ቅማንት ከጎደር አማራ ሕዝብ የተለየ አማራ ክልል ካለው፤ የአክስሙ ትግሬ ሕዝብ ከአጋሜ የተለየ ትግሬ ክልል ሊኖረው ይገባል።

የቀደመ ታሪክን ለግንዛቤ መጥቀስ የጽሑፍ መግቢያ መንደርደሪያ ከመሆኑም በላይ አዲሱ ታሪክ ከትየ ጀመረ ከየት ይደርሳል? የሚለውን ለመረዳት ለመገንዘብና ለማስተዋል፣ መመዘን ይረዳል። ከላይ የተጠቀሰውን ዕርስ በታሪክ ግንዛቤ መነሻነት ለማመሳከር፣ በትክክል ለማረቅ የታሪኩን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ፤ ወደኋላ ያለውን አስቀርተን  በአጭሩ ከአክሱማዊት  ዘመነ መንግሥት እንነሳለን፤ አክሱም ሥልጣኔ ከኢሩሳሌም ማዕከለ ምድር ጋር የተያያዘ የታሪክ ገጽታ እንዳለው በተደጋጋሚ የታሪክ ክስተት ተደጋግሞ የተነገረና የተዘገበ ጉዳይ ነው።

ቀደመ ታሪክ እንደሚያስረዳን በአክሱም መሬት ላይ የሰፈሩት ነገደ እስራኤላውያን አይሁዳዊ ሲሆኑ ይኸውም በውስጡ ያአገው ነገድን የሚያጠቃልል እንጅ ከአክሱም ውድቀት ቀጥሎ ቀስ በቀስ ከጊዜ ብዛት በዙ ዘመናት ከተቆጠረ በኋላ ቁጥራቸው እየጨመረ የሄደው ከበርሃው ወደ ነፋሻ ወይና ደጋ ቀመሱ እየተስፋፉ የሄዱትን አሁን በጠቅላላው ትግራይ ሆነው ትግርኛ የሚናገሩትን በታሪክ ምድረ አጋመ/ሜ ተብሎ የሚጠራውን አይወክልም።

በአጭሩ በአክሱም ስልጣኔ የነበሩ ቅሬተ አካላት መረጃዎች፣ የታሪክ አሻራዎች ብንመለከት አረማይክ፣ እብራይጥ፣ ግዕዝና አገውኛ ቋንቋን የሚናገሩትን ከአይሁድ ነገዶችን የአክሱም ቀዳሚ ባለመሬቶች መሆናቸውን በግልጽ የሚረጋግጥ የጽሑፍ፣ የሃይማኖት ማምለኪያዎች የባህል መገለጫዎችን የሚያንጸባርቁ እንጅ መነሻውን ወደ ቆላማው ወዳደርጉ ትግረኛ ተናጋሪዎች ወይም በቀደመ ታሪክ ምድረ አጋሜ/መ ተብለው ከሚጠሩት ምድማውያን የትውልድ ሐረግ ከሚመዘዙት ሰፋሪዎች ዘንድ ፍጽሞ አይዛመድም። ንግሥተ ሳባም ሆነ ዮዲት ጉዲት የአይሁዳውያን የገው ነገድ ተወላጆች እንጅ የምዳሜውያን ወይም ያጋሜያውያን ነገድ ውስጥ አይታቀፉም።

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ዋቢነትና እና እንደ ታላላቅ ጥናታዊ መዝገበ ቃላት ገለጻ አጋሜ/መ የሚለው ዘር ምዳሜ ከሚለው ከአብርሃም ልጅ ከያቆብ የዘር ሐረግ የሚቆጠር ሳይሆን፤ በእስማኤል በኩል የሚመዘዝ የዘር ሐረግ ያለው ነው። ምድዳማውያን በእስራኤል ታሪክ ውስጥ በንጉሥ ሰሎሞን ስልጣን ላይ ያመጹ የነበሩና ሳይሳካልቸው የቀረ በመጨረሻም ከፊሎቹ ወደ ደቡባዊ ኢስራኤል በየመን ጥግ አድርገው ወደ ኢትዩጵያ ቆላማ ክፍል ተሻግረው የሰፈሩ፣ ፍየልና ግመል በማርባት የሚተዳደሩ እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክና የመዝገበ ቃላት ትርጉም በሚገባ አብራርቶ ያስረዳል።

