October 1, 2017 11:43

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያን ለማታውቀው ገንዘብ ምስክር አልሆንም አሉ፤ የመቀሌው ታላቁ ታወር መስቀል ከማኅበረ ቅዱሳን በተገኘው «ግብር በማያውቀው ሕገወጥ ገንዘብ» ወጪ እደተሠራ ተነገረ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ የሒሳብ ሪፓርት ማድረግ አለብኝ በማለት ፓትርያርኩን እየተማጸነ ነው፤ ማኅበሩ ጥፋቱን ለመሸፍን የፈጠረው ስልት በሚል ተቀባይነት አላገኘም፤ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ስም ያካበተውን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ገንዘብና ንብረት ወደ ሕጋዊ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ሶርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካዝና እንዲመልስ ፓትርያርኩን መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ሊቃነ ጳጳሳትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች በከፍተኛ ደረጃ እየመከሩበት መሆኑ ተሰማ። ቅድሚያ ማስገንዘቢያ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  የእምነት ሥርዓት ውስጥ ማኅበር ማለት  ከእምነት ጋር  በተቆራኘ በመንፈሳዊ  በበጎ አዳራጎት፣ ለመረዳዳትና ለመተሳሰብ፣ እንዲሁም ሰላማዊ ግኑኝነት ለምፍጠር በቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ስም የጽዋ ማኅበራትና ክርስቲያናዊ ዕድሮች እየተቋቋሙ፣ ምዕመናን ይሰባሰቡበታል። የማኅበራቱ የአባላት ቁጥር እየበዛ ሲሄድ አቅማቸው እየጠነከረ ሲመጣ በተሰባሰቡበት ቅዱስ ስም የቤተ ክህርስቲያን ሕግ እና ሥራዓት በሚፈቅደው መሠረት በአጥቢያ ደረጃ  አቢያተ ክርስቲያናት በማቋቋም የአቢያተ ክርስቲያናት መሠረት ጌጥና ውበት ሆነው ሲኖር ዘመናት ተቆጥረዋል። ወጣቶችም እንደዚሁ በአጥቢያው ሰበካ ጉባዔ እየተደራጁ ትምህርተ ወንጌል እያገኙ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው እንዲያድጉ ከመምሪያ ጀመሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በተዘረጋ መዋቅር ታቅፈው እንዲያድጉ በማድረግ ከሃምሳ ዓመት በላይ ሲሠራበት ቆይቷል። በአጭሩ ማኅበራት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ አስተዳደር ሥር የሚተዳደሩና የሚመሩ የአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን አባላት በመሆን የሚያገለግሉ በካህናት የሚዘከር የሚባረክ የምዕመናን አንድነት የጽዋ ወይም የዕድር ማኅበር በመባል ይታወቃል። ከዚህ ውጭ የበላይ የበታች ከፍተኛ ዝቅተኛ የሚባል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላ ማኅበር አይታወቅም። ቅዱስ ሲኖዶስና ከመንበረ ፓትርያርክ  ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ በየደረጃው በተቋቋሙ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የሀገረ ስብከትና የወረዳ ቤተ ክህነት መሥሪያ ቤቶች የሚያስተዳድሩት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናትን እንጅ ማኅበራትን አያስተዳድርም አያቋቁምም። ይህን በሚመለከት ያወጣችው የቤተ ክርስቲያን ሕግ የለም። ከሃያ አምስት ዓመት በፊት በነበረው የቤተ ክርስቲኗ ታሪካዊ ሐዋርያዊ ጉዞ እንደዚህ ዓይነት ተግባር አይታውቅም። በቤተ ክርስቲያን ሕግም ቅዱስ ሲኖዶስ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትን እንጅ፤ የጽዋ ማኅበራትንም ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸውን ማኅበራትን እያደራጀ እንዲያስተዳደር አልተደነገገምለት። ማኅበረ ቅዱሳን እራሱን አደራጅቶና ፍጹም መንፈሳዊ መስሎ የገባው ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ጀምሮ  እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ በተዘረጋው መስመርና በትክክለኛ በር ሳይሆ የሲኖዶስ አባልቱን ከፍሎ የንስሐ አባት በማድረግ በመሰላልነት ወጥቶ በጉልላቱ በኩል እራሱ በእራሱ የመግቢያ ምስኮት ቀዶ የገባው ተቋም ነው። ይህን ኃይልና ጉልበት ለማግኘት ወጣቱን በሃይማኖት አሥሮ ያለአመጽ ይጠብቃል በሚል ከወያኔ መንግሥት በኩልም ድጋፍ አለው። ለዚህም ነው የመጀመሪያውን ኢግዚቢሽን እንዲያደግ ፈቅዶለት በ1985/86 ዓ.ም በአንድ ጊዜ የአሥራ አምስት ሚሊዮን ብር ገንዘብ ባለቤት እንዲሆን የተመቻቸ ሁኔታ የተፈጠረለት። ከዚህም በተጨማሪ ይህን ሕገወጥ ተግባሩን ሕጋዊ ለማስመሰል ማኅበሩ ከመፈጠሩ በፊት በ1982 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሕይዎተ ሥጋ የተለዩትን ታዋቂ አባቶች እነደነ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ያሉትን ስም በመጥቀስ ማኅበረ ቅዱሳንን አምጠው የወለዱ  እያለ  በስማቸው በመነገድ  የማሳመኛ ፓሮፓጋንዳ ሰርቷል። ማኅበሩ ዛሬ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ በመምሪያ ሥር እተዳደራለሁ ይላል፤ አቅሙ ከመምሪያው በላይ አሥር እጥፍ ገዝፎ እና አልፎ ቅዱስ ሲኖዶስን ይገዳደራል። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶችን በመሰለል እንደ አስፈላጊነቱ እንደሚከተለው ከፋፍሎ ይቆጣጠራቸዋል፤ 1ኛ/ ደጋፊዎቹን ሊቃነ ጳጳሳት ክንፍ ያውጡ የበቁ የጸደቁ ናቸው ብሎ በማምስገን በወዳሴ ከንቱ በመሳሪያነት ይጠቀምባቸዋል፤ 2ኛ/ የሚቃወሙትን ሊቃነ ጳጳሳት ንስጥሮሳዊ፣ አርዮሳዊ፣ ተሐድሶ፣ አማሳኝ፣ቅባት እያለ ክብረ ነክ በሆነ መልኩ በእራሱ ሥልጣን ያወግዛል፤ 3ኛ/ የጤና ችግር ያለባቸውን ሊቃነ ጳጳሳት የሕክምና ወጭ በማድረግ በገንዘብ ድጎማ እያታለለ ሳይውድ በግዳቸው ደጋፊው ያደርጋቸዋል፤ 4ኛ/ የተወሰኑትን ሊቃነ ጳጳሳት ሀጥያት አለባችሁ ምስጢራችሁን እናውቃለን  ትጋለጣላችሁ እያለ ተቃውሞ እንዳያነሱ ጸጥ ረጭ በሉ እያለ አፋቸውን ለጉሞ ያስፈራራል። 5ኛ/ የተወሰኑትን ሊቃነ ጳጳሳት የጠሉትን በማኅበራዊ መገኛኛ /በሚድያ/ ስም አጥፊዎችን ቀጥሮ ሰለሚሰደብላቸው የማኅበሩ ጀሮ ጠቢ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሆነው የቅዱስ ሲኖዶስን እንዲሰልሉ አድርጎ በመያዝ በየዕለቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚተነፍሳትን ሁሉ ማታ ማታ እያናዘዘ አለዚያም በስብሰባ ወቅት ሥልካቸውን ከፍተው እንዲቀመጡ በማድረግ ስልኩን ጠልፎ በመያዝ ማንኛውንም የሲኖዶስ ውይይት ቀጭ ብሎ የሰማና በሐራ ዘተዋህዶ ድህረ ገጹ ለራሱ ፍጆታ በሚፈልገው መልኩ የሚያጸድቀውን አጽድቆ የሚኮንነውን አውግዞ አቀናጅቶ ያቀርባል። ሲኖዶስ በአሁኑ ስዓት የማኅበረ ቅዱሳን እስረኛ ነው። ማኅበሩ ዚህ ዓይነት መንገድ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ከፍተኛ የአስተዳደር ችግር ሲፈጥር እንደቆየ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል። በአድባርትና ገድማት አስተዳዳሪዎችም  አመራር ላይ ችግር እየፈጠረ በከፍተኛ  ሰቆቃ እያማረሩ የቆዩ  ከመሆኑም በላይ በቅርቡ በአማሪካን የአማረኛ ድምጽ ሪዲዮ ቪኦኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በእውነት ላይ በተመሠረተ ከፍተኛ ትችት የደረሰበት ሲሆን፤ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰዎችን  በማንቃት ይህ ማኅበር ማን ነው? የሚለውን ጥያቄ እንዲያነሱ እንዲመረምሩ አስገድዷል። ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ገቢ መሆን የሚችለውን ገንዘብም ስልጡን በሆነ በዘመናዊ ስልት በመጠቀም ለዘመናት በረቀቀ ምስጢር ደጋግ አባቶቻችን ሽንብራ እየቆረጠሙ ወገባቸውን አስረው በክብር ያቆዩትን ውድ  ቅርሶችን ማይክሮ ፊልም በማንሳት፣ ፎቶ ኮፕ በማድረግ፣ ሊቃውንቱን በትንሽ ድጎማ በማታለል ብዙ ቅጆችን በማባዛት፣ የቤተ ክርስቲያኗን ነባራዊ ታሪካዊ ሁኔታ በግሉ አለማንም ፈቃድ ኢግዚቢሽን በማሳየት፤ የሊቃውንቱን መጽሐፍ የቃላት ቁማር እየተጫወተ የእራሱ አስመስሎ  በአዲስ መልክ እያሳተመ በመሸጥ፤ የመካነ ቅዱሳን ጉብኝት ጉዞ በማዘጋጀትና በመሳሰሉት ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ነገር ግን ማንም ሊገባበት በማይችለው መልኩ በግሉ በብዙ ሚሊዮኖች  የሚቆጠር ከፍተኛ የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ገንዘብና ንብረት አካብቷል። ንብረቱ ከቤተ ክርስቲያን አብራክ በቤተ ክርስቲያን ስም የተሰብሰበ ቢሆንም ተቀማጭነቱ ቤተ ክርስቲያን በማታውቃቸው ባልወከለቻቸው ግለሰቦች ኃላፊነት ብቻ ነው። ይህ ድርጅት በግሉ በየክፍለ ሀገራት ብዙ ማዕከላትን ከፍቶ ንግዶችን ያስፋፋል። ከሀገር ውጪ በአውሮፓና በአሜሪካ ጭምር ውስጥ ውስጡን ገለልተኛ የሚባሉትን ቤተ ክርስቲያን በማጠናከርና በመቆጣጠር የቤተ ክርስቲያንዋ ብቸኛ ባለቤት ለመሆን ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኝ ነው። በአሜሪካን ሀገር አሥራ አራት በሚደርሱ ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቀጥታ እጁ አለበት። በኢትዮጵያ አርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ የአስተዳደር  ሰንሰለትን በመጠቀም እራሱን በየደረጃው አዋቅሮ ማዕከላትን ከፍቶና ተስፋፍቶ ከወያኔ መንግሥት ጋር ተግባብቶና ተስማምቶ ለሃያ አምስት ዓመት በዋናነት የቤተ ክርስቲያኗን አካል መስሎ  ውጫዊና አፋዊ መንፈሳዊነትን አጉልቶ በማሳየት በነጭ አልባሳት አሸብርቆና ተሸፍኖ የእራሱን የንግድ መረብ ዘርግቶ ምንም ግብር ሳይከፍል የሚሠራ ነው። ዛሬ ጉልት ድንችና ሽንኩርት የመትሸጠው ድሃ ዜጋ ቆጥራው ያማታውቀውን ግብር እንድትከፍል ስትገደድ፤ ወያኔን በረቀቀ ስልት የሚያገለግለው ማህበሩ ከማኝኛውም ግብር ነጻ ነው። በቤተ ክርስቲያን ሀበትና ንብረት አራት ኪሎ በሚገኘው የማኅበሩ ሕንጻ ሰፊውን የሕንጻ ክፍል የሚጠቀምበት ወጋገን ባንክ የሚባለው የህውሀት የግል ባንክ ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱን ተከታይም በግሉ እየመለመለ አባል በማድረግ አሥራት በኩራት/ የአባልነት መዋጮ እያለ ያሰባስባል። ይህም በማወቅም ሆነ ባለማውቅ እያንዳንዱ አባል በሚኖርበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ኩባኤ አስተዳደር ማድረግ የሚገባውን የእምነት ግዴታ ሳልፎ በመስጠት የማኅበሩ ምርኮኛ ገባር ወርንዝና ጅረት ለመሆን ተገድዋል። ወጣቶችን ማኅበሩ በዙ ሳይንቲስቶች ኢንጅነሮች ያሉበት ቅዱስ ማኅበር ነው። እያለ በማወጅ፤ አንዳንዶች ማኅበረ ቅዱሳን አባል መሆን ማለት፤ የተማሩ የተራቀቁ ማኅበር አካላት፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የታውቁ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የተላኩ ልቡሰ ሥጋ በምድር ላይ የተለቀቁ መልአእክት፤ በእምነት የተመረጡ ቅዱሳን  ከመሞታቸው በፊት ገነት መግባታቸውን ያረጋገጡ የሆኑ ስለሚመስላችው እራሳቸውን እያታለሉ የማኅበሩ አባላት በመሆን ሳያውቁት በቤተ ክርስቲያን ላይ ሕገ ወጥነትን በማዳበር ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያንን ያዳክማሉ። ማኅበሩን የማይደግፉትን የአባቶችን ክብር ያዋርዳሉ። የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ያፋልሳል። ለመንፈሳዊ አስተዳደር እንቅፋት ይፈጥራል። የቀዱስ ሲኖድስ ውሳኔ ያዳክማል። የቤተ ክርስቲያን አባቶች ወደ እርቅ ወደ ሰላም እንዳይመጡ እንቅፋት ይፈጥራል። አገልጋዮች ካህናትን በጎሳ ይከፋፍላል ለችግርም ይዳርጋሉ። ወጣቶች በመፈሳዊ አብቶቻቸው ላይ አመጽና ድፈረት እተሞላው ባህሪ እንዲኖራቸው መጥፎ አርአያ ይሆናል። ማኅበሩ ይህ  የተበላሸ  ሰይጣናዊ ዓላማው ጎልቶ እንዳይወጣበትና እንዳይታወቅበት ካሉት ስልጡን ስልቶች መካከል ጥቂቶቹና ዋናዎቹ የሚከትሉት ናቸው፤ 1ኛ/ ቤተ ክርስቲያኗን የሚጠብቅ ከእግዘብሔር የተላክ ልዩ መልክተኛ የጻድቃን ሰማዕታቱ ልዩ ጠበቃ ትክክለኛ ፍጹም አማኝ አድርጎ እራሱን በመስበክ፤ 2ኛ/ ያለባቸውን ደካማ ጎንና ችግር በማጥናት አንዳንድ ታዋቂ ሊቃውንትን በመጠነኛ ደጎማ በማግባባትና በማታለል፤ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አዋጅ ነጋሪ ነገር ቀማሪ አድርጎ በማጥመቅ፤ 3ኛ/ በመንፈሳዊ  ዕውቀታቸው፣ በእምነት ብቃታቸው ጠንካራ የሆኑ ታዋቂ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር እራሱን በከፍተኛ ደረጃ በማስጠጋት ፍጹም አማኝ የቤተ ክርስቲያን መሠረት አድርጎ ማኅበረ ቅዱሳን ከሌለ ቤተክርስቲያን የለችም ብለው እንዲያውጁ ያግባባል ያስገድዳል፤ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ  በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው። 4ኛ/ አንዳ አንድ ታዋቂ መካነ ቅዱሳንና የታሪክ ቦታውችን እያጠና ከአካበተው ከፍተኛ ገንዘብ ላይ ትንሽ ምጽዋት እየሰጠ የራሱን ቅድስና አጉልቶ በማሳየት እራሱን በራሱ በማስተዋወቂያ ስርጭት በማጋነን በቤተ ክርስቲያን  በሬ ጠምዳ ባላረሰችው ይዞታዋ በሆነው ድንግል መሬቷ ላይ እያረሰ ምርቱን በልዮ በሆነ ምድራዊ ጎተራ በመዘገብ ኃይልና ጉልበት በማግኘት የቤተ ክርስቲያ ገዥ ለመሆን እይደፈረ ነው ። ለዚህ ነው ብፁዕ ውቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ «ቤተ ክርስቲያን በራሷገንዘብ በቅኝ ግዛት ቀነብር ውስጥ ተይዛለች» ያሉት። ዛሬ የማኅበሩ በተለይም በአመራር ደረጃ ያሉት በሙሉ ከመንግሥት ሚኒስተር  መሥሪያ ቤት በምንስትር ደራጃ ካሉት የፓለቲካ ተቀጣሪዎች በላይ እንዲሁም ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሚያገኙት ደመወዝ የላቀ በከፍተኛ ደረጃ ደመወዝ የሚከፈላቸው ናቸው።  ይህም በልዩ ልዩ ምክንያት የሚከፈላቸን ሳይጨምር ነው። የማኅበሩ ከፍተኛ አመራር አባላት በሙሉ በአዲስ እባባ ከተማ ሠርተው የሚንደላቀቁባቸው ቪላዎች እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያላቸው ናቸው። ይህ በንዲህ እንዳለ በቤተ ክርስቲያን ስም ከቤተ ክርስቲያን አብራክና ጉረሮ በየጊዜው እየሰበሰበ ከሚያገኘው ትርፍ ዶላር በመግዛት ሲያካብት የቆዩ ቢሆንም፤ የወያኔ መንግሥት የራሱን ታማኝ ሰላዩች አስቀምጦ ገንዘቡ ከየት እንደሚመጣ ወዴት እንደሚሄድ በቅርብ እርቀት ሲከታተልና ሲቆጣጠር ነበር። ማኅበሩም ባለሀብት ኢንቨስተር  እንደመሆኑ መጠን ይህ ንብረቱ እንዳይወሰድበት  ለመጠበቅ የወያኔ አንጋች አጎንባሽ ሆኖ ለሃያ አምስት ዓመታት አብረው ተስማምተውና ሰምና ወርቅ ሆነው ተደጋግፈው እስካሁን ዘልቀዋል። ከፓትርያርኩ ጋር በተጣሉ ቁጥር በማኅበረ ቅዱሳን በኩል አማላጅ ሆነው የሚላኩት አቶ ካሣ ተክለ ብርሃን የሚባለው የወያኔ ሰው ነው። የቤተ ክህነቱ ሰዎች የማኅበረ ቅዱሳን ልዩ አባል በማለት ለአቶ ካሳ  ስም አውጥተውለታል። አቶ ካሳ ተክለብርሃን ሳይገባው በሆነ ባልሆነው  ምክንያት እየፈጠረ በቅድሱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መገኘት ወክሎ ለሚልከው  ለማኅበረ ቅዱሳን የነበረው ጥብቅና ወደር የለውም በማለት ውስጥ አዋቂዎች ይጠቁማሉ።  ለዚህ ነው ብፁዕ ወዱስ አቡነ ማትያስ  ፓትርያርክ የማኅበሩ አባል የሚሆኑት ሀበታሞች እየተመረጡ ነው። በማለት አጋድመው የተናገሩት። ማህበረ ቅዱሳን በሃያ አምስት ዓመት ውስጥ አምስት ሚሊዮን  በላይ  የቤተ ክርስቲያኗ  እምነት ተከታይ ጠፍቷል ሲባል ድምጹን አላሰማም፤ ድምጹን ካሰማ ከመንግሥት ጋር ይጣላል፤ ሀብትና ንብረቱን ላይ አደጋ ይመጣል። የዋልድባ መነኮሳት መከራቸውን ሲያዩ ድምጹን አላሰማም፤ ድምፁን ካሰማ ከመንግሥት ጋር ይጣላል ሀብትና ንበረቱን ያጣል። በአደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ የወጣ ዜጋ ሕዝብ ሲገደል ማኅበረ ቅዱሳን ድምጹን አላሰማም፤ ድምፁን  ካሰማ ከመንግሥት ጋር ይጣላል  ሀብትና ንብረቱንም ያጣል።  በሰሜኑ ክፍል የወያኔ ወታደሮች አቢያተ ክርስቲያናትን ፈተሹ ታቦታትን በረበሩ ሲባል ማኅበረ ቅዱሳን ድምጹን አያሰማም ድምጹን የሚያሰማ ከሆነ  ያካበተወን ሀበትና ንብረቱን ያጣል። ታዲያ የማኅበረ ቅዱሳን ቅድስና የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪነት ክንፍ እስኪያውጣ መጠበቅ የእኛ ድርሻ  መሆኑ ነው። የወያኔ መንግሥትም  በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የቅዱስ ሲኖዶስን ጩኽት እየሰማ የፓትርያርኩን ልቅሶ እያዳመጠ የዝሆ ጀሮ ይስጠኝ ብሎ  ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳንን በስውር ይከታተላለዋል ይጠብቀዋልም። ይህም የሆነበት ምክንያቱም ወጣቱን በሃይማኖት ስም አፍኖ« ነይ ነይ እምየ ማርያም» እያለ ሲያዘምረው ይወላል በሎ ስለሚያስብ ነው። አንዳንድ ማኅበረ ቅዱሳን ድጋፍ ያልተለያቸው  ሰባክያነ ወንጌልም በሀገር ውስጥ ብቻ  ሳይሆን በውጭ ሀገራት ጭምር እየተዘዋወሩ ይህን የሚያስፈጽሙ እንዳሉ መዘንጋት የለብንም። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳን ያለውን ንብረት እንዲያሳውቅ፣ የሒሳብ ምርምራ እንዲደረግ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲመራ፣ ደርጃውን ጠብቆ የሰንበት ትምህርት ቤት መምሪያ ታዛዥ ሆኖ እንዲሠራ፤ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ላይ ችግር እንዳይፈጥር፣ የቤተ ክርስቲያን ገቢ ሳይገባው እንዳይሰበሰብ፤ በቤተ ክርስቲያን ስም አላግባብ ተጠቃሚ መሆን እንዲያቆም ብለው ትዕዛዝ በመጻፋቸው ብቻ፤ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው እንደ አረማዊ ተፈርዶባቸው፤ አሥራ ሁለት ገጽ በደፍረት የተሞላ የውግዘት መግለጫ አወጡባቸው። አሁንም በማኅበረ ቅዱሳን የሚደርስባቸው ወንጀላና ስም ማጥፋት አልተገታም። ከዚህ በከፋ እና በሚያሳዝን መልኩ በስደት ያሉትን አባቶች ከፓለቲካ ተቃዋሚ ጎራ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የወያኔ መንግሥትን ለማስደሰት አንደበተ ደፋር የሆኑትን ማለትም እርማት ሳይደረግባቸው ያደጉትን በቤተ ክርስቲያን ስም አሰልጥነው በማሰማራት፤ በካሴት እያሳተሙ ስማቸውን ከማጥፋቸውም በላይ እጅግ በሚያሳዝን እና በሚዘገንንን መልኩ እግዚ አብሔር አቡነ መርቆሬዎስን እንደተቀየመ፤ አቡነ ጳውሎስን እንደመረጠ። አፄ ቴዎድሮስን  እንደተቀየመ ንጉሥ ምኒልክን እንደመረጠ  አድርገው ተአምረ ማርያም አሳትሞ እስከ ማሰራጨት ድረስ በሃይማኖት የተሸፈነ ቃላት ገልጾ ሊጨርሰው የማይችል ከፍተኛ ተንኮል ሸፍጥ  ሲፈጽም ቆይቷል። ይህ መሰሪ ተግባር በሌላ አቅጣጫ ውስጥ ውስጡን በተቃዋሚ በኩል ጽምጹን አጥፍቶ ሰርጎና ዘልቆ በመግባት እና ካድሬዎቹን ቤተ ክርስቲያን የማታውቃቸውን ምልምል በሰባኪ ወንጌልነት በማሰማራት ከሚያካሄደውን ከፍተኛ ሥውር የሆነ ፓለቲካዊ ንግድ በተጨማሪ በተቃዋሚዎች በኩልም መሀል ሰፋሪ በመሆን የሚፈጽመው ሴራ እንዳይጋለጥ ሃይማኖታዊ መሰል አንደበቱ ሸፍኖለት እንዲቆይ ትልቅ እድል  እድል ሰጥቶት ቆይቷል። አቶ ኤርምያስ የሚባል  አሁን በኢሳት ቴሌቭዝን የሥራ ባልደረባ የሆነ ጎልማሳ፤ ቀደሞ ሲል የወያኔ ባለሥልጣን በዳንኤል ክብረት ወያኒያዊነት ላያ ማውጣት የጀመረው ምስጢር  መቶ በምቶ ትክክል መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ፤ ዳንኤል ክብረትን በደፋር አንደበተኝነት በቀዳሚነት ይጠቀሰ እንጅ፤ ሴራው ግን ሁሉንም የማኅበረ ቅዱሳን በተለይም አመራር አካላት በሙሉ የሚመለከት የወያኔዊነት ተግባር መሆኑን በቅድሚያ እናስገንዝበን ወደ ዜናው እናልፋለን። የአርዕስተ ዜናው ሀተታ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ከላይ በተጠቀሰው ማስገንዘቢያ መሠረትነት መጠነ ሰፊ ገንዘብ ዶላር  እየገዛ ከአካበተው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት  መካከል አንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን ዶላር አንድ የማሀል ሀገረ ተወላጅ በሆኑ ኢየሩሳሌም ድርጅት ኃላፊ ታምኝ ሰው አድርገው አስቀመጥው ነበር። ወያኔ በስውር በቅርብ እርቀት ሲጠብቀው የቆየውን ይኸው ዶላር ጠርቀም ማለቱን ሲያረጋግጥ፤  ይህ ግብር ያልተከፈለበት ዶላር ከየት መጣ ብሎ ይጠይቃል።  የኢየሩሳሌም ድርጅቱም ኃላፊም ገንዘቡ ከማኅበረ ቅዱሳን በኩል በአደራ የተቀመጠ ነው የእኛ አይደለም በማለት ያረጋግጣሉ። ማኀበረ ቅዱሳን ሲጠየቅ፤ ገንዘቡ የእኔ ነው በማለት ቃሉን ይሰጣል። ገንዘቡ ግብር ያልተከፍለበት ሕገወጥ ነው ሲባል፤ ገንዘቡ ግብር ያልተከፈለበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በመሆኑ ነው በማለት የእምነት ክህደት ቃላሉን  ይሰጣል። ወያኔም ሁሉን ነገር እንደማያውቅ ሆኖ፤ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ከሆነ ከቤተ ክርስቲያን ካዝናና ባንክ መቀመጥ አለበት እንጅ እዚህ ምን ያደርጋል የሚል ምክንያት ተጠቅሞ በስውር እየተንከባከበ ሲጠብቀው ሲያሳድገው የቆየውን ገንዘብ  ግብር ያልተከፈለበት ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ሕገ ወጥ ገንዘብ የሚል ስያሜ ሰጥቶ እንቅ አድርጎ ይይዛል። ማኅበረ ቅዱሳን የሚገባበት ቀድዳ ይጠፈዋል። የመጨረሻ አማራጭ ሲያጣ አቤቱታውን ለብፁዕ ውቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ገንዘባችን ተያዘ ያድኑን የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ነው ብለው ይመስክሩ ብሎ እንደጠየቀ የደረሰን ዜና በስፋት ያትታል። ዜና ዘጋቢያችን እንዳቀናበረው እንደ አቡነ ጳውሎስ በስጦታ የማይደለሉት አማኙና ታምኙ ካህን ብፁዕ ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ እኔ ስትሰብስቡ አልነገራችሁኝ። ያላቸሁን ንብረት ለቤተ ክህነት አታሳውቁም። እሪፓርት አድርጋችሁ አታውቁም። ሒሳባችሁን አታስመረምሩም። እናንተ እኮ ከቤተ ክርስቲያን አቅም በላይ ናቸሁ። እኔ ከየት እንዳመጣችሁት የትስ ንዳስቀመጣችሁት አውቄ ነው  ዓይኔ ያላየውን እጄ ያልቆጠረውን ገንዝብ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ነው ማለት የምችለው። እኔ በዚህ ጉዳይ እጀን ጣልቃ አላስገባም፣ አንደበቴም አያልፍም ተውኝ እባካችሁ!  