September 13, 2017 18:09


ፋሽስቱ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባርና ተላላኪው ብአዴን በአዲሱ አመት ዋዜማ ለመላው የጎንደር ህዝብ የሰጡት ስጦታ ቢኖር ሰላምና አንድነትን ሳይሆን አካሉ የሆነውን የጠገዴን ማህበረሰብ ለሁለት እንደ ቅርጫ መቀራምትን ነው።
ታላቋን ኢትዮጵያ የማፍረስና ህዝቧን የማተራመስ ተልዕኮ እንደ ቀደምት ባንዳ አባቶቹ ከጠላቶቻችን የተሰጠው የትግራዩ ወራሪ ቡድን የአማራን ህዝብና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቀዳሚ ኢላማው አድርጎ በውድ ሃገራችንና በኩሩው ህዝባችን ላይ መርዙን መዝራት ከጀመረ እነሆ 26 የፅልመት አመታት ተቆጠሩ።
ከሽፍትነት ዘመኑ ጀምሮ ታሪካዊና ለም የሆኑትን የጎንደር መሬቶች በተቀዳሚነት ኢላማው ያደረገው ወራሪው ወያኔ የተከዜን ወንዝ በመሻገር የወልቃይትን መሬት ከረገጠበት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በወገናችን ላይ ያደርስ የነበረው ዝርፊያ፣ እስራት፣ ድብደባና፣ ግድያ እስከ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ሲሆን በተለይም ከአንድ አመት በፊት የወልቃይትን ህዝብ ሙሉ ውክልና ይዘውና የህዝብን ጥያቄ አነግበው በሰላማዊ መንገድ ፍትህን የጠየቁ የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ መሪዎችና አባላት በሽብርተኝነት ተወንጅለው በዋና ዋና የህወሃት የማሰቃያ ካምፖች ውስጥ መከራን እየተቀበሉ የሚገኙ ሲሆን፤
ወረራውንና መስፋፋቱን በፍፁም ጭካኔና ማንአለብኝነት የቀጠለው ይህ እኩይ ቡድን ወደ ጠገዴና ጠለምት ያደረገውን ወረራ የተቃወሙትን ታሪክ ነጋሪ የሃገር ሽማግሌዎችን፣ ትውልድና ሃገር ጠባቂ ጎልማሳዎችን፣ እንዲሁም ሃገርና ታሪክ ተረካቢ የሆነውን ወጣት ትውልድ በግልፅና በስውር በመጨፍጨፍ ካጠፋ በኋላ ዕርስታችንን በሃይል ወደ ትግራይ በመጠቅለል በይፋ የምትገነጠለው ትግራይ አካል ከተደረገ እነሆ ሃያ ስድስት የሰቆቃ አመታት አሳለፍን።
ምንም እንኳ ህዝባችን በፋሽስቱ ህወሃት የጭቆና አገዛዝ ስር ሆኖ ቃላት ሊገልፁት በማይቻላቸው መከራና ስቃይ ውስጥ ቢገኝም ጭቆናንና ባርነትን አሜን ብሎ መቀበል ከአባቶቹ አልወረሰምና በሚቻለውና ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ ተጠቅሞ የጠላቱን እኩይ ሴራ በማክሸፍ ላይ ይገኛል። ይሁንና ይህ ህዝባዊ ተጋድሎ እረፍት የነሳውና ኢትዮጵያን የማፈራረስና ትግራይን የመገንጠል ሰይጣናዊ ተልዕኮ እያኮላሸበት የሚገኘውን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ለማዳከምና ከፋፍሎ ለማጥቃት በማለም አንድን ቤተሰብ የሆነውን የጠገዴ ማህበረሰብ ለሁለት በመክፈል ግማሹን ጠገዴ ሌላኛውን ግማሽ ፀገዴ በማለት ለያይተው የሚቻላቸውን ክፉ ተግባር ሁሉ ሲፈፅሙብን ኖረዋል።
