የቋንቋ ፌደራሊዝም መሃንዲሱ ህወሃት-ወያኔ ዋነኛው ተዋናይ ነው::ህወሃት በኢትዯጵያውያን ላይ የጫነውን የጎሣ የበላይነትና የአፓርታይድ ስርዐት ጊዜውን ጠብቆ ቢገረሰስ ትግራይን ገንጥሎ ለመሄድ ዝግጅቱን የጀመረው በረሃ ነው:: ካመቸው ኢትዮጵያን እየገዛ ለመቀጠልና እስከዚያ ድረስ የህዝቡን ሃብትና ንብረት በማጋዝና በመዝረፍ <<ለትግራይ ሪፑብሊክ>> ምስረታ መስራት ነው::ለዚህም እኩይ አላማው መሳካት የነደፈው እስትራቴጂ ኢትዮጵያውያንን በጎሣ ፖለቲካ ጠብጥቦና አስሮ እርስ በርሣቸው የጎሪጥ እንዲተያዩና እንዲፋጁ በማድረግ በአንድነት ተነስተው እንዳይፋለሙት ኢትዮጵያዊ አንድነታቸውን አዳክሞ መግዛት ይህ ካልተሳካም ትግራይን ገንጥሎ መሄድን አላማው አድርጎ ይንቀሳቀሳል::

2. ሁለተኛው ፀረ-ኢትዯጵያዊ ሃይል ኦነግ ነው::ይህ ድርጅት ከፈጣሪው ሻዕቢያና ምግዚቱ ህወሃት የወረሰውን የፖለቲካ ፕሮግራም ጨብጦ <<ኢትዯጵያ ቅኝ የገዛችውን የኦሮሞ ህዝብና መሬትን ነፃ አውጥቼ የራሴን መንግስት አቋቁማለሁ>>በማለት ከነዚሁ ፈጣሪዎቹ ላለፉት 46 በላይ ዓመቶች የነፃነት ፍርፋሪ አገኛለሁ በሚል ተከታዯቹን እየማገድ የሚኒሶታን አድባር እየተለማመነ ያለ ነው::የህወሃቶችም ድብቁ አሾክሻኪም ነው::በአክቲቪስት ስም ያድራጃቸው እንደ ጃዋር፣ፀጋዬ አራርሳና ግርማ ጉተማ የመሳሰሉት ዋነኛዎቹ የዚህ አስተሳሰብ አቀንቃኞች ናቸው::«ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም::ኢትዮጵያዊ ማንነት መኖር የለበትም»የሚለው የየለቱ ድንፋታቸው የፀረ-ኢትዮጵያዊነታቸው መገለጫ ከሆነ ሰነባብቷል። ኢትዮጵያውያንም ሆነ ኢትዮጵያዊነትም አሉ።

ለመሆኑ ኢትዯጵያዊነት ከሽፏል?

ኢትዯጵያዊነትን ዋልታ ማገር ሆነው ያቆሙት እነዚህ ጠባብና አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞችም አይደሉም።ኢትዯጵያዊነት የእልፍ አህላፍ ኢትዯጵያዊያን ረቂቅ መገለጫና የማንነታቸው መጠሪያ ነው።ጠባብና አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ስልጣንና የሚኒሊክ ቤተ-መንግስት ባማራቸው ጊዜ የሚንዱት የሚኒሶታ የቅዠት ዳንኪራ አይደለም።እነርሱ ከከሰረ ፖለቲካቸው ጋር በከሰሩ ጊዜ ሁሉ የሚከሽፍ የእንቧይ ካብ ወይም የምስጥ ጉድጓድ/ኩይሣ/ አይደለም።ኢትዯጵያዊነት በጋራ ባለቤትነት የተቀመረ ረቂቅ ተሻጋሪ ሃሳብና የሁሉም ኢትዯጵያዊ የጋራ ንብረት የሆነ ነው።በነዚህ ጠባብና አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች ውስጥ ኢትዮጵያዊነት የተካደው እ.ከ1971 የኦነግ ምስረታ ከዛሬ 46 ዓመት ጀምሮ ነው።ምንም እንኳ ሻዕቢያ ለፖለቲካዊ ግቡ፣ወያኔ ኢትዮጵያን ለመግዛት እንደ ጋማ ከብት የጫኑዋቸውን ቀቢፀ-ተስፋ አንግበው በጊዜ፣ሁኔታና ቦታ ላለመቀየር የወሰኑ ድፍኖችም ናቸው።