እርገጠኛ ሆኖ ለመናገር አክሱም በትውልደ ከምዳሜ የትወልድ ሐረግ ከሚሳበው በአጋሜ/መ ዛሬ ትግሬ ብለን በምንጠራቸው ተስፋፊዎች የቀናች አይደለችም። ከምዳማውያን ዘር የሚመዘዙት አጋሜ ቁጥራቸው እየበዛና እየሰፋ የሄደው ከአሥራ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን ገደማ ጀምሮ መሆን አዳልበት ይታመናል። አክሱም አክሱም ተብላ እራሷን ችላ የምታወቅ ግዛት እንጅ ትግራይ ተብላ የተመዘገበችበት ቅድመ ታሪክ የለም። አጋመም በአክሱ ምድር አልሰፈረም፤ አጋመውያን ቀደም ብለው በአክሱም ምድር ሰፍረው ቢሆን ኖሮ  ክጥንት ዘመን ጀመሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተደረገ የሰነ ታሪክ ቅሬተ አካል ምርምር የአጋሚያውያን ቋንቛ ጥንተ መሠረት የሆነው የዛሬው የትግረኛ ወይም የአጋሜዎች ወይም የምዳማውያን የዘር ሐረግ ያላቸው «ተጋሩዎች» ጽሑፍ በአስረጅነት ይገኝ ነበር። ነገር ግን አልተገኘም። በመሆኑም በምርምር ውጤቶች የሚከሰቱት ቅሬተ አካላት በመሉ የምዳማውያን /ከእስማኤላዊ ትውልድ የሚመዘዘው ወገን ሳይሆን  የአይሁዳዊ ኢስራኤላዊያን ቋንቋ የአረማይክ፣ የኢብራይስጥኛ፣ የግዕዝኛና የአገውኛ ቋንቋ ወጤትና የታሪክ  ቅሬተ አካላት ግኝቶች ብቻ ናቸው።

ይህንም ይበልጥ ለማጠናከር የአክሱም ዘመነ መንግሥት ፈርሶ ወደ ላስታ ሥረዎ መንግሥት ሲሸጋገር የቀደሞ ምድማውያን ወይም አጋመውያን ቋንቋ ዛሬ በጀምላ ትግረኛ ብለን የምንጠራው ወደ ላስታ ፍልሰት አላደረገም። ነገር ግን በአክሱም የነበረው የስራኤላውያን እና የአገው ቋንቋ ፍልሰት አድርጎ በላስታ ሥረዎ መንግሥት ምንም እኳን የግዕዙ ቋንቋ የመጠቀም ኃይል እየበረታ  ቢመጣም ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ተወራርሶ የመጣው አረማይኩ እና ኢብራይስጡ በላስታ ውስጥ እረጅም ጊዜ በጥምር ቋንቋነት ያገለገለ መሆኑ እንደ ርዕሰ አድባራት ተድባበ ማርያም እና በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ታላላቅ አድባራት የሚገኙ  የአረማይክ፣ የእብራይስጥ እና የግዕዝ ድርሳናት በማስረጃነት ያመለክታሉ። እነዚህም በቀጥታ ከአክሱም የታሪክ ቅሬተ አካላት ጋር ይዛመዳሉ።

ሆኖም በክሱም ሥርዎ መንግሥት መፍረስ ምክንያት ሁሉም ወደ ላስታ ሥረዎ መንግሥት የትዛመተ ቢሆንም በወቅቱ ቁጥራቸው አናሳ ሚሆኑ ኢስራኤላዊያንና የአገው የዘር ሐረግ ያላቸው አይሁዳዊያን  የመሬቱ ባለይዞታዎች ነባሮቹ በአክሱም ምድር ላይ ቆይታ አድርገው ከአክሱም ውድቀት በኋላ የቀደመው ተግባራቸው እንደተጠበቀ  በግብርና፣ በንግድና በዕደ ጥበባት ሥራ ሙያተኝነት ተሰማርተው እየኖሩ ቆይተዋል።

የእነዚህ የዘር ሐረግ ከበስተ ኋዋላ ቅዱስ ያሬድና እስከ ንጉሥ አርምሀ ድረሥ የተያያዘ ነው። ቅዱስ ያሬድ ኢስራኤላዊ እንጅ ከአጋመውያን ወይም  ከጥንት ምድማውያን ትውልድ የሚቆጠር አይደለም። ቅዱስ ያሬድ ይናገር የነበረውም ዛሬ አጋሜ ወይም የጥንት ምዳሜ የሚናገሩትን የአሁኑን ትግርኛ ይናገር የነበረ ሳይሆን፤ በቀጥታ ከአክሱም ሥረዎ መንግሥት ወደላስታ የተዛወረውን አረማይክ፣ እብራይስጥ ና ግዕዝን ብቻ ይናገር ነበር። ትምህርቱንም የተማረው በኢስራኤላውያን ስም ይጠራ ከነበረው ከአጎቱ ከጌዴዎን እንጅ በወቅቱ የአክሱምን ምድር ካልረገጡት ከአጋሜያውያን ከጥንት ምዳሚያውያን ከአሁኑ ትግርኛ ተናጋሪዎች ጋር ምንም ዓይነት ግኙኝነት አልነበረውም።

