September 26, 2017 15:51

ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የተላከ ወቅታዊ መግለጫ

Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP)
(አንድነት/United)

መስከረም ፰ ቀን ፪ ሺህ ፲ ዓ. ም

የህወሓት/ኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ በአገራችን ያደረሰውን መጠነሰፊ ጥፋት እኛም ሌሎች ድርጅቶችና ዜጎችም በስፋት በመተቸት ፖሊሲው በአስቸኳይ እንዲቆምና የመቻቻልና የዴሞክራሲያዊ አንድነት ፖለቲካ እንዲተገበር ደጋግመን ጥሪ አድርገናል። እብሪተኝነትና ማንአህሎኝነት የተጠናወተው የህወሓት አገዛዝ በጎሰኝነት ሥነልቦናው ታውሮ ጊዜያዊ ጥንካሬው በቋሚነት የሚኖር መስሎት፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የብሄር ክፍፍል መርዝ በመርጨቱ እነሆ በችግር ላይ ችግር እየፈጠረ አገራችንን ከአደጋ አፋፍ ላይ አድርሷታል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት እንኳን የፈጠራቸውን ችግሮች ብንቃኝ፣ በኢትዮጵያዊ ሶማሌዎችና ኦሮሞዎች መካከል በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው “የድንበር ጦርነት” የሕዝብ ለሕዝብ መጨራርስ በማስከተሉ ለትውልድ የሚተርፍ ቂም ፈጥሯል። በወልቃይት ችግር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና በወከላቸው የጎንደር ሕዝብ ላይም እንደዚሁ፣ “ከጎንደር በጉልበት ወደ ትግራይ የተካለልኩትን የወልቃይትን፣ የጠገዴንና የፀለምትን አካባቢዎች ጉዳይ ለምን ታነሳላችሁ” ብሎ የጎንደር ሕዝብ ላካሄደው ሕዝባዊ አመፅና እንቅስቃሴ አገዛዙ የቂም በቀል እርምጃ በመውሰዱ እነሆ ዛሬ የጎንደር ገጠር አካባቢዎችና ከተሞች በወታደራዊ ጭቆና በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ። ሕዝቡ ግን የአልሞት ባይ ተጋዳይነቱን ስለገፋበት ዛሬ ጎንደርና አካባቢው የጦርነት አውድማ ሆነዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ህወሓት በዚህ ሕዝባዊ አመፅ የደረሰበትን ጥቃት ለመመለስና ቂሙን ለመወጣት ሲል በቅርቡ ብአዴን የሚባለውን አገዛዙ እንዳሻው የሚዘውረውን እጅ ጠምዝዞ የጠገዴ ወረዳዎችን፣ የግጨውን በረሃና አካባቢውን ወደ ትግራይ ከልሎታል።

የአገር ህልውናና የሕዝብ ደህንነት የተጠናወተው ህወሓት፣ አሁንም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ላይ እኩይ ተግባሩን አላቆመም። ለዓመታት ሞክሮ ያልተሳከለትን ቅማንትንና አማራን የመከፋፈሉን እቅድ አሁን እንደገና ነፍስ ዘርቶበት፣ ሆድአደር ካድሬዎችን ተጠቅሞ “የቅማንት ወረዳዎች” ያላቸውን ክልሎች ሁሉ ብዙኃኑ የቅማንት ተወላጆች በከፍተኛ ድምፅ እየተቃወሙና ”ከአማራ ወንድሞቻችንና እህቶችን የሚለያየን የለም፤ አትከፋፍሉን!’’ እያሉ እንኳን “ጆሮ ዳባ ልበስ” ብሎ መሬት ማካለሉን ተያይዞታል ።

ይህ በህወሓት ተቀናጅቶ ጎንደርን እያፈረሰ ያለው የዘር ፖለቲካ በጎንደር ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነ ደጋግመን መግለጻችን የሚታወስ ነው። የሶማሊዎችንና የኦሮሞዎችን ሁኔታም ጠቅሰናል። አዲስ አበባንም በጎሣ ፖለቲካ ለማመስና ሕዝቡን እርሰ በርሱ ለማጋጨት ”የኦሮሞዎች በከተማዋ ልዩ ተጠቃሚነት” በሚል ፓርላማ ተብየው በቅርቡ ውሳኔ እንዲሰጥ ‘መታዘዙ’ ተጠቃሽ ነው።