ይሁን እንጂ ምንግዜም ቢሆን ጀግና መውለድ የማታቆመው የጎንደር እናት ዛሬም እንደ ትላንቱ አንድ ጠገዴ!!! ብለው በተነሱ ልጆቿ አማካኝነት ህዝባዊ ትግሉን በማፋፋም የፋሽስቱን ጎራ እያንቀጠቀጡት ይገኛሉ። “ወላድ በድባብ ትሂድ” እንዲሉ በጠገዴ የቁርጥ ቀን ልጆች የማያወላዳ ጥያቄ የተሸበረውና የዘመናት ሴራው በዜሮ የተባዛበት የተገንጣዩ ጎራ ከጳጉሜ 1, 2009 ዓ.ም ጀምሮ አንዳች የአማራ ህዝብ ድጋፍ በሌለውና እርሱ ህወሃት በአምሳሉ ጠፍጥፎ ከሰራው ብአዴን ተብዬ የአሻንጉሊቶች ስብስብ ጋር በመሆን አንዱን የጠገዴ ቤተሰብና ዕርስቱን ለሁለት በመከፈል መቀራመታቸውን በየፊናቸው እያወጁ ይገኛሉ።
የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ጥያቄ ግልፅና አንድ ነው። ይሃውም ህዝቡ ጎንደሬ/አማራ፣ መሬቱ የጎንደር፣ ድንበራችን ተከዜ ነው! የሚል ነው። ከዚህ ታሪክና ማንነትን መሰረት ካደረገ ህዝባዊ ጥያቄ አንዳች ጎደሎና እንከን የታከለበት ሽርፍራፊ ምላሽ ህዝባችን እንደማይቀበል የአለፉትን ሃያ ስድስት የፅልመትና የጭቆና ዘመናትን በፅናት በማለፍ ዛሬ እንደ አዲስ አይነቱንም ሆነ ይዘቱን ቅንጣት ሳይቀር ዳግም በወጣቱ ትውልድ መነሳቱ አብይ ማረጋገጫ ነው።
ታዲያ ይህን ታሪካዊ እውነታ አንዴ “በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ” ኮሚቴ አማካኝነት፣ ሌላ ጊዜ “ጠገዴ አንድ ነው” በሚለው የጠገዴ ህዝብ ጥያቄ ሳይወድ በግዱ እንዲጋፈጠው የተደረገው ፍሽስቱና ተስፋፊው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር “የማይተማመን ጓደኛ በየወንዙ ይማማላል” እንዲሉ ለሃያ ስድስት አመታት በሃይል ከልሎ ሲበዘብዛቸው የኖሩትን የጠገዴ ወገኖችን በተለይም ዕርስታችን የሆኑትን የግጨውና የጎቤ ጎንደሬ/አማራ መንደሮችን ትግሬ ያደረገ የትግራይን ድንበር ከአማራ ጋር ተካልያለሁ በማለት ሎሌዎቹን ሰብስቦ ከበሮ እየደለቀና ሻምፓኝ እየተራጨ ይገኛል።
እኛ በመላው ዓለም የምንገኝ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ተወላጆች ዛሬም እንደትላንቱ በአንድነት ከህዝባችን ጐን በፅናት በመቆም የትግል አጋርነታችንና አንድነታችን እየገለፅን ከጳጉሜ 1, 2009 ዓ.ም ጀምሮ በህወሃትና በብአዴን መሪዎች አማካኝነት የታወጀው ጠገዴን ከሁለት በመክፈል በተለይም የጎንደር/አማራ ለምና ታሪካዊ የሆኑትን የግጨውና የጎቤ መንደሮችን ወደ ትግራይ መከለል ፍጹም ሰብአዊነት የጎደለውና አንድን ቤተሰብ ለሁለት የሚከፍልና የሚለያይ ጭራቃዊ ተግባር በመሆኑ የምንፀየፈው አጥብቀን የምናወግዘው መሆኑን እየገለፅን፤
ትላንት ከቀጣሪዎቹ በተሰጠው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ባንዳዊ ተልዕኮ አንዱ የሆነውን ኤርትራን የማስገንጠልና የህጋዊና ዓለም አቀፋዊ ድንበር ባለቤት የማድረግ ሴራና ድራማ በቅጡ መከወን ያልተቻለው ፍሽስቱ ሟች መለስ ዜናዊ  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊያስፈፅም አልጀርስ ላይ ከኤርትራ ጋር የተስማማበትንና በአንፃሩ ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ከጅምሩ አጥብቆ የተቃወመውን መሰሪ ውል ሲያፈርስ እንደ ዋነኛ ምክንያት ሲቀላምድ የነበረው “አንድ ቤተሰብ ለሁለት የሚከፍል” ፍርድና የድንበር ማካለል አልቀበልም በማለት ነበር።