የኦነግና አምስተኛ ረድፍ አክቲቪስቶቹ ዋነኛ ተልኮም ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው።ከራሳቸው አንደበት የሚደመጠውም «ኢትዮጵያ ካልፈረሰች፤ ኦሮሚያ ነፃ አትሆንም»የሚለው የደንቆሮ ለቅሷቸው ነው።ሌላው «ኢትዮጵያዊነት ከሽፏል» የሚለው ቅዠታቸው ነው።ኢትዮጵያዊነት ሊከሽፍ የሚችለው ኢትዮጵያዊነታቸውን በካዱት ጠባቦችና በሚኒሶታ መታጎሪያቸው ውስጥ ብቻ ነው።ልብ ብንል ለምሳሌ ያህል እነርሱ ታጉረውበት የስደት መንግስት የሚያውጁበት አሜሪካ ውስጥ ያሉ አፍሪካ-አሜሪካዊ ጥቁሮች እንኳ የሚደርስባቸውን የዘር መድሎን በአሜሪካዊነታቸው ኮርተው ይፋለማሉ እንጂ አሜሪካዊ አይደለሁም አላሉም።ታሪካዊ በደል ተፈፅሞብናል ብለው የታሪክ እስረኛ በመሆን ከአሜሪካ ተገንጥለን የራሣችንን መንግስት እንመስርትም አላሉም።

የኦነግና አክቲቪስቶቹ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በሃይልና በግፍ ተጨፍልቀናል።በመሆኑም የኛ የ16ኛው ክፍለ ዘመን ድርጊቶችን አታንሱብን ይሉናል።ዘር አቀፍ የጎሣና የጅምላ ቅጣትም/kin & collective punishment/ ለማድረግ እንደተነሱ ከዚህ በፊት በበደኖ፣በአርባ ጉጉና በጉራ ፈርዳ ፍንጭ ሰጥተዋል።እነርሱ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በአካል ተገኝተው የሚያስቡትና የሚኖሩት የ19ኛው ክፍለ ዘመንን ነው።

የ1ኛው ዓለም ጦርነት የ16 ሚሊዮን ሠዎችን ህይወት ቀስፏል።ጎራ ለይተው በጦርነቱ ተሳትፈው የተፋለሙ አገሮች ውስጥ ጥቂቶቹን ብንወስድ ቡልጋሪያ፣ጀርመን፣ኦቶማን ኢምፓየር፣ኦስትሪያ-ሃንጋሪ ወ.ዘ.ተ.በአንድ ወገን እንግሊዝ፣ፈረንሣይ፣ራሺያ፣ፖርቱጋል ወ.ዘ.ተ.ነበሩ።የ2ኛው ዓለም ጦርነት ከ50-80 ሚሊዮን ሠዎችን በጦርነቱ ተጎድተዋል።ራሺያኖች፣አይሁዶች፣ቼኮች ወ.ዘ.ተ በግፍ ተጨፍጭፈዋል።የዚህ ጦርነት ጫሪ መንግስታት አባሎች ተወግደው ሃገሮቹ በፖሊቲካ፣በኢኮኖሚና በባህል ተሳስረው ዛሬ በጋራ ይኖራሉ።አይሑዶቹ ይሁን ቼክ-ሩሲያውያን ለሂትለር ስራ ጀርመናውያንን ተጠያቂ አያደርጉም።ጃፓኖቹም በሂሮሺማና ናጋሣኪ ላይ ለወረደባቸው አቶሚክ ቦንብና ለደረሰው እልቂት ሳቢያ ዛሬ ከአሜሪካኖች ጋር ሆድና ጀርባ አልሆኑም ያውም ምርጥ ሸሪክ እንጂ።አሜሪካኖቹም ለፔሩ ሃርበር እንደዚሁ።