ከአክሱም ፍልሰት ከብዙ ዘመናት በኋላ በቆላማው ምድር ፍየልና ግመል የሚያረቡት አጋሜያውያን ከጥንት ስማቸው የምዳማዊ የዘር ሐረግ ያላቸው ትግረኛ ተናጋሪዎች ቁጥራቸው እየጨመረ ወደ ነፋሻው የአክሱም ምድር እየተስፋፉ ቢሔዱም፤ ቅድመው የአክሱም ምድር ባለቤት በነበሩት እረጅም ዘመናት የኖሩት አይሁዳዊ /ኢስራኤላዊያ/ እና  በአገው ትውልድ የተናቁ በመሆናቸው አክሱሞች ከአጋሜዎች ጋር ለመጋባት ቀርቶ ልጆቻቸው ከልጆቻው አይጫወቱም፤ ከብታቸው ከከብታቸው ተቀላቅለው አይውሉም ነበር።

ይህም ኢስራኤላዊ አክሱማውያንና አገዎችን ከንጉሡ የሰለሞን  አይሁዳዊ ዘር መሠረቱን ሲያደርግ፤ ምዳማውያን ደግሞ ከአገልጋይዋ ከአጋር ጋር በስማኤል በኩል የተመዘዘ  በደረጃው አናሳ የትውልድ ሐረግ ልዮነት አላቸው የሚል   አስተሳሰብ በጊዜው የነበረ ስለሆነ ነው።

ይህ ታሪክ እስካሁን ዘልቆ በአክሱማውያንና በአጋሜያውያን የጥንት ምዳማውያን መካከል መናናቅ አለ። አክሱማውያን የአጋሜ ዘር እያሉ ሲጠሩዋቸው፤ የጥንት ትውልደ ምዳማውያን ወይም አጋመ ደግሞ የክሱማዊ ኢስራኤላዊያንን አይሁዳዊ ጥበበኝነትና ሙያተኝነት መነሻ በማድረግ ጠንቋይ፣ ቡዳ ጠይብ እያሉ ይሰድቧቸዋል።

ከላይ እደተጠቀሰው ቅዱስ ያሬድም ወደፊት ወገኖቹ የአክሱም ኢስራኤላውያንና አገዎች አይሁዳዊያን ከአክሱም በኋላ መንግሥታቸውን ወደ ሚያጸኑበት አቢያተ ክርስቲያናት አንጸው ወደሚያመልኩበት ወደ ላስታና ወደ በጌምድር መካከለኛ ምድር ወደሆነው ዛሬ በጎንደር ክፍለ ሀገር ውስጥ ጋይንት ዙርአንባ ተብሎ ወደ ሚጠራው ተቀምጦ መጽሐፍትን ጻፈ ደቀመዛሙርትን አስተማረ በኃላም ወደ ጣና ገዳማት ገብቶ ቀረ እንጅ ወደፊት ከጥንት ከምዳምውያን ዘር ተሳስበው  እየተስፋፉ ዛሬ ቀድሞ አክሱም ከቀሩት ኢስራኤላዊያን ጋር ከተቀላቀሉት አጋመ ትግረኛ ተናጋሪዎች ወደ ሚበዙበት ምድር መቀመጫውን አድርጎ የሠራው አንድም ነገር አይታወቅም። እርግጥ ነው ከላይ እንደ ተጠቀሰው በልጅነቱ ትምህርቱን ጌዴዎን ከሚባል አክሱማዊ ኢስራኤላዊ አይሁድ መማሩ የታውቀ ነገር ነው።

