Wednesday, September 20, 2017

ጉዳያችን / Gudayachn

www.gudayachn.com

 

በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከተካተቱት ንዑስ አርዕስቶች ውስጥ

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ እርምጃ ምን መምሰል ይገባዋል?

የኢትዮጵያ የቅርብ ወቅታዊ ተግዳሮት ምንድን ነው?

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ህዝብን የሚንጥ እና ሚልዮኖችን ከጎናቸው የሚያሰልፍ የፖለቲካ ራዕይ ለሕዝቡ ማሳየት ለምን አልቻሉም?

እና ሌሎችም

መግቢያ 

ኢትዮጵያን ውክፕድያ በድህረ ገፁ ላይ እንዲህ ይገልፃታል

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ርዕሰ ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ ዓመት የሚያንስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ ነገሥታት እና ንግሥተ ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወመንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።ይላል

PDF ለማንበብ ይህን ይጫኑት⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/09/gudayachen.pdf