በማለት መልስ የሰጡ መሆናቸውን  የዜና ምንጫችን  አጥናክሮ ያብራራል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ማኅበረ ቅዱሳን ከየአቅጣጫው የሚደርስበትን ነቀፌታ እያደገ የመጣ መሆኑን በመገንዘብ፤ ሃያ አምስ ዓመት ሙሉ በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም በእንቢተኝነት  ያካበተው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ  በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀበትና ገንዘብ በማን እጅ እንዳለ መጠኑ ምን ያህል ንደሆነ ገቢውና ወጪው የማይታውቅ ከመሆኑ አጻር በቅርቡ «ግብር የማያውቀው ሕገ ወጥ ገንዘብ» ነው ተብሎ የተወረሰበትን ገንዘብ ለመሸፈን ለ36ኛው የመጪው የጥቅምቱ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ በአቋራጭ እሪፓርት ማድረግ አለብኝ እያለ ቅዱስ ፓትርያርኩን መውጪያ መግቢያ እንዳሳጣቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ለቤተ ክህነቱ ቅርበት ያላቸው ኃላፊዎች መግለጫ እየሰጡን ነው። የዜና ምንጫችን አጠናክሮ  እንደዘገበው ማኅበረ ቅዱሳን ይህ እንዳይሰማበት  የውሽማ ሞት አድርጎት በከፍተኛ ምስጢር  ሲጠብቀው የቆየ ቢሆንም፤ ጉዳዩ ቀስበቀስ ሰው ጀሮ እየተዳረሰ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያዎችም እየደወሉ ሲጠይቁት በአውሮፓ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮቹን ጨምሮ በከፍተኛ ስብሰባ ላይ ተጠምዶ የቆየና ይህን ገንዘብ የሚሸፈንበት ሪፓርት አዘጋጅቶ በአቋረጭ ለማቅረብ ፓትርያርኩን ለሚመጣው 36ኛው የጥቅምት ጉባኤ ሪፓርት ማቅረብ ይፈቀድልኝ ብሎ ውጥር አድርጎ የያዘበት ምስጢሩ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሰራው ደባ እንዳይጋለጥ ባደረበት ከፍተኛ ሥጋት መሆኑን በአጽንዖት ያብራራሉ። ይህ የማይታመን እንግዳ ነገር መሆኑን  የተረዱት ቅዱስ  ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ፤ ሃያ አምስት ዓመት ሙሉ አንድም ሪፓርት ሳታስደርጉ፣ ምን ያህል የሚንቀሳቀስና ማይንቀሳቀስ  ንብረትና ተቀማጭ ገንዘብ እንዳላችሁ ሳታሳውቁ አሁን በድንገት ይህ ነገር እንዴት ለፈጠር ቻለ። ባላችሁበት ቆዩ ሕግ ይለየናል በማለት በቁጣ መልስ በምስጠታቸው ማኅበረ ቅዱሳን  ዘንድ የፓትርያርኩን ስም ማጥላላቱን በሰፉው የተያያዘው መሆኑን ለማወቅ ተችላል። አንዳንድ የቅርብ አዋቂዎች እንደሚሉት አሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ  በክፍተኛ ፍጥነት መቀሌ ውስጥ የተሰራው በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው ትልቁ የብረት ታውር መስቀል የተሠራው በዚሁ ግብር በማያውቀው ሕገወጥ ተብሎ በተያዘው በማኅበረ ቅዱሳን ዶላር   ወጪ ነው በማለት ሐሳባቸውን አጠናክረ ያቀርባሉ። የዜና ምንጫችን ይህን በሚመለከት ዝርዝር ሁኔታው ክትትል እየተደረገበት ስለሆነ ወደፊት በማስረጃ አስደግፈው በሰፊው አጠናክረው እንደሚያቀርቡልን ቃል ገብተዋል። ግብር ያልተከፈለበት ሕገ ወጥ ገንዝበ በመባል በወያኔ የተወረሰውን አንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን ዶላር የማኅበረ ቅዱሳን ገንዘብ አስመልክቶ መረጃው የደረሳቸው ነጻ የሚዲያዎች ፤ ለአማራሩ ከፍተኛ አካላት እየደወሉ መግለጫ እንዲሰጡ ቢጠየቁም.፤ መግለጫ እንድንሰጥ በዋናው የማኅበሩ ሊቀመንበር ካልተፈቀደልን በስተቀር ይህን በሚመለከት ምንም መግለጫ ለመስጠት ፈቅደኛ አደለንም በማለት መልስ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ አርቶኦድክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም የሰበሰበው የሚንቀሳቅስና የማይንቀሳቅስ ገንዝብ በሙሉ ከቤተ ክርስቲያኗ ከአብርኳ የተገኘ ከጎተራዋ የወጣ እንደመሆኑ መጠን አንድ በአንድ ተቆጥሮ ለቤተ ክርስቲያን ካዝና በሕጋዊ መንግድ ገቢ መሆን አለበት፤ ማህበሩም በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓትን ጠብቆ የቅዱስ ሲኖድስን መመሪያ አክብሮ መመራት አለበት የሚሉ የሊቃነ ጳጳሳት የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎችና ጽሐፊዎችን ያቀፈ አካል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን በመደገፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ ለቤተ ክርስቲያን ቅርበት ያላቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ዝርዝር መግለጫ እየሰጡ መሆናቸው ተረጋግጧል ማህበረ ቅዱሳንም  የዚህ ሥጋት እንዳጋጠመው ታውቛል። የአድባራትና የግዳማት አስተዳዳሪዎች በየጊዜዎ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በቅዱስ ፓትርያርኩ ሰብሳቢነት በሚደረገው አጠቃላይ ስብሰባ፤ በማኅበረ ቅዱሳና ሕገወጥ ጣልቃ ገብነት መከፋፈልና ልዩነትን በማስፋት ከፍተኛ  ደረጃ ለመፈሳዊ የአስተዳደር ሰላማዊ አሠራር ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን በምሬት በሰፊው ሲገልጹ የቆዩ መሆናቸው  በሁሉም ዘንድ የሚታውቅ ነው። አስተዳዳሪዎቹ ማኅበረ ቅዱሳን በሚያዝባቸው ድህረ ገጾች ወይም ዌብ ሳይቶች እንደ ሀራ ዘተዋህዶ፣ ደጀ ሰላምና የመሳሰሉት በማህበሩ ውስጥ ያልታረመና ያልተገራ አንደበት ባላቸው ጋጠወጥ አባልቱና ግለሰቦች ያለስማቸው ስም እየሰጡ የሚደርስባቸው ስም ማጥፋትና ስድብ ሃይማኖታቸውን የሚፈታተን ሰቆቃ እንዳደረሰባቸው  በከፍተኛ ሀዘኔታ ሲያቀርቡ እንደቆዩ በሁሉም ዘንድ የሚታወስ እወነት ነው። የዕለቱ በማኅበረ ቅዱሳን ዙሪያ የተጠናከረው የዜና ሀተታ በዚህ አበቃ። ከዚህ ጋር በተያያዙ ሌሎች ዝርዝር ዜናዎችን በሚደርሱን ተጭባጭ ማስረጃዎችና የዜና ምንጮች ላይ ተመሥርተን ሁኔታውን እየተከታተልን አጠናክረን በመዘገብ ይዘን እንቀባለን።