ማጠቃለያ፦

ዛሬ በጉልህ የሚታይ አንድ እውነት ከፊታችን ተደቅኗል።ይህም የፖሊቲካዊ ሃይል አሠላለፍ ይመስለኛል።
በአንድ ጎኑ ኢትዮጵያን እንደ አንበጣ መንጋ ወሮ፤ኢትዮጵያዊያንን በቋንቋ የፌደራሊዝም ክልል ሸንሽኖ አፓርታዲያዊ የፖሊቲካ ስርዓትን መስርቶ ኢትዮጵያን በግፍ የሚገዛ የህወሃት ወራሪ ሃይል ነው።ይህ ስርዓት ከተፈጥሮው ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱም ከጣሊያን ባለሟሎቹ በተቀዳ ስልትና እቅድ የሚመራ ነው።ይህ ሃይል መገርሰስ የሚቻለው በኢትዮጵያዊያን የተቀነባበረና የተቀናጀ ትግል ብቻ ነው።ይህ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ትግል ያጋጠመው እንቅፋት የህወሃት ህዝባዊ ድጋፍ መሠረት ሣይሆን፤ ኦነግ በፀረ-ኢትዮጵያዊነት መሰለፉና በተዘዋዋሪ ለህወሃት ጥንካሬና የእድሜ ማራዘሚያ ኪኒን ሆኖ መገኘቱ ነው።

ኦነግና ህወሃት በጋራ የሚያመሳስላቸው ሁለቱም ፀረ-ኢትዮጵያ መሆናቸው ነው። የሚከተሉትን በቅጡ ማጤን ይበጃል።

1.ኦነግ የኦሮምኛ ተናጋሪ ጠባብና አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች ጥርቅም እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ማለት አይደለም።የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምንና የኢትዮጵያም የጋራ ባለድርሻ ነው።ከኦሮሞ ህዝብ ከ60-65% በላይ የሚሆነው ከሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ጋር የተደባለቀ ነው።ኦነግ የኦሮሞን ህዝብ ከወገኖቹ ኢትዮጵያውያን ለመለየት የኦሮሞን ህዝብ ይሁንታ/mandate/ ያላገኘ በበታችነት ስሜት በተወጠሩ ግለሰቦች የሚመራ ድርጅት ነው።

2. አክራሪ ብሄረተኝነት ለህብረ-ብሄራዊነት ጠንቅ ነው።ኦነግና ህወሃት ለጋራ አላማ የሚሰሩ ፀረ-ኢትዮጵያ ሃይሎች ናቸው።በሁለቱ መካከል የታክቲክ እንጂ የስትራቴጂ ልዩነት የለም።

3. ህወሃት ያለ ኦነግ፤ኦነግም ያለ ሀወሃት አይኖሩም።አልኖሩምም።አንዱ ያለሌላው ስለማይኖርና ኢትዮጵያን በማፍረስ ተግባር የተሰማሩ በመሆኑ ሁለቱንም በጋራ ታግሎ መጣል የወቅቱ ጥያቄ ነው።አንዱን ከሌላው በቀዶ ጥገና ዘዴ ለይቶ «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ»በሚል የፖለቲካ ቧልት መጃጃል ክስረት ብቻ ነው።

ህወሃት ኦነግ፤ ኦነግም ሀወሃት ነው።ኢትዮጵያን ማዳን የምንችለው እነዚህን የኢትዮጵያ ጣምራ ጠላቶች በጋራ ስንታገል ብቻ ነው።ጊዜው የሚጠይቀው ኢትዮጵያዊ ሃይሎች የማይሰራና ወቅቱ ያራከሰውን ፖለቲካዊ ስሌት በመተው በጋራ ተነስተው እነዚህን ጠላቶች በጋራ ተፋልመው የጋራ ሃገራቸው ኢትዮጵያን መታደጉ ነው። በሃገር አቀፍ ስሌት የተዋቀሩም ድርጅቶች አቁዋማቸውን ገምግመው ለህዝቡ የማሣወቂያ ጊዜ አሁን ብቻ ነው። በመንታ መንገድ ላይ የምትገኘውን አገራችንን የምንታደግበትና ለአንድነቷ በጋራ የምንቆምበት ብቸኛው ወቅትም አሁን ነው።

«ህወሃት ኦነግ፤ኦነግም ሀወሃት ነው።ህወሃት ያለ ኦነግ፤ ኦነግም ያለ ሀወሃት አይኖሩም።አልኖሩምም።በጋራ እንፋለማቸው!!»