ሙሉነህ ዮሐንስ

(አርብ መስከረም 5 2010) በቋራ መስመር ያለችው ሽንፋ ከተማ በዲሽቃና በከባድ መሳሪ እየተናወጠች ነው የሚባል መረጃ ደርሶናል። የወያኔ አጋዚ ሰራዊት በብዛት እየተጫነ ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መሆኑ ተገልጿል። የመረጃ ልውውጥ እንዳይኖር ወያኔ የስልክና የኔትወርክ አገልግሎቱን እየዘጋ ነው። መረጃውን ከቦታው ያደረሱን ሰወች ዝርዝሩን የማንገልፀው ዘዴ ተጠቅመው ነው። የከባድ መሳሪ ድምፅ አካባቢውን እያናወጠው መሆኑን ገልፀው ህዝቡ እራሱን ለመከላከል እየጣረ ነው የድረሱልን ጥሪ አስተላልፈዋል።

ማስገንዘቢያ፦ የኔትወርክ መዘጋት በማጋጠሙ ተጨማሪ የማጣራት ስራ መከወን ባንችልም ቅድመ መረጃውን ከማድረስ ሌላ አማራጭ የለንም። ከሰአታት በፊት ባቀረብነው ዘገባ ወያኔ ቅማንትን ሰበብ አድርጎ ለመስከረም 7 ምርጫ አደርጋለሁ ማለቱ በአካባቢው ውጥረት ማንገሱን ጠቅሰን ነበር።

________

ቀደም ያለው ዜና:

በቋራ ውስጥ ሽንፋ አካባቢ የተቆጣው ጎንደሬ ወያኔ በአማራው ላይ የሸረበው በደል አንገብግቦት በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ነው። ባለፈው አመት ህዝብ ሲያፋጁ የተነቃባቸውና ሸሽተው የነበሩ ትግሬወች አሁን ተመልሰው እየመጡ ቅማንት ነን ብለው ለመምረጥ መሞከራቸው በመታወቁ እንደገና ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። አማራው ነቅቶባቸው አሁን መግቢያ አጥተዋል። አካባቢው ውጥረት ነግሶበታል።

ይህን የተረዳው ወያኔ እንደ አለፈው አመት የመተማ መስመር ይዘጋብኛል ብሎ ስለ ሰጋ በመቶወች የሚቆጠሩ የጭነት መኪናወች ምንነቱ ያልታወቀ እቃ በገፍ ከሱዳን እያስገቡ ወደ ትግራይ እያጋዙ ነው። የታርጋ ቁጥሩ ትግራይ ካለ አደጋ ይደርስብናል ብለው ስለፈሩ ከፎቶው እንደሚታየው አ.አ. በሚል ቀይረዋቸዋል።

በተፃራሪ ደግሞ መሬቱን እየተቀማ ለሱዳን የተሰጠበት የአማራ ወጣት ከፎቶው ላይ እንደሚታየው ጊዜያዊ ስራ ፍለጋ ሱዳን ጋላባት እየተሰደደ በእልህና በቁጭት ኮሽታ እስኪነሳ ሁኔታውን እየጠበቀ መሆኑ ከቦታው ዘገባውን ያደረሱን አብራርተውታል።

የጎንደርን ህዝብ የተባበረ ፀረ ወያኔ ትግል ለማክሸፍ አማራና ቅማንት ብለው በ12 ቀበሌ የወጠኑት ምርጫ ተብየ በአራቱ ቀበሌ እኛ አንከፋፈልም አማራ ነን ምርጫ አንፈልግም በማለቱ አስቀድሞ ሙሉ ለሙሉ በህዝቡ ውድቅ ተደርጓል። የወያኔ ሚዲያም በግድ በነዚህ ቀበሌወች ምርጫው “ተስተጓጉሏል” ብለው ዘግበዋል። በተቀሩት ቀበሌወችም ህዝቡ በነቂስ አንከፋፈልም የጋራ ጠላታችን ወያኔ ነው እያለ ነው።