 

October 1, 2017 11:43

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያን ለማታውቀው ገንዘብ ምስክር አልሆንም አሉ፤
የመቀሌው ታላቁ ታወር መስቀል ከማኅበረ ቅዱሳን በተገኘው «ግብር በማያውቀው ሕገወጥ ገንዘብ» ወጪ እደተሠራ ተነገረ፤

ማኅበረ ቅዱሳን ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ የሒሳብ ሪፓርት ማድረግ አለብኝ በማለት ፓትርያርኩን እየተማጸነ ነው፤ ማኅበሩ ጥፋቱን ለመሸፍን የፈጠረው ስልት በሚል ተቀባይነት አላገኘም፤

ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ስም ያካበተውን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ገንዘብና ንብረት ወደ ሕጋዊ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ሶርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካዝና እንዲመልስ ፓትርያርኩን መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ሊቃነ ጳጳሳትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች በከፍተኛ ደረጃ እየመከሩበት መሆኑ ተሰማ።

ቅድሚያ ማስገንዘቢያ፤

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  የእምነት ሥርዓት ውስጥ ማኅበር ማለት  ከእምነት ጋር  በተቆራኘ በመንፈሳዊ  በበጎ አዳራጎት፣ ለመረዳዳትና ለመተሳሰብ፣ እንዲሁም ሰላማዊ ግኑኝነት ለምፍጠር በቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ስም የጽዋ ማኅበራትና ክርስቲያናዊ ዕድሮች እየተቋቋሙ፣ ምዕመናን ይሰባሰቡበታል። የማኅበራቱ የአባላት ቁጥር እየበዛ ሲሄድ አቅማቸው እየጠነከረ ሲመጣ በተሰባሰቡበት ቅዱስ ስም የቤተ ክህርስቲያን ሕግ እና ሥራዓት በሚፈቅደው መሠረት በአጥቢያ ደረጃ  አቢያተ ክርስቲያናት በማቋቋም የአቢያተ ክርስቲያናት መሠረት ጌጥና ውበት ሆነው ሲኖር ዘመናት ተቆጥረዋል። ወጣቶችም እንደዚሁ በአጥቢያው ሰበካ ጉባዔ እየተደራጁ ትምህርተ ወንጌል እያገኙ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው እንዲያድጉ ከመምሪያ ጀመሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በተዘረጋ መዋቅር ታቅፈው እንዲያድጉ በማድረግ ከሃምሳ ዓመት በላይ ሲሠራበት ቆይቷል።

በአጭሩ ማኅበራት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ አስተዳደር ሥር የሚተዳደሩና የሚመሩ የአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን አባላት በመሆን የሚያገለግሉ በካህናት የሚዘከር የሚባረክ የምዕመናን አንድነት የጽዋ ወይም የዕድር ማኅበር በመባል ይታወቃል። ከዚህ ውጭ የበላይ የበታች ከፍተኛ ዝቅተኛ የሚባል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላ ማኅበር አይታወቅም።

ቅዱስ ሲኖዶስና ከመንበረ ፓትርያርክ  ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ በየደረጃው በተቋቋሙ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የሀገረ ስብከትና የወረዳ ቤተ ክህነት መሥሪያ ቤቶች የሚያስተዳድሩት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናትን እንጅ ማኅበራትን አያስተዳድርም አያቋቁምም። ይህን በሚመለከት ያወጣችው የቤተ ክርስቲያን ሕግ የለም። ከሃያ አምስት ዓመት በፊት በነበረው የቤተ ክርስቲኗ ታሪካዊ ሐዋርያዊ ጉዞ እንደዚህ ዓይነት ተግባር አይታውቅም። በቤተ ክርስቲያን ሕግም ቅዱስ ሲኖዶስ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትን እንጅ፤ የጽዋ ማኅበራትንም ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸውን ማኅበራትን እያደራጀ እንዲያስተዳደር አልተደነገገምለት።

