September 15, 2017 – ቆንጅት ስጦታው

ወደ 61 ቀበሌዎች ህዝብ ሳይወስን የቅማንት ዞን እንደሆኑ እየተነገረ ነው  (ግርማ ካሳ)

ብዙ ወገኖች ያላወቁት ሕዝብ ሳይወስን እና ሳየመርጥ ወደ ስድሳ አንድ ቀበሌዎች ከወዲሁ በሕወሃት ዉሳኔ የቅማንት ልዩ አስተዳደር ውስጥ እንዲሆኑ ተወስኗል።፡

መስከረም 7 ይደረጋል የተባለው ምርጫ፣ ከስድሳት አንድ ቀበሌዎች በተጨማሪ ነው እንግዲህ በ12 ቀበሌዎች የሚደረገው። ምርጫውን የሚያደርገው ምርጫ ቦርድ ሲሆን የቦርዱን ድህረ ገጽ ስመለከት ምንም አይነት መረጃ የለበትም። የአማራው ክልል የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ድህረገ ገጾች ጋር ስሄድ፣ እዚያም በቂ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

ምርጫ እንዲደረግባቸው የተወሰኑት አሥራ 12 ቀበሌዎች አንደኛ በጣም ለምለም አካባቢዎች ስለሆኑ ነው ከጭልጋ፣ ከአማርጭሆና ከመተማ ወደ ቅማንት ልዩ አስተዳደር ለመዉሰድ ተብሎ እንደሆነ አስተያየት የሚሰጡ አሉ።

በአሥራ ሁለት ቀበሌዎች ምርጫ እንደሚደረግ በይፋ ቢነገረም፣ ከአሥራ ሁለቱ ቀበሌዎች ጭልቃግ ዉስጥ በሚገኙ በአራቱ ቀበሌዎ ምርጫ እንደማይደረግ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ፣ምክንያቱን በግልጽ ሳያስቀምጡ አሳውቀዋል። በነዚህ ቀበሌዎች የሚመዘገብ በመጥፋቱ እንደሆነ ከአካባቢው የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በስምንቱ ቀበሌዎች ከተመዘገቡት መካከል አብዛኞቹ አማራ ነን የሚሉ ሲሆኑ ራሳቸውን ቅማንት ነን የሚሉ ቁጥራቸው በጣም ትንሽ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። በአንድ የምርጫ ጣቢያ ላይ 600 አማሮች ፣ 18 ቅማንቶች ፣ 30 ትግሬዎች 170 ጉምዞች የተመዘገቡበት ሁኔታ ነው ያለው። ሽንፋ በተባለው አካባቢ፣ በአጠቃላይ 5 ቀጠናዎች ያሉ ሲሆን፣ በቀጠና አንድ የተነዘገቡት አማራዎች 2246 ሲደርሱ ቅማንቶች 8፣ በቀጠና 02 ደግሞ አማራዎች 1865 ሲደርሱ ቅማንቶች 12 ብቻ ናቸው።

ምርጫ በሚደረግባቸው ሌሎች ቀጠናዎችና ቀበሌዎች ተመሳሳይ ሁኔታ ስለሆነ ያለው፣ ምርጫውን ለማጭበርበር ከሌሎች ቀበሌዎች ሰዎችን ለማስመዝግ የተሞከረበትም ሁኔታ አለ። ለምሳሌ የቅማንት ነው ምርጫ አይደረግበትም ከተባለው ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ፣ ወደሽንፋ አሥገብተው ካርድ ለማስወጣት ሢሞከር በአማራ ተአዛቢዎች 147 ተይዘው እንደተመለሱ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ጎንደር ያሉ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

የሕወሃት ምርጫ ቦርድ ድምጽ ይሰርቃል ተብሎ የሚጠበቅ ይጠበቃል። በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ፣ መተማ፣ አለፋ ውጥረቱ ነግሷል፡፡ መተማ ፣ ገንድውሃ ፣ ኮኪት ያለው ህዝብ አስመራጮችን ከቦታው አባሯል፡፡ በመተማ እና በሽንፋ መሀከል በሚገኘው ጉባይ ጀጀህኝ በተባለው አከባቢ ከቅማንትና ከትግራይ ተወላጆች የተወጣጡ 80 የሚሆኑ ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቁ ሃይሎች ሰፍረዋል። የከባድ መሳሪያ በመጠቀም በታሪክ የኢትዮጵያን ወሰን በሱዳን በኩል በመጠበቅ የሚታወቀውን የመተማ አካባቢ አርሶአደር ላይ ጦርነት እንደተከፈተና ሽንፋ ላይ የከባድ መሳሪያ ጩኽት ይሰማ እንደነበረም ተዘግቧል።

የቅማንት የማናንተ ጥያቄ በሕወሃት አስተባባሪነት የተጠነሰሰ ሲሆን፣ የዚህ ኮሚቴ ዋና ጽ/ቤት መቀሌ መሆኑ ይታወቃል። ህወሃት በአማራ ክልል የቅማንት የማንነት ጥያቄ እንዲከበር ይሄን ያህል ሲደክም፣ በክልሉ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ያነሱ ወገኖች ሽብርተኛ እያለ ማሰሩ አላማው የዜጎችን መብት ማክበር ሳይሆን ጎንደርን ማዳከምና በአማራው ክልል የሕዝብ ለሕዝብ እልቂት እንዲፈጠር ስለመሆኑ ግልጽ ማሳያ ነው።

ብዙ ወገኖች ሕዝቡ ጥንቃቄ እንዲወስድ፣ ታሪካዊ አንድነቱን እንዲያስብና ለሕወሃት ሰራሽ መከፋፈል በሩን እንዲዘጋ እያሳሰቡ ነው።