አንዳንድ የታሪክ አዋቂዎች እንደሚያስረዱት አቡነ አረጋዊ ኢስራኤላዊ ከአይሁዳዊ እመነት ክርስትናን የተቀበሉ ሲሆኑ ክርስትናን አበክረው ሲሰብኩ ከምዳምውያን ዘር እየተሳሳቡ የመጡት አጋሜ/መ ቆለኞች ትምህርታቸውን አይቀበሉም አያምኑምም ነበር። እንዲያውም አቡነ አረጋዊን ሊገድሏቸው የፈልጓቸው ያሳድዷቸው ነበር። አቡነ አረጋዊ በነዚህ አጋሜዎች ወይም ምዳማውያን ተሰላችተው ፈጣሪያቸውን ሲያማርሩ እግዛብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ በዘንዶ ኃይል አጋሜዎች ሊወጡበት ሊደርሱበት ወደ ማይችይሉት ተራራ ደብረዳሞ እንደወረወራቸው እና ሰላማዊ የጸሎት የማማር የማስተማር ሃማኖታዊ ሕይዎታቸውን በተራራው ላይ  እንደገፉ ይተርካሉ። ታሪኩ ምን ያህል እውነት እንደሆነ በጽሑፍ ደረጃ የቀረበ በማስረጃ የተገኘ ስልመሆኑ የቀረበ ነገር ባይኖርም ታሪኩ ከእወነት የራቀ ነው  ብሎ ለመናገር ይከብዳል።

ቀናት እየተዋለዱ ወራት እየተቆጠሩ ዘመናት እየተራዘሙ በሄደ ቁጥር ከምዳማውያን ትውልድ ሐረግ የሚመዘዙት ፍየልና ግመል እያረቡ ይተዳደሩ የነበሩት ቆለኛ ወይም የምድረ አጋመ ሰዎች ትግረኛ ተናጋሪዎች ወደ ነፋሻው አክሱም እየተስፋፉ ሲመጡ  ወደ ላስታ ከተደረገው ሽግግር ውስጥ በአክሱም ምድር የቀሩት ኢስራኤላውያንና አገው እነሱን በመሸሽ ግማሾቹ ዛሬ ምድረ ሀሜሴን/ሀማሸን/ አስመራ ኤርትራ ተብሎ ወደ ሚጠራው አካባቢ ሲሻገሩ፤ ግማሾቹ ግን ከምዳምውያን የዘር ሐረግ መቀላቀል ግድ ሆኖባቸው ጥቂቶች በብዞዎች ተውጠው በአብዛኛው ወደ ላስታ ብሎም ወደ ጎንደር  የፈለሰው ኢብራይስጡ፣ግዕዙና ያአገው ቋንቋ በቆለኛው ያአጋሜ ቋንቋ እየተሸነፈ መጣ።

ልክ እንደ አክሱሞች ሁሉ በሃማሴን/በሐማሸን/ የአሁኑ አስመራ አካባቢ ኤርትራ የሰፈሩት ኢስራኤላውያንና አገው የዘር ሐረግ ያላቸው ለቆለኛ ሰፋሪዎች አጋመን ዝቅ አድርገው የማየት ባህሪያቸው አብሮ የቆየ ሲሆን እስካሁን ድረስ የዘለቀ ነገር ለመሆኑ ሁሉም በተጨባጭ ሊያረጋግጠው የሚችል ነው። ሐማሴናዊያን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለብዙ ዘመናት  ወንዶቹን ለጨው ሸክም ወደ ምጽዋ፤ ሴቶቹን ለቤት አገልጋይነት እየቀጠሩ ያሠሯቸው እንደነበረ ሁሉም የሚያውቀው የታሪክ ሃቅ ነው።

ተከዜና አቋርጠው ወደ ጎንደርም ሲመጡ ወንዶቹ ለጤፍ አጨዳ፣ ለጥጥ ለቀማና ለሰሊጥና ለማሽላ ቆረጣ ሴቶቹም እንዲሁ ቤት ውስጥ አገልጋይነት እየተቀጠሩ ይሠሩ ነበር። እንዲያውም ወደ ጎንደር  ከመግባታቸው በፊት የማመልከቻ ጩኸት የሚያሰሙበት ቦታ ነበር ፤ ይኸውም አጋመ ጋራ ወይም ትግሬ መጮክያ የሚባል ቦታ ነበር፤ አሁን ከጊዜው የበላይነት በተያያዘ  ይህን ስያሜ  መጥራት ወንጀል ስለሚሆን ቦታው በሌላ ስም ካልተቀየረ በስተቀር።

ይህ የተአሪክ ገጽታ አሁን በሰለጠነው ዘመን እነሱ እንደሚሉት በትምክተኝነት ለማየት ሳይሆ፤ ዛሬ ሰለጠኑ በምንላቸው እንግሊዞች እስኮትላዶችን በዚህ መልኩ ያሠሯቸው እንደነበረ ከዓለም የማኅበረሰብ ሕይዎት የበላይና የበታች  ታሪክ ውስጥ ተያይዞ በቀደመው ጊዜ የተገከናወነ ተግባር በመሆኑ  በሀግራችን የተከሰተ ለታሪክ ማስታዎሻነት ዋቢነት አጠናክሮ ከማቅረብ አንጻር እንደ ማስረጃ ሆኖ የቀረበ ነው።

