Skip to content
ባሳለፍነው እሁድ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንቶች ሰላም እንዲሰፍን እንሰራለን ካሉ በኋላ በምሥራቅ ሐረርጌ ጭናክሰን ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ቀሰሉ። ባደረግነው ማጣራት በጭናክሰን ወረዳ ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ 22 ሰዎች መገደላችውን፣ 35 ሰዎች መቁሰላቸውንና 86 የአርብቶ አደር ቤቶች በእሳት መጋየታቸውን ታውቋል። የጭናክሰን ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጀማል ሙሳ ጥቃቱ የተፈጸመው ከሶማሌ ክልል ተሻግረው በመጡ ታጣቂዎች ነው ሲሉ ለቢቢሲ የተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትዎርክ ያናገራቸው የወረዳው የፀጥታ ሃላፊ ጥቃቱ የተፈፀው በልዩ ሃይል እንደሆነ ገልፀዋል። አቶ ጀማል ሙሳ ጨምረው እንደተናገሩት ጥቃቱ ከመቆም ይልቅ እየጨመረ የመጣ ሲሆን የጥቃት ፈጻሚዎቹም ቁጥር ከፍ እያለ መሆኑን ነው። የሁለቱ ክልል ፕሬዝዳንቶች ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እናደርጋለን በማለት ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ያለው ግጭት እንደቀጠለ ነው።
የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትዎርክ ጋዜጠኛ ከጭናክሰን ወረዳ በጥቃቱ እየተቃጠለ የነበረ ቤት የተመለከተ ሲሆን በጥይት ተመተው የቆሰሉ ሰዎችንም አነጋግሯል።
Like this:
Like Loading...