ዛሬ የሙት መሪያቸው ራዕይ ወራሾች ነን በሚል በየመድረኩ ሲምሉና ህዝብን ሲያደነቁሩ የሚውሉ ውልደ ፋሽስቶች ህዝባችን በወኪሎቹ አማካኝነት “እኛ አንድ ቤተሰብ ነን!” “ጠገዴ አንድ ነው!” በሚል ያቀረበውን ህዝባዊ ጥያቄ ለአልጀርሱ በተባው የክህደት ምላስና ህሊናቸው “አንድ ቤተሰብ ለሁለት የሚከፍል ፍርድና የድንበር ማካለል አንቀበልም” ማለትን እረስተው ህዝባችንን ዛሬም ድረስ ዘመን መለወጫን እየጠበቁ ያስለቅሱታል። ዕርስታችንም ታላቋን ትግራይ ለመመስረት በሚል ቅዥት ወደ ትግራይ በማካለል ለሕዝባቸው የአዲስ አመት ስጦታነት ያውሉታል። በዚህም ህወሃት በትግራይ ሕዝብ ስም ከትውልድ ወደ ትውልድ የማይረሳ ታሪካዊ ስህተት እየፈፀመ እንደሆነና ይህ ግፍና ጭቆና የማይናቅ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ማሳሰብ እንወዳለን።
ይሁን እንጂ ዛሬም ህዝባችን በፍፁም ጨዋነት ያቀረበው ሰላማዊና ህጋዊ ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረት በተገንጣዮች የእብሪት እርምጃ አሁንም እንዲለያይ በግፍ የተፈረደበት ቤተሰባችን ዳግም አንድ ሆኖ በሃገሩ ላይ በነፃነትና በእኩልነት መኖር እስኪችልና ሰላሙና አንድነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ትግላችን ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ለፍሽስቱ ህወሃትና ለተንበርካኪው ብአዴን አመራሮች፣ አባላትና፣ ደጋፊዎች እያሳወቅን፤ በዚህም ምክንያት ለሚደርሱት ማንኛቸውም ሃገራዊና አካባቢያዊ ችግር ብቸኛ ተጠያቂው ፋሽስቱ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባርና ተላላኪው ብአዴን አመራር አካላት መሆናቸውን ከጥብቅ ማሳሰቢያ ጋር እንገልፃለን።

ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!
ተገንጣዩ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር የኢትዮጵያን ሕዝብ እርስ በእርሱ በማጋጨትና በማፈናቀል የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም እለት በእለት መቋጫ የሌላቸውን ወንጀሎች እየፈፀመ ይገኛል።
በቅርቡ ለዘመናት በሰላምና በመከባበር በጉርብትና የኖሩትን የሱማሌና የኦሮሞ ወገኖቻችን መካከል የተፈጠረው ደም አፋሳሽ ግጭት መነሻውና መድረሻው ህወሃትና በአምሳሉ ጠፍጥፎ የሰራቸው አሻንጉሊቶቹ ኦህዴዲና አብዴፓ ሲሆኑ ብቸኛም ተጠያቂዎቹ እነዚህ ዘራፊ የጥፋት ሃይሎች ናቸው። ስለሆነም መላው የኦሮሞና የሱማሌ ወገኖቻችን ከማንኝውም የእርስ በእርስ ግጭት እራስን በማግለል ሙሉ ሃይላችሁን የኢትዮጵያና የህዝቧ ጠላት፣ ፀረ-ሰላምና፣ ፀረ-አንድነት የሆነውን ፋሽስቱን የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባርና ኦህዴድና አብዴፓን የመሳሰሉ ተላላኪዎቹን ማስወገድ ላይ ታውሉት ዘንድ በጥብቅ እያሳስብን፤ መላው የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ማህበረሰብ ከጎናችሁ እንደሆነና ህመማችሁ ህመማችን መሆኑን ማረጋገጥ እንሻለን።