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት አክሱም የቀናቸው በአማራዎች ነው ብለው ምስክርነታቸውን ሲሰጡ፤ አክሱም ዘመነ መንግሥት በኃላ ወደ ላስታና ወደ በጌምድር ለውጥ ያደረገውን ሥረዎ መንግሥት ኢስራኤላዊያን እና የአገው ማኅበረሰብ በኃላም ከቅማንቱ፣ ከቋረኛው ከጋፋቴው ከዋክሹሙ ከየጁ አሮሞ ተቀላቅሎ አማራ የሆነውን እስከ ጎንደር ዘመነ መንግሥት የነበረውን አሁንም ያለው አማራ የአክሱም የመሬቱ ባለ ዕርስት የአክሱም መንግሥት አቅኝና የሥልጣኔ ባለቤት መሆኑን ሲያረጋግጡ ነው፤ እንጅ አማራ የቢባለው ቋንቋ በዚያን ዘመን ብዙም የቀና አልነበረም።

ከአክሱም ወደ ላስታ የተሸጋገረው የኢስራኤላዊያና የአገው ሥረወ መንግሥት እስከ አስራ ሁለተኛው ክፍለዘመን አጋማሽ ቆይቶ፤ ቀደም ብሎ በስድስተኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ ቅዱስ ያሬድ በላስታና በበጌምድር ማዕከለኛ  የተቀመጠበትን የጋይንትን ምድር አጠቃሎ ወደ ጎንደር ዘመነ መንግሥት ተሸጋገረ። በጎደንር ጎጃም አጠቃሎ ከአክሱም ተነስተው በላስታ የኢራኤላዊያንና አገዎች ይናግሩት ከነበረው በተለይም ግዕዝና ኢብራይስጥ ተቀራራቢ የሆኑ አገውኛ፣ ቋረኛ ጋፋትኛ የሚናገሩ እንደዚሁ ቀድመው የሰፈሩበት በመሆኑ ከዚያን ወቅት ጀምሮ ብዙ የተማሩ ጠበብተና ሊቃውንት አይሁድና አገው የሰፈሩበት ምድር በጌምድር ወይም በሊቃውንት የሚተዳደር መሬት በኋላም ጎንደር /የአካል ማሳረፍያ፣ ማደርያ ደልዳላ ምቹ ታላቅ መሬት የሀገር ጎን/ በማለት ሰይመው መንግሥታቸውን አጸኑ ሃይማኖታቸውን ሰበኩ።

በዚህን ጊዜ የጎንደር መሬት እስከ ተከዜ ወንዝ ምላሽ ወንዙን ተከዜን ጨምሮ የጎንደር ነገሥታት ይዞታ ሲሆን፤ ከተከዜ  ወንዝ ማዶ ደግሞ ከምዳማውያን የዘር ሐረግ  የሚሳቡት ምድር ወይም ምድረ አጋሜ/መ ተብሎ እስከ ዛሬው መቀሌ ድረስ የሚታውቅ ሲሆን በዚህ በሰለጠነ ዘመን እንደ ወያኔ ወደኋላ ዘር ቆጥርን የመከፋፈል ምርኮኞችና የደካማ አስተሳሰብ ግዞተኞች ሆነን ብናስብ፤ ከላይ በአጭሩ ለመጥቀስ እንደሞከርነው ጥንት የታሪክ መሠረታዊ ገጽታ ስንነሳ አክሱም በፍጹም የመቀሌ ወይም የምደረ አጋመ አካል ሊሆን አይችልም ነበር። በጥንት ታሪክም በቋንቋም በባህልም በነገድም በስልጣኔም አክሱም እና ምድረ አጋመ ሁለቱ ፍጹም የተለያዩ ናቸው።