የህወሓት የጎሣ ፖለቲካ መዘዝ ማለቂያ የለውምና ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች የተውጣጡና የተዋለዱ ኢትዮጵያዊነታቸውን ብቻ የሚያውቁ ኢትዮጵያውያንን የእንጀራ ልጆችና የበኩር ወራሽ ልጅ እያለ በሕዝባችን ሕይወት ቁማር እየተጫወተ ይገኛል። በተጨማሪም፣ የምዝበራው አካል አንድ ክፍል የሆነው ስግብግብነት ከተጨባጭ ሁኔታው ጋር የሚጻረር የግብር አሰባሰብ አዋጅ በማወጁ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት ይኽውና ዛሬ ከነጋዴው ጋር በትንንቅ ላይ ይገኛል።

አሁን 2010 . ም ገና ከመግባቱ ደግሞ ሕዝባዊ ንቀቱ ጣራ የነካው የህወሓት አገዛዝ፣ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ያማከሉ አዳዲስ የሙዚቃ ጣዕመ ዜማዎችን ያቀናበረውንና በእጅጉ የሕዝብ አድናቆት ያተረፈውን የቴዎድሮስ ካሳሁንን (የቴዲ አፍሮን) የዘመን መለወጫ ዝግጅት ያለምንም ሃፍረት አግዶበታል። አገር ወዳዱ የኪኒት ሰው አገዛዙን ከማንቀጥቀጥ ባሻገር ተወዳጅነቱ በሕዝባችን ዘንድ ከዕለት ዕለት እየጨመረ እንዲሄድ አድርጎታል።

ይህ ሁሉ የህወሓት ዕብርተኛነት በድምሩ የሚያመለክተን አንድና አንድ አብይ ጉዳይ ብቻ ነው። ይኸውም፣ አገዛዙ ለ26 ዓመታት እየተሻለው ሳይሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት እንደመጣ ነው። ከእንግዲህ ወዲያ አገዛዙን ከማጋለጥና ከመተቸት ባሻገር ሕዝባችን መብቱንና የአገሩን ህልውና ለማስከበር የተናጠል እርምጃ ሳይሆን የተደራጀና የተቀናጀ ሕዝባዊ አመፅ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ማካሄድ ብቻ ነው! እንዳለፉት ጊዜያት እዚህም እዚያም የሚነሱ ፀረአገዛዙ አመፆች በቀላሉ የሚያፍናቸው እንዳይሆን በቁርጠኝነት የተነሳ አገርአቀፍ አደረጃጀትና ብሔራዊ ይዘት ያለው አገዛዙን ከማሰወገድ መለስ ምንም ዓይነት ግብ እንደሌለ የቆረጠ አመፅ ሊካሄድ ይገባል እንላለን።

አዲሱ ዓመት የፖለቲካ እስረኞቻችንን የምናስፈታበትና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የምንገነባበት ዘመን ይሁንልን!

ይህ ሁሉ የህወሓት ዕብርተኛነት በድምሩ የሚያመለክተን አንድና አንድ አብይ ጉዳይ ብቻ ነው። ይኸውም፣ አገዛዙ ለ26 ዓመታት እየተሻለው ሳይሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት እንደመጣ ነው። ከእንግዲህ ወዲያ አገዛዙን ከማጋለጥና ከመተቸት ባሻገር ሕዝባችን መብቱንና የአገሩን ህልውና ለማስከበር የተናጠል እርምጃ ሳይሆን የተደራጀና የተቀናጀ ሕዝባዊ አመፅ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ማካሄድ ብቻ ነው! እንዳለፉት ጊዜያት እዚህም እዚያም የሚነሱ ፀረአገዛዙ አመፆች በቀላሉ የሚያፍናቸው እንዳይሆን በቁርጠኝነት የተነሳ አገርአቀፍ አደረጃጀትና ብሔራዊ ይዘት ያለው አገዛዙን ከማሰወገድ መለስ ምንም ዓይነት ግብ እንደሌለ የቆረጠ አመፅ ሊካሄድ ይገባል እንላለን።

አዲሱ ዓመት የፖለቲካ እስረኞቻችንን የምናስፈታበትና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የምንገነባበት ዘመን ይሁንልን!

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በልጆቿ አንድነት ይከበራል!

P.O.Box 91384 Phone: 202- 241 2078

Los Angeles, CA 90009


eprp_united@eprp-ihapa.com