September 26, 2017 21:15

እውነት አማራ ላይ የተፈፀመውና ያንዣበበው አደጋ በቋንቋ የሚገለፅ አይደለም

1.አማራው #በምጣኔ ሀብታዊ እድገት መለኪያ ላለፉት ተከታታይ አመታት እድገት ካስመዘገበው የመንገድና መብራትን ዘርፍ የሚሸፍነው መሰረተ ልማት ተጣቃሚ አይደልም።

(የዓለም ባንክ የጥናት ውጤትና የአማራ ብዙሀን መገናኛ ከሳምንታት በፊት የሰራው ዘገባ የዚህ ዘርፍ ማሳያ ነው።)
በየመንደሩ ስራ አጥ ሁነው የተቀመጡ ከዩኒቨርቲና ኮሎጅ የተመረቁ ወገኖቻችን መመልከት ብቻ በቂ ነው።

2.አማራው #በማህበራዊ በተለይ በጤናው ዘርፍ ተጠቃሚ አይደለም።

DHS 2016 የዘርፉን የኢትዮጵያ እድገት እና የክልሎች አፈፃፀምና ድርሻ በግልፅ ባሰፈረበት ከአስር በላይ መስፈርት የአማራ ክልል ከወሊድ ምጣኔ ውጭ (ይህም ጠቃሚም ጎጅም ነው) በሁሉም ዘንድ ዝቅተኛ እና መጨረሻ ነው።

3.አማራው #በፖለቲካው ዘርፍ ውክልና የለውም።ወይም ያለው ሀይል ሳተላይት አስተዳዳሪ (ፖስተኛ) እንጅ ከአብራኩ በወጡ፣የአማራን ህዝብ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጡ፣እውነተኛ እና የመደራርደ አቅማቸው የህዝቡን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሪዎች የሉትም።ይህ ጉዳይ በተለይ ለአዲሱ የብአዴን አባላት ከመረጃ እጥረትና ከአማራጭ ማጣት ጋር ተያይዞ እውነት መሆኑን ለመቀበል ይቸግራቸዋል።በዚህ አስተሳሰብ የተቃኙ የሰው ሀብት ልማት ላይ ፊት ለፊት የሚሰለፉ የእኛ ወገኖች ግን ከማስፈራራትና ከመዋሸት ወደጠላት ካምፕ እንዲጠጉ ከማደረግ ይልቅ በምክንያት ማስረዳት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

4.አማራው #የዘር_ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞበታል።ይህንን ደረቅ ሀቅ ለመቀበል ብዙዎቻችን በተለይም በዞንና ወረዳ የምንኖር የጥናቶችና የድብቅ ሰነድ ማስረጃዎች በቀጥታ የማናገኝ ሰዎች ጆሯችን አቁመን የት፣መቸ፣እንዴት፣ በእነማን…የሚሉት ጥያቄዎች እንዲመለሱ ማነፍነፍ አለብን።የዛሬ 10 ዓመት ገደማ በፓርላማ ላይ የተደረገ ሪፖርት ከሀገሪቱ ህዝብ ቁርጥ 2 ሚሊዮን ቁጥር ሲጎድል ይህ “ከአማራ እና አዲስ አበባ ጋር የተያያዘ ነው” የሚለው የፓርላማ ማጠቃለያ ቀላሉ ማስረጃ ነው።በ1974 ከኦሮሞው በ3 ሚሊዮን ይልበጥ የነበረ የአማራ ህዝብ ከ30 ዓመት በኋላ ከኦሮሞው በ15 ሚሊዮን አንሶ ሲገኝ ለምን? ብለን ስንጠይቅ ሙሉ መልስ እናገኛለን።

5.አማራ #እሴቱ እና ባህሉ እንዲጠፋ እየተሰራ ነው።

የኢትዮጵያ መለያ የሆኑ የባህል እና ወጎቻችን “የነፍጠኛው ስርዓትና እና የነገስታቱ ቤተሰቦች ናቸው፤ እናንተ ላይ እኮ በሀይል ተጭነውባችሁ ነው እየተባለ እንዲጠፉ እየተደረገ አማራውም የበለጠ በእሴቶች እንዳይኮራ፣ እንዳይንከባከባቸው፣ በታሪኩ እንዳይመካ እየተደረገ ይገኛል።

የምኒልክ ሰፋሪ፣ የነፍጠኛው ስርዕት የወለደው ትምክህተኛ፣ የሸዋ ጨቋኝ ነገስታት መገለጫዎች፣ ወዘተ ናቸው በሚል ዘሬ ነጭ ልብስ፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ምልክት ያለው ነገር ሁሉ እንዲጠፋ ሰፊ ስራ ተሰርቷል።የአማራው የደስታና የሀዘን መግለጫ ስነስርዓቶች የቴሌቪዥንም ይሁን የሬዲዮ ሽፋን አይሰጣቸውም።ይልቁንም የታዳጊ ብሄሮች ጭፈራ ሰፊ ሰዓቱን እየያዙ ሌላው ነባር ባህል እየተረሳ እየመጣ ነው።

የዚህ መፍትሄው አንተ የጠላውኸን አሞሌ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉታል ነውና መፍትሄው የራስህን አልማዝ ሌባና ተንኮለኛ የማይደርስበት ቦታ ከፍ አድርገህ መስቀል ነው።

6.አማራው #ከርስቱ ተፈናቅሏል።ያለፈቃዱ ተካሏል።እዚህ ላይ እነ መተከል፣ራያ፣ወልቃይት ያለ ማብራሪያ ቋሚ ምስሮራች ናቸው
የዚህ መፍትሄው አንተ የጠላውኸን አሞሌ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉታል ነውና መፍትሄው የራስህን አልማዝ ሌባና ተንኮለኛ የማይደርስበት ቦታ ከፍ አድርገህ መስቀል ነው።

6.አማራው #ከርስቱ ተፈናቅሏል።ያለፈቃዱ ተካሏል።እዚህ ላይ እነ መተከል፣ራያ፣ወልቃይት ያለ ማብራሪያ ቋሚ ምስሮራች ናቸው

7.አማራው #ማህበረሰባዊ_እረፍት እንዳይኖረው እየተደረገ ነው።አማራ በባህሪው ሰላማዊና ካልደረሱበት የማይደስር ህዝብ መሆኑ አስረጅ አይሻም።በቅማንት ስም ወሃትው መቀሌ ቢሮ የከፈታቸው “ትግረ-ቅማንትነይ” ጃኬት ለባሾች ለዚህ ቀላል ምሳሌ ናቸው። አፋር አካባቢ፣ ሰሜን ሸዋ ላይ ኦሮሚያ ክልል ድንበር ጋር፣ ወዘተ በየወቅቱ የሚለኮሱ የሰደድ እሳቶችን ቆም ብላችሁ ለምን? ብችሁላ አጢኗቸው።