ከላይ እንደተጠቀሰው በጎንደር ዘመነ መንግሥት ውስጥ ጊዜ እየተራዘመ በመጣ ቁጥር የየጁ ኦሮሞች ሳይቀር ተቀላቅለው በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የገቡበትና ሀገር ያቀኑበት ሁኔታ በተጨባጭ ታሪክ የተዘገበ መሆኑ መደጋገሙ አስፈላጊ ባይሆንም፤ ከዚህ ሁሉን አቀፍ ሆኖ ከአምስት ምቶ ዓመታት በላይ ከሆነው የማዕከላዊ የመንግሥት መናገሻ ምድር ጎንደር በጌምደር፤  በቀድሞ የእርሻ ምሬት ይዞታ በሚነሳ የሰጥ አገባ ክርክር  የአያት የቅድሜያት የቅማንቴ በሚል የተለያዩ ወንድሞች ይጣሉ የሟገቱ ይከራከሩ ነበር። ቅማንት ማለት ትልቅ አባት የሚለውን ትርጉም ከመስጠት በስተቀር ሌላ እሳቤ የለውም።

ከዚያ አንጻር ቅማንት የሚል እንደ መገለጫ ስም ሆኖ የቆየ አሉታ አለ እንጅ ቅማንት ከነባሩ ከአክሱም እና ከላስታ በኋላም ወደ ጎንደር እየተሸጋገረ ከመጣው ከኢስራኤልና ከአገው ቀጥሎም ከየጁ ኦሮሞ፣ የጋፋተኛውና የቋረኛው፣ ከዋክሹሙ ጋር ተቀላቅሎ አማራ ከሆነው ሕዝብ ባህልና ቋንቋ የተለየ የዘር ሐረግ አይደለም። ሊሆንም አይችልም።

ቅማንትን ከጎንደር ከጎጃምና ከላስታ አማራ ለይቶ ማየት ከቶ የአንድ ኩንታል ሰርገኛ ጤፍን ጥቁሩን ከነጩ እና ከቀዩ ጤፍ ለይቶ የማውጣት ያክል እጅግ ከባድና እረቂቅ ነው። ቅማንት የሚለውም ስያሜ እንደ ጋፍቴውና ቋሬው ኢስራኤላዊዩና የአገው ነገድ እንዲሁም የየጁ ወረሴ ኦሮሞ ሁሉ ከጥንት ቋንቋው ከአራማይኩ፣ከኢብራይስጡ፣ ከአገው፣ከቋረኛው ከጋፋቴው ነጥሮ የወጣውን ጉረሮ የማይዘውን ተለሳልሶ፣ላልቶም፣ ጠብቆም በተፈለገ አቅጣጫ ሊነገር የሚችለውን ከሁሉም የተውጣጣ የነጠረ ቋንቋ አማርኛን የሚናገር  በአንድ አማራ ማኅበረስብ የሚጠራ በላስታ፣ በጎንደር በጎጃም ቀጥሎም ወደ ሸዋ መሬት ላይ ባለመሬት ሆኖ የሚኖር  አማራ እንጅ የተለየ ክልል የለውም።ሊኖረውም አይችልም።

በመሆኑም ለቀደሙት አክሱም ኢስራኤላዊያን የአሁኑ አክሱም ትግሬዎች ፤ ከምዳማውያን አጋሜ/መ ትግሬዎች ተለይተው የአክሱም ክልል ይሰጠን ብለው እንደማይጠይቁ ሁሉ፤ የቀድሞው ከአክሱም ወደ ላስታ ከላስታ ወደ በጌምድር የተሸጋገሩት ጥንታዊ የኢስራኤላዊይና የአገው ተወላጅ አይሁዳውያን በኋላም ከዋክሹሙ ከቋረኛው፣ ከወረሴው፣ ከጋፋቴው ከሌላውም የተቀላቀለው አማራ በሚል ስም ተጠቃሎ  በሺህ የሚቆጠር ዘመናትን ካስቆጠረ በኋላ  ቅማንቴ፣ጋፋቴና ቋሬ እንዴት ክልል ይሰጠው የሚል ክፋት ወደ ኋላ ዘመናትን አቋርጦ አሁን  ጎንደር ውስጥ በትግራይ ተወላጆች ጥያቄ ሆኖ ሊነሳ ይችላል?

ይህ የሀገር ዋልታ የሆነውን ባለታሪኩን የአንድነቱን መሠረት ጎንደርን ከማፈርስ አንጻር የተጸነሰ ሰይጣናዊ ሴራ መሆኑን አስቀድሞ ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል።  ወያኔ ከትግራይ ውጭ በሆኑ ብሔሮች የማይቋረጥ ጦርነት በመጫር እራሱም የሚቻለውን ያክል በየቀኑ እየገደለ በመቀነስ እራሱን ብቻ  እያባዛ  መስፋፋቱን፣ መስረቁን እንደ መልካም ባህልና ቅርስ እያዳበረው ለትውልድ እያስተላለፈው ከመሁንም ከተለያየ ነገድ ተዋቅሮ የቆመውን በሰላም በሚኖረው ሕዝባችንና በትውልዳችን መካከል እንደ ዘመኑ አይሁዳውያንና ፍልስጤማውያን የማይታረቅ መርዝ እየደፋብ ይገኛል።

