September 21, 2017

ኢትዮጵያ አገራችን ከተመሠረተችበት 4 ሽህ ዘመናት ጀምሮ የምትመራበት በአምልኮተ እግዚአብሔር ነው።  የቀደሙ መንግሥታት ወደራሳቸው ክብርና ፍላጎት እየጠመዘዙ ህዝቡን በሚመቸውና በወደደው መንገድ የመምራት ጉድለት ቢታይባቸውም፤  እንደ ወያኔ ወራሪ ጠላት ድንበሯን አፋልሶና ቆራርሶህዝቡን በቋንቋ አናክሶ ያጫረሰ መንግስት አልተከሰተም። በመላ አፍሪካ ህዝብ የየራሱ የሆነ አፍሪካዊ ባህላዊ እምነት ቢኖረውም ከህሊናውና ካርበኝነት ጋራ ተዋህዶለት እንደ ኢትዮጵያ አጥር ግርግዳ ሆኖ ሐይማኖቱና ሥርአቱ ከወራሪ እንዲከላከል አልረዳውም። የህዝቡን ስነ ልቡና አንድ አድርጎ  ዜግነትን ጀግንነት ወንድነትንና አርበኝነትን በህዝቡ ልብ ላይ ሊቀርጽ አልቻለም። ባለማቻሉም ከአገራችን ከኢትዮጵያ በቀር ያልተወረረ ያልተገዛ የለም።

ኢትዮጵያን ዘላለማዊ ነጻነቷን ስንመለከት፤ የአምልኮት ስርአት  ነገረ መለኮቱ ከኦሬንታሎች ጋራ ያለን እንደተጠበቀ ሆኖ ኦርቶዶክሳዊነቱን ሳይለቅ ያምልኮቱን ስርአት የበዓላት አከባበር ከቀሩት እህት አብያተ ክርስቲያናትና ከባዛንታይኖች ለየት በማለት ለወራሪዎችና ለቅኝ ገዥዎች የተግሳጽ መልእክት በየበዓላቱ ከቤተ መቅደስ ታቦቱን መስቀሉን በማንቀሳቀስ ለተወላጁ ማንቃትና ማስጠንቀቅ ለወራሪዎች ተግሳጻና ቁጣ እያስተጋቡ ኢትዮጵያን ጠብቀው ሲያስጠብቁበት ኖረዋል። ይህንም ተረድተው ለህዝብ ማስረዳት የሚችሉ ከህጻንነታቸው ከፊደል ጀምሮ እስከ ከፍተኛው ያብነቱ ትምህርት ነጥረው ከተረዱ ምርጥ ሊቃውንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነገረ መለኮት አተረጓጎም አላምጠው ከተረዱ በኋላ፤ የምእራቡንና የምስራቁን ያተረጓጎም መንገድ የተረዱ መሆን ይገባቸዋል።

ዛሬ የወረሩን የኢትዮጵያን ቤተክርርስቲያን በሚገባ ሳይረዱ የሮማ ካቶሊኩን የፕሮቴስታንቱንና የባህላዊውን ሁሉ እንዲሁም ፍልስፍናውንና የተለያየውን ርዮዕተ-ዓለም እየቀላቀሉና እያግበሰበሱ ከባዕዳን የቀፈፉትን ሽርፍራፊ እውቀት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናት ውስጥ በእብሪት እየተጩት ይገኛሉ። ከዚህ ከዛም የቀላወጡትንና ለዘመናት በአብነት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጭምር ሲሰራባቸው የነበሩትንም ከተለያየ መጽሃፍት እየቀዱ የራሳቸው ስራ አስመስለው በመጽሃፍ መልክ እያወጡ ዋጋውን ለማክበድ እየጠለሰሙ ሃይማኖቱንም እያበላሹ ያበላሹበትንም መጽሀፍ  ለምዕመናን እየቸበቸቡ ኪሳቸውን እየሞሉ ህዝቡን በብዙ መንገድ እየበደሉት ነው።

እንደተረዳነው እያንዳንዱ በዓል የሚመለከው እግዚአብሔር አድርገው በበዓሉ ዙሪያ በመንደርና ባደባባይ የሚከናወኑት ባንዳንድ ባልበሰሉ ሰዎች ተከስተው ከሚታዩ  እንደስካርና መዳራት በቀር በዓበይት በዓላት የሚከናወኑት ህዝባውያን ሆታዎች፣ ዘፈኖች፣ ሽለላዎች፣ቀረርቶዎችና ግጥሞች ሁሉ ህዝባዊ ክብርን የነጻነትን ልዕልናን የሚያንጸባርቁ ናቸው። አንዱ በሚቀጥለው የምናስታውሰው የደመራው በዓል ነው። ይህን ተረድታችሁ ደመራን እንድታከብሩ “ደመራ” በሚል ርእስ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ያዘጋጁትን ታሪካዊ ጦማር ከበዓሉ አሰቀድመን አቅርበንላችኋል። ከዚህም በተጨማሪ አውደ ምህረት ላይ “ደመራ የጸሎት ስርአት ወይስ አርበኝነት?” በሚል ርዕስ ከዓመት በፊት በሁለት ክፍል ቀሲስ የሰጡትን ትምህርተ ወንጌልም አቅርበንላችኋል። ጦማሩን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ደመራ