ማኅበረ ቅዱሳን እራሱን አደራጅቶና ፍጹም መንፈሳዊ መስሎ የገባው ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ጀምሮ  እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ በተዘረጋው መስመርና በትክክለኛ በር ሳይሆ የሲኖዶስ አባልቱን ከፍሎ የንስሐ አባት በማድረግ በመሰላልነት ወጥቶ በጉልላቱ በኩል እራሱ በእራሱ የመግቢያ ምስኮት ቀዶ የገባው ተቋም ነው። ይህን ኃይልና ጉልበት ለማግኘት ወጣቱን በሃይማኖት አሥሮ ያለአመጽ ይጠብቃል በሚል ከወያኔ መንግሥት በኩልም ድጋፍ አለው። ለዚህም ነው የመጀመሪያውን ኢግዚቢሽን እንዲያደግ ፈቅዶለት በ1985/86 ዓ.ም በአንድ ጊዜ የአሥራ አምስት ሚሊዮን ብር ገንዘብ ባለቤት እንዲሆን የተመቻቸ ሁኔታ የተፈጠረለት። ከዚህም በተጨማሪ ይህን ሕገወጥ ተግባሩን ሕጋዊ ለማስመሰል ማኅበሩ ከመፈጠሩ በፊት በ1982 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሕይዎተ ሥጋ የተለዩትን ታዋቂ አባቶች እነደነ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ያሉትን ስም በመጥቀስ ማኅበረ ቅዱሳንን አምጠው የወለዱ  እያለ  በስማቸው በመነገድ  የማሳመኛ ፓሮፓጋንዳ ሰርቷል።

ማኅበሩ ዛሬ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ በመምሪያ ሥር እተዳደራለሁ ይላል፤ አቅሙ ከመምሪያው በላይ አሥር እጥፍ ገዝፎ እና አልፎ ቅዱስ ሲኖዶስን ይገዳደራል። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶችን በመሰለል እንደ አስፈላጊነቱ እንደሚከተለው ከፋፍሎ ይቆጣጠራቸዋል፤

1ኛ/ ደጋፊዎቹን ሊቃነ ጳጳሳት ክንፍ ያውጡ የበቁ የጸደቁ ናቸው ብሎ በማምስገን በወዳሴ ከንቱ በመሳሪያነት ይጠቀምባቸዋል፤

2ኛ/ የሚቃወሙትን ሊቃነ ጳጳሳት ንስጥሮሳዊ፣ አርዮሳዊ፣ ተሐድሶ፣ አማሳኝ፣ቅባት እያለ ክብረ ነክ በሆነ መልኩ በእራሱ ሥልጣን ያወግዛል፤

3ኛ/ የጤና ችግር ያለባቸውን ሊቃነ ጳጳሳት የሕክምና ወጭ በማድረግ በገንዘብ ድጎማ እያታለለ ሳይውድ በግዳቸው ደጋፊው ያደርጋቸዋል፤

4ኛ/ የተወሰኑትን ሊቃነ ጳጳሳት ሀጥያት አለባችሁ ምስጢራችሁን እናውቃለን  ትጋለጣላችሁ እያለ ተቃውሞ እንዳያነሱ ጸጥ ረጭ በሉ እያለ አፋቸውን ለጉሞ ያስፈራራል።

5ኛ/ የተወሰኑትን ሊቃነ ጳጳሳት የጠሉትን በማኅበራዊ መገኛኛ /በሚድያ/ ስም አጥፊዎችን ቀጥሮ ሰለሚሰደብላቸው የማኅበሩ ጀሮ ጠቢ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሆነው የቅዱስ ሲኖዶስን እንዲሰልሉ አድርጎ በመያዝ በየዕለቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚተነፍሳትን ሁሉ ማታ ማታ እያናዘዘ አለዚያም በስብሰባ ወቅት ሥልካቸውን ከፍተው እንዲቀመጡ በማድረግ ስልኩን ጠልፎ በመያዝ ማንኛውንም የሲኖዶስ ውይይት ቀጭ ብሎ የሰማና በሐራ ዘተዋህዶ ድህረ ገጹ ለራሱ ፍጆታ በሚፈልገው መልኩ የሚያጸድቀውን አጽድቆ የሚኮንነውን አውግዞ አቀናጅቶ ያቀርባል። ሲኖዶስ በአሁኑ ስዓት የማኅበረ ቅዱሳን እስረኛ ነው።

ማኅበሩ ዚህ ዓይነት መንገድ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ከፍተኛ የአስተዳደር ችግር ሲፈጥር እንደቆየ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል። በአድባርትና ገድማት አስተዳዳሪዎችም  አመራር ላይ ችግር እየፈጠረ በከፍተኛ  ሰቆቃ እያማረሩ የቆዩ  ከመሆኑም በላይ በቅርቡ በአማሪካን የአማረኛ ድምጽ ሪዲዮ ቪኦኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በእውነት ላይ በተመሠረተ ከፍተኛ ትችት የደረሰበት ሲሆን፤ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰዎችን  በማንቃት ይህ ማኅበር ማን ነው? የሚለውን ጥያቄ እንዲያነሱ እንዲመረምሩ አስገድዷል።

ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ገቢ መሆን የሚችለውን ገንዘብም ስልጡን በሆነ በዘመናዊ ስልት በመጠቀም ለዘመናት በረቀቀ ምስጢር ደጋግ አባቶቻችን ሽንብራ እየቆረጠሙ ወገባቸውን አስረው በክብር ያቆዩትን ውድ  ቅርሶችን ማይክሮ ፊልም በማንሳት፣ ፎቶ ኮፕ በማድረግ፣ ሊቃውንቱን በትንሽ ድጎማ በማታለል ብዙ ቅጆችን በማባዛት፣ የቤተ ክርስቲያኗን ነባራዊ ታሪካዊ ሁኔታ በግሉ አለማንም ፈቃድ ኢግዚቢሽን በማሳየት፤

የሊቃውንቱን መጽሐፍ የቃላት ቁማር እየተጫወተ የእራሱ አስመስሎ  በአዲስ መልክ እያሳተመ በመሸጥ፤ የመካነ ቅዱሳን ጉብኝት ጉዞ በማዘጋጀትና በመሳሰሉት ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ነገር ግን ማንም ሊገባበት በማይችለው መልኩ በግሉ በብዙ ሚሊዮኖች  የሚቆጠር ከፍተኛ የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ገንዘብና ንብረት አካብቷል። ንብረቱ ከቤተ ክርስቲያን አብራክ በቤተ ክርስቲያን ስም የተሰብሰበ ቢሆንም ተቀማጭነቱ ቤተ ክርስቲያን በማታውቃቸው ባልወከለቻቸው ግለሰቦች ኃላፊነት ብቻ ነው።