ከላይ ተያይዞ የመጣው የታሪክ አሻራ እንደተጠበቀ ሆኖ ጥልቅ ጥናታዊ ሥራውን በታሪክ ጠበብትነት ይበልጥ ለተራቀቁበት ባለሙያዎች በጥናታዊ ማስረጃ እንዲያረግጡልን አደራ ሰጥተን፤ የወያኔ መንግሥት ስሪት ኢትዮጵያን ያማፍረሱን ተግባር መሠረታዊና  ወሳኝ ዓላማው አድርጎ የተነሳ መሆኑን ደጋግመን በቁርጠኝነት መፈተሽ እና ስለሀገራችን ኢትዮጵያ ሁላችንም ከብረት በጠነከረ በአንድነት ተያይዘን መቆም ይኖርብናል። ወያኔ እየራቀ እየራቀ በከፍተኛ ጠላትነት የተነሳብን እንጅ ከአለፈ ጥፋቱ ተምሮ በጸጸት የመመለስና የማስተዋል ህሊናው መቶ በመቶ ተሰርዟል።

ወያኔ የቀድሞ ምድረ አጋመ የአሁኑ ትግራይን ከመገንጥልና በሀብትና በንብረት የበለጸገች ከማድረግ አንጻር የተጠቀመበት ማታለያ ስልት ሪፓፕሊካዊ ሳይሆን ፈደራላዊ የሚል ነው። ፌደራል ማለትም በክልል መንግሥስታት የሚተዳደር ክልልላዊ መንግሥት ኖሮት በማከላዊ መንግሥት የበላይነት የሚመራ  ሀገር ማለት ነው።

ፈደራል መንግሥታዊ አደረጃጀት መለያየትን፣ መከፋፈልን ውስብስብ ችግሮችን የሚያመጣ በመሆኑ  በአደጉ በተመነደጉ ሀገሮች ተመራጭነትና ተቀባይነት የለውም። አሜሪካ ኢትዮጵያን የሚያክሉ አምሳ ሁለት ሀገራት ይዛ በሪፓፕሊክ መንግሥት አደረጃጀት ነው የምትመራው፤ እንግሊዝም ዘውዳዊ ሪፓፕሊክ ዮናይትድ ኪንግደም ሁና ነው። የምትተዳደረው፤ እህንድም ሠላሳ ሁለት ኢትዮጵያን የሚያክሉ ሀገራት ይዛ በሪፓፕሊክ አደረጃጀት ነው የምትተዳደረው….. ወያኔ  በድሃ  ሀገራችን የሠራው ፈደራሊዝም የመከፋፈል አገዛዝ ሆን ብሎ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያዘጋጀው ቡል ደውዘር ወይም ደማሚት ነው።

ፊደራሊዝም  አንዱ ክልል በሌላው ክልልሉ ነጻነት ውስጥ ጣልቃ የማይገባበት ነጻነት ያለበት የሚመስል ሕግ ያለው ቢሆንም፤ ወያኔ ግን የአንድን ትግራይን ክልል ማንም በማይገባበት ሁኔታ በነጻነት እራሳቸው ይዘው ማዕከላዊ መንግሥቱንም ተቆጣጥረው ሌላውን እያደባደቡ በጦርነት እያመሱ እየከፋፈሉ በሌሎች ክልልሎች በማኝኛውም መልኩ ጣልቃ እየገቡ፤ ትግራይን ብቻ እንደ እንቁላል አስኳል የሚጠብቁበትና የሚስፋፉበትን መንገድ ብቻ ሆኖ ሌት ተቀን የሚሠሩበት የጥፋት ስልት መሆኑ ለማንም የተሰወረ አለመሁኑ ሲታውቅ፤ ለዚህ አስተዋጾዖ የሚያደርገው ደግሞ የሌሎቹ በየምክንያቱ ለመበላት የተዘጋጀ የተከፈፈለ ዳቦ ወይም የቅርጫ ሥጛ ሆኖ  ተዘጋጅቶ መጠበቅ ለወያኔ ይበልጥ ሠርግና ምላሽ ሆኖለት የመከራ ዘመናችን እንዳበዛው ማረጋገጥ ይኖርብናል።