የኢትዮጵያ ህዝብ በሃገሩና በወገኑ ላይ ምን አይነት ግፍና በደል እየተፈፀመ እንዳለ ጠንቅቆ ያውቃል የሚል እምነት አለን። በተለይም ቀደም ሲል ጀምሮ በጉራፈርዳ፣ በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በኮንሶ፣ … ወዘተ ወገኖቻችን ላይ ለተፈፀመው የጀምላ ፍጅት የሴራው ባለቤትም ሆነ ፍጅቱን የፈፀመው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር መሆኑንና ተላላኪዎቹም በክልል መንግስታት ስም ያስቀመጣቸው አሻንጉሊቶቹ መሆናቸውን ለህዝባችን ማስታወስ እንወዳለን። ትላንት አዲስ አበባ በተለምዶ ቆሸ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው የምንዱባን መኖሪያ ለደረሰው እልቂትና የእሬቻን አመታዊ በዓል ለማክበር ቢሾፍቱ በታደሙ ንፁሃን ወገኖቻችን ላይ ፍሽስታዊ ጭፍጨፋ ያካሄደው የትግራዩ ነፃ አውጭ ቡድን፤ እነሆ ዛሬም በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በጎንደር ህዝብ ላይ ቅማንት እና አማራ በሚል ከፋፍሎ ተመሳሳይ እልቂት ለመፈፀም አሰፍስፎ ይገኛል። ስለሆነም ይህን እኩይ ሴራ ለማክሸፍና ህወሃትን ለአንዴና ለመጨርሻ ጊዜ ወደ ማይቀርለት ዘላለማዊ የውርደት ሞት ለመሸኘት እያደረግን ላለነው ትግል ድጋፋችሁን በመስጠት ከህዝባችን ጎን እንድትሆኑ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ጀግናው የጎንደር ህዝብ ሆይ!
በተመሳሳይ ሁኔታ የህወሃት ፋሽስታዊ ስርዓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከተሸከመው ተልዕኮና ህልም ዋነኛና ተቀዳሚ የሆነው ታሪካዊቷን ጎንደር ማዳከምና ማፈራረስ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰነበተ። ይህን እኩይ ሴራ አስቀድሞ የተረዳው ጀግናው የጎንደር ሕዝብ ባደረጋቸው ያላሰለሰ ሰላማዊ ጥረቶችና ተጋድሎዎች የህወሃት ህልም ጉምን እንደመዝገን ያህል እንዲቆጠር እያደረገ ይገኛል። ከዚህም መካከል በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ መሪዎች በሰጡት የላቀ የአመራር ብቃትና መላው የጎንደርና የጎጃም ህዝብ ከ ሃምሌ 5, 2008 ዓ.ም ጀምሮ በከፈለው ታላቅ መስዋዕትነት አማካኝነት የወልቃይትን የጎንደር ታሪካዊ መሬትነትና ሕዝቡም ጎንደሬ/አማራ የመሆኑን እውነታ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለታሪክ ዳግም አረጋግጦ አልፏል።
ይሁን እንጂ  ጎንደር ላይ በኢትዮጵያዊነት መንፈስና በአባቶቻችን የጀግንነት ወኔ አይቀጡ ቅጣት የተቀጣው ፋሽስቱ ህወሃት የጎንደርን ሕዝብ አማራና ቅማንት በሚል ለመከፋፈልና እርስ በርሱ ዳግም ለማጋጨት በከፍተኛ ሁኔታ እያሴረ ይገኛል። በተለይም በቀርቡ ጎንደርን በሶስት ዞኖች በመክፈል አስተዳድራለሁ ያለ ሲሆን፤ በተጓዳኝም ለቅማንት ህዝብ “እራስን በእራስ የማስተዳደር” ስልጣን እሰጣለሁ በሚል የ“ህዝበ ውሳኔ” ምርጫ ለማድረግ ከበሮ እየደለቀ ይገኛል። በዚህ ምርጫ ተብዬ ድራም ውስጥ መራጩ፣ አስመራጩ፣ ታዛቢው፣ ቆጣሪው፣ እንዲሁም ውጤት ነጋሪውና አስፈፃሚው ህወሃትና ህወሃት ብቻ መሆኑን ከወዲሁ ማወቅና መረዳት ያሻል።
