Posted by admin
የመለስ_ዜናዊ ደጋፊዎች ታላቁ መሪ፥ አባይ ደፋሪ፣ የተለየ ሃሳብ ፈሪ፣ የሃሳብ ደሃ ሆኖ “የሃሳብ ድህነትን” ያስወገደ መሪ…ጲሪሪሪ እያሉ ሲያሽቃብጡለት፥ ሲያሽቋልጡ፥ ሲያመልኩት አዝቅክት ውስጥ ጥሎን አለፈ፡፡ በመለስ ዜናዊ ላይ የስድብ መዓት ሲያወርዱ የነበሩት ደግሞ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተነካብን ብለው “ያዙኝ-ልቀቁኝ” እያሉ ነው፡፡ ይሄም እንደቀድሞ ሰው ማምለክ፥ አጎብዳጅነት…ማሽቃበጥ፥ ማሽቋለጥ፥… ነው፡፡
ማንኛውም የመንግስት ሃላፊ በሥራ አፈፃፀሙ ላይ ትችትና ነቀፌታ ሊሰነዘርበት ይችላል፡፡ በሥራው ካጠፋ በአስቸኳይ እርማት መስጠት፣ ካላጠፋ ማስተካከያ(ማስተባበያ) መስጠት በሃላፊነቱ የተጣለበት ግዴታ ነው፡፡ አቶ ገዱ ‘ያለአግባብ ተሰደብኩ ካለ፣ በዚህም ሰብዓዊ ክብሬ ተነካ ወይም መልካም ስሜ ጠፋ” የሚል ከሆነ ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርቦ መብቱን ማስከበርና ተገቢውን ካሣ መጠየቅ ይችላል፡፡