በአሁኑ ጊዜ ትግራይ በፊደራል አስተዳደር ስም ነገር ግን በሌሎች ክልሎች ነጻነት በሁሉም መንገድ ጣልቃ በመግባት በሌሎች ክልሎችን የዘረፈችውን ንብረት ከአቅሟ በላይ በመሸከሟ ወገቧ ጎብጧል፤ ወደ ጎንደርና ወደ ወሎ ወደ ጎጃም  ቆዳዋን እየለጠጠች ቦርጯን በቀበቶ ማሰር ተስንዋታል ሚዛን ለክቶ በማይዘልቀው ከፍተኛ በሆነ የክብደት መጠን ላይ ተነፋፍታና ተወጥራ ትገኛለች።

ከዚህ አንጻር እንግዲህ በጥንት ስሙ ምድረ አጋሜ/መ ተብሎ የሚጠራውን ወጣ ገባ ሰንሰለታማውንና ገደላገድሉ ዳግም መወጣት መወረድ ከማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች። ይህን ያጎበጣትን የንብረት ክምችት በብቸኝነት ለመብላት አላግባብ በተለጠጠው ደልዳላ ቦርጯ ውስጥ አስገብታ ለመንፈላሰስ እንዲረዳት፤ የሀገር ዋልታ የሆነውን አማራውንና ኦሮሞውን ማዳከም  የመጨረሻ ወሳኝ ዓላማ አድርጋ ይዘዋለች።

በጎንድር በኩል የሀገራችን አዋሳኝ የሆነውን የሱዳንን ጦር ጣልቃ በማስገባት በወልቃይትና በጠገደ የሚገኘውን ህዝብ በጀምላ ስትጨፈጭፍና ስታስጨፈጭፍ የእራሳዋን ጎጆ በተገደሉት ወገኖች መቃብር ላይ በመገንባት ሥራ ላይ እጅግ ተጠምዳለች። አሁን ደግሞ ሱማሌን በኦጋዴን በኩል አሳልፋ በማስገባት ኦሮሞችን እያስገደለች  እያፈናቀለች  በኦጋዴን የሀገራችን መሬት ሶማሌን አስፍራ ኦረሞን ሕዝባችን መውጪያ መግቢያ ልታሳጣ  ከፍተኛ ጥረት እያደርገች ነው።

በጎንደር ውስጥ የቀድሞ ይዞታውን ነጥቃ መውሰድና መስፋፋትና በየቀኑ ከሚገደለው ወጣት በተጨማሪ ቅማቅንት ነን የሚል ስም ትግሬ ፈጥራ ተገንጣይ ከቀድሞ ምድረ አጋመ ወይም ትግረ ጋር የሚዛመድ፣ የሚሳሳብና የሚመሳሰል ክልላዊ ተገንጣይ ህዋስ ትግሬ ለመፍጠር  በከፍተኛ ደረጃ  እየደከመች ነው፤ ይህን ለማስፈጸም እነ ገዱ የቢባሉ እንሳዎችን ቀንበር ጭና እያረሰችባቸው ትገኛለች።

ስለዚህ በጠቅላላው ከአክሱም  ጀምሮ  የላስታ የጎጃምና የጎንደር  አንድነት ከፈጠረው የዘር ሐረግ ግንድ፣ ቋንቋ ና ነገድ ባህልና ታሪክ ህልውና ሞቱ በአንድ ላይ ከሆነው  አማራ ኢትዮጵያዊ ይዞታና ክልል ውስጥ ቅማንት የሚባል አማራ ክክል መፍጠር አይቻልም። ይህ የሚቻል ከሆነ ጥንታዊ የኢስራኤላዊ የአገው ክልል የሆነው አክሱም ትግሬ፤ ከምዳማውያን ሐረግ ከሚመዘዘው የጋሜ/መ ትግሬ ክክልል ተለይቶ መከለል ያስፈልገዋል ማለት ነው። ምክንያቱ ያክሱማውያን ይኖሩ የነበሩት አይሁዳዊ የኢስራኤላዊያንና የአገው ትወልድ፤ ሳይወድ በግዱ በምዳማውያን አጋሜ ትግሬ ተውጧልና የአክሱም ታሪክ በአይሁዳዊ ኢስራኤላዊ የአገው ታሪክ ብቻ ሆኖ ሳለ ተስፋፊ ከምዳማውያን የዘር ሐረግ የሚመዘዘው አጋሜ/መ በስመ ትግሬ የአክሱምን ክልል በወረራ በተስፋፊነት የቀማ በመሆኑ ነው።

ቸር ይግጠመን፤
Mengesha Melkie
melkiemenegesha@hotmail.com