ዛሬ መስከረም 7 ቀን በጎንደር ስምንት ቀበሌዎች፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ ለመቀጠል ወይንም ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ሕዝብ ድምጽ ሳይሰጥበት ሌሎች ቀበሌዎች ያቅፋል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የቅማንት አስተዳደር ውስጥ ለመቀጠል ፣ ሕዝብ በብዝት ወጥቶ ድምጽ እየሰጠ ነው።

ሕዝበ ዉሳኔ እንዲሰጥ ታስቦ የየነበረው በ12 ቀበሌዎች የነበረ ሲሆን በአራቱ ቀበሌዎች ሕዝብ ቅማንት አማራ እያልን አንለያየም ብሎ ከወዲሁ በመወሰኑ ተመዝጋቢ አልነበረም።
በሽንፋ/መተማ የሚመርጡት 4 ቀበሌወች 14,500 አካባቢ ሰው ተመዝግቧል። በጎንደር ዙርያ ያሉ 3 ቀበሌወች 3200 የሚሆን በቋራ ደግሞ አንድ ቀበሌ ወደ 2200 ህዝብ ለምርጫ ተመዝግበዋል። በነዚህ 8 ቀበሌወች የተመዘገበው ወደ 20ሽህ ህዝብ 85% እስከ 90% የተመዘገበው አማራ መሆኑ ስለታወቀ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ግልጽ ነው። በርካታ ቅማንቶችም ቋንቋቸው አማርኛ እንደመሆኑና ለዘመናት ከአማራው ጋር በመዋለዳቸው “ቅማንቶችን ከአማራው ጋር ሊያጣሉን ነው፡” በጎንደር ዞን ለመቀጠል ፍልጎት ያላቸው ናቸው።
ሆኖም ግን ህዝብ ዉሳኔዉን የሚያስተዳደር የሕወሃት ምርጫ ቦርድ እንደመሆኑ፣ ምርጫ ቦርድም ሕዝብ ከሰጠው የተለየ ውጤት ሊያወጣ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ብዙዎች ይገመታሉ። የጎንደር ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በመምረጡ በመደናገጣቸው ሕወሃቶች እና እነርሱ ያሰማሯቸው ጥቂት የቅምናት ኮሚቴ አባላት ግርግር ለመፈጠር እየሞከሩ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ህዝብ ዉሳኔ የሚደረገው በ1 8 ቀበሌዎች ቢሆንም፣ ወደ አዲሱ ቅማንት አስተዳደር ያለ ህዝብ ዉሳኔ የተጠቃለሉ 61 ቀበሌዎችም ሕዝብ ዉሳኔ መደረግ እንዳለበት አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። 61 ቀበሌዎች ቅማንትኦች በብዛት የሚኖሩባቸው ናቸው በሚል ነው ያለ ህዝብ ዉሳኔ ቅማንት ኣስተዳደር ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉት። የክልሉ ምክር ቤት 42 ቀበሌዎች 21 ደግሞ የቀበሌዎች ምክር ባሏቸው ዉሳኔ ያል ህዝብ ድምጽ እንዲወሰን መደረጉም ተዘግቧል። የክልል፣ የቀበሌ ምክር ቤት ተባለ እንጂ፣ ከበስተጀርባ እጅ እየጠመዘዘ የወሰነው ሕወሃት መሆኑ ብዙ ምርምር አያስፈልገውም።
ሆኖም ግን በ61 ቀበሌዎች ህዝብ ድምጽ እንዲሰጥ አለመደረጉ በሕግና በዲሞክራሲያዊ አሰራር አንጻር የሚያስኬድ አይደለም።

አንደኛ – ቅማንቶች ስለመብዛታቸው ምንም አይነት ማረጋገጫ የለም። ፈረንጆች አቆጣጠር የ2007 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት እንደዉም ቅማንትን እንደ ብሄረሰብም አልቆጠረም። በ1994 የነበረዉን የሕዝብ ቆጠራ ውጤት ከግምት በማስገባት ከሆነ ደግሞ፣ ከ23 አመታት በፊት የተደረገን የሕዥብ ቆጠራ እንድ እመረጃ መውሰድ ትክክል አይደለም።

ሁለተኛ ቅማንቶችና አማራዎው በብዛት በሚኖርባቸው ባሏቸው 12 ቀበሌዎች የተመዘገበው የቅማንቶች ቁጥር ከ10 በመቶ የበለጠ አይደለም። በመሆኑም በ61 አንዱ ቀበሌዎች ቢያንስ ከ10 በመቶ በላይ አማራ ስለሚኖር ፣አማራና ቅማንት በብዛት የሚኖሩባቸው ተብለውም ለሕዝብ ዉሳኔ መቅረብ ነበረባቸው።

ሶስተኛ – ቅማንቶች በብዛት የሚኖሩባቸው የተባሉት እነዚህ ቀበሌዎች እንደተባለው እዉነት ነው ብለን ብንቀበለው እንኳን፣ ቅማንቶች ከሰሜን ጎንደር ዞን በመውጣቱ ዙሪያ የነርሱስ ፍላጎት መጠየቅ አለነበረበትም ወይ ? ሕወሃት የመለመላቸውና የገዛቸው ጽ/ቤታቸውንም መቀሌ እያደረጉ ትቂት ግለሰቦች እንዴት ቅማንቶችን በሙሉ እንደወከሉ ተደረጎ ይወሰናል። ይሄ ቅማንቶችን ራሱ መናቅ ነው።፡በመሆኑም በ61 ቀበሌ የሚኖሩ ነዋሪዎች ድምጻቸውን መስጠት አለባቸው። ህዝብ መከበር አለበት።