ህወሃት ዛሬም እንደ ትላንቱ ከጎንደር ህዝብ ጋር የገባበት ጦርነት ዳግም በህዝባዊ ቁጣ አይቀጡ ቅጣት የሚቀጣበትና በአጠቃላይ ከጎንደር ተዋርዶ የሚወጣበትን ጉድጓድ እየቆፈረ እንደሆነ አበክረን መግለፅ እንወዳለን።  ልክ እንደ ዛሬው ከ 70 ዓመታት በፊት የጎንደር ህዝብ አማራና ቅማንት በሚል ለመከፋፈል የሞከረው የጣሊያን ፋሽስታዊ ወራሪ ሃይል ነበር። በወቅቱም ፋሽስት ጣሊያን የገጠመውን ህዝባዊ ቁጣና ታሪካዊ ኪሳራ የሚያስታውስ ማንኛውም ሃይል በዚህ እጅግ አደገኛና ጎንደርን ዳር-እስከዳር በሚያቆጣ ካርድ እንደማይጫወት የምናውቅ ቢሆንም ህወሃት ግን ፍፃሜውን ለማፋጠን የቆረጠ በሚመስል ሁኔታ በጉዳዩ ላይ እየገፋበት ይገኛል። የዚህ እኩይ ተግባር ግንባር ቀደም አስፈፃሚ በመሆን በአማራ ስም ከፊት የተሰለፈው ትላንት ጠገዴን መሬት በእልልታና በፌሽታ ለህወሃት ያስረከቡት የብአዴን መሪዎች የመሆናቸው ጉዳይ የታቀደው “ህዝበ ውሳኔ” ጎንደርን የማፈራረስ ዋነኛ አካል ስለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ይሰጣል።
ስለሆነም በጎንደር ህዝብ መካከል ቅማንትና አማራ በሚል ለመከፋፈል በጎንደር ከተማ ዙሪያ፣ በጭልጋና፣ በመተማ አካባቢ በሚገኙ የተለያዩ አስራ ሁለት ቀበሌዎች ከመስከረም 7, 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሊደረግ የታቀደውን ሃሰተኛ “ህዝበ ውሳኔ” ከወዲሁ የምናወግዝ ሲሆን ሂደቱም በአስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን። ይልቁንም ማንኛው የጎንደር ህዝብ በዚህ የውሸት ምርጫ እንዳይሳተፍ በጥብቅ እያሳሰብን ህወሃት እርስ በእርሳችን ለማጋጨት ባሴረብን ወጥመድ ውስጥ ህዝባችን እጁን እንዳያስገባ አደራ እንላለን። የቅማንት ወገኖቻችንም ቢሆን ማንኛውንም የማንነትና የመብት ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ የሚያገኘው ከፍሽስቱ ህወሃት እጅ አለመሆኑን ተገንዝባችሁ ጥያቄዎቻችሁ ከዚህ ተስፋፊ ቡድን መወገድ በኋላ በፍትሃዊው ትግላችን በምንጎናፀፈው ህዝባዊ ስርዓት አማካኝንት የሚስተናገድ መሆኑን ከወዲሁ ተገንዝባችሁ ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ህዝባዊ ትግል ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ከጎንደር ህዝብ ትግል ጎን ትሰለፉ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።
በመጨረሻም በቅርቡ ይህን የቅማንታ/አማራ ጉዳይ አስመልክቶ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት (ጎሕ) እንዲሁም የወሎ አሊያንስ ድርጅት ያወጡትን የአቋም መግለጫ ሙሉ በሙሉ የምንደግፈው መሆኑን እየገለፅን፤ ጎንደር በማዳን ታላቋን ኢትዮጵያ ከጥፋት ለመታደግ በሚደረገው ህዝባዊ ትግል ውስጥ የድርሻችንን ለመወጣት ከምንግዜውም በላይ ዝግጁዎች መሆናችንን እንገልፃለን።

ጠገዴ አንድ ቤተሰብ፣ ድንበሩም ተከዜ ነው!
ልሳነ ግፉዓንና የጠለምት አማራ ማንነት ጥምረት ኮሚቴ
መስከረም 1, 2010 ዓ.ም
ሰሜን አሜሪካ