ይህ ድርጅት በግሉ በየክፍለ ሀገራት ብዙ ማዕከላትን ከፍቶ ንግዶችን ያስፋፋል። ከሀገር ውጪ በአውሮፓና በአሜሪካ ጭምር ውስጥ ውስጡን ገለልተኛ የሚባሉትን ቤተ ክርስቲያን በማጠናከርና በመቆጣጠር የቤተ ክርስቲያንዋ ብቸኛ ባለቤት ለመሆን ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኝ ነው። በአሜሪካን ሀገር አሥራ አራት በሚደርሱ ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቀጥታ እጁ አለበት። በኢትዮጵያ አርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ የአስተዳደር  ሰንሰለትን በመጠቀም እራሱን በየደረጃው አዋቅሮ ማዕከላትን ከፍቶና ተስፋፍቶ ከወያኔ መንግሥት ጋር ተግባብቶና ተስማምቶ ለሃያ አምስት ዓመት በዋናነት የቤተ ክርስቲያኗን አካል መስሎ  ውጫዊና አፋዊ መንፈሳዊነትን አጉልቶ በማሳየት በነጭ አልባሳት አሸብርቆና ተሸፍኖ የእራሱን የንግድ መረብ ዘርግቶ ምንም ግብር ሳይከፍል የሚሠራ ነው። ዛሬ ጉልት ድንችና ሽንኩርት የመትሸጠው ድሃ ዜጋ ቆጥራው ያማታውቀውን ግብር እንድትከፍል ስትገደድ፤ ወያኔን በረቀቀ ስልት የሚያገለግለው ማህበሩ ከማኝኛውም ግብር ነጻ ነው። በቤተ ክርስቲያን ሀበትና ንብረት አራት ኪሎ በሚገኘው የማኅበሩ ሕንጻ ሰፊውን የሕንጻ ክፍል የሚጠቀምበት ወጋገን ባንክ የሚባለው የህውሀት የግል ባንክ ነው።

የቤተ ክርስቲያኒቱን ተከታይም በግሉ እየመለመለ አባል በማድረግ አሥራት በኩራት/ የአባልነት መዋጮ እያለ ያሰባስባል። ይህም በማወቅም ሆነ ባለማውቅ እያንዳንዱ አባል በሚኖርበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ኩባኤ አስተዳደር ማድረግ የሚገባውን የእምነት ግዴታ ሳልፎ በመስጠት የማኅበሩ ምርኮኛ ገባር ወርንዝና ጅረት ለመሆን ተገድዋል።

ወጣቶችን ማኅበሩ በዙ ሳይንቲስቶች ኢንጅነሮች ያሉበት ቅዱስ ማኅበር ነው። እያለ በማወጅ፤ አንዳንዶች ማኅበረ ቅዱሳን አባል መሆን ማለት፤ የተማሩ የተራቀቁ ማኅበር አካላት፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የታውቁ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የተላኩ ልቡሰ ሥጋ በምድር ላይ የተለቀቁ መልአእክት፤ በእምነት የተመረጡ ቅዱሳን  ከመሞታቸው በፊት ገነት መግባታቸውን ያረጋገጡ የሆኑ ስለሚመስላችው እራሳቸውን እያታለሉ የማኅበሩ አባላት በመሆን ሳያውቁት በቤተ ክርስቲያን ላይ ሕገ ወጥነትን በማዳበር ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያንን ያዳክማሉ።
ማኅበሩን የማይደግፉትን የአባቶችን ክብር ያዋርዳሉ። የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ያፋልሳል። ለመንፈሳዊ አስተዳደር እንቅፋት ይፈጥራል። የቀዱስ ሲኖድስ ውሳኔ ያዳክማል። የቤተ ክርስቲያን አባቶች ወደ እርቅ ወደ ሰላም እንዳይመጡ እንቅፋት ይፈጥራል። አገልጋዮች ካህናትን በጎሳ ይከፋፍላል ለችግርም ይዳርጋሉ። ወጣቶች በመፈሳዊ አብቶቻቸው ላይ አመጽና ድፈረት እተሞላው ባህሪ እንዲኖራቸው መጥፎ አርአያ ይሆናል።

ማኅበሩ ይህ  የተበላሸ  ሰይጣናዊ ዓላማው ጎልቶ እንዳይወጣበትና እንዳይታወቅበት ካሉት ስልጡን ስልቶች መካከል ጥቂቶቹና ዋናዎቹ የሚከትሉት ናቸው፤

1ኛ/ ቤተ ክርስቲያኗን የሚጠብቅ ከእግዘብሔር የተላክ ልዩ መልክተኛ የጻድቃን ሰማዕታቱ ልዩ ጠበቃ ትክክለኛ ፍጹም አማኝ አድርጎ እራሱን በመስበክ፤

2ኛ/ ያለባቸውን ደካማ ጎንና ችግር በማጥናት አንዳንድ ታዋቂ ሊቃውንትን በመጠነኛ ደጎማ በማግባባትና በማታለል፤ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አዋጅ ነጋሪ ነገር ቀማሪ አድርጎ በማጥመቅ፤

3ኛ/ በመንፈሳዊ  ዕውቀታቸው፣ በእምነት ብቃታቸው ጠንካራ የሆኑ ታዋቂ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር እራሱን በከፍተኛ ደረጃ በማስጠጋት ፍጹም አማኝ የቤተ ክርስቲያን መሠረት አድርጎ ማኅበረ ቅዱሳን ከሌለ ቤተክርስቲያን የለችም ብለው እንዲያውጁ ያግባባል ያስገድዳል፤ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ  በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው።

4ኛ/ አንዳ አንድ ታዋቂ መካነ ቅዱሳንና የታሪክ ቦታውችን እያጠና ከአካበተው ከፍተኛ ገንዘብ ላይ ትንሽ ምጽዋት እየሰጠ የራሱን ቅድስና አጉልቶ በማሳየት እራሱን በራሱ በማስተዋወቂያ ስርጭት በማጋነን በቤተ ክርስቲያን  በሬ ጠምዳ ባላረሰችው ይዞታዋ በሆነው ድንግል መሬቷ ላይ እያረሰ ምርቱን በልዮ በሆነ ምድራዊ ጎተራ በመዘገብ ኃይልና ጉልበት በማግኘት የቤተ ክርስቲያ ገዥ ለመሆን እይደፈረ ነው ። ለዚህ ነው ብፁዕ ውቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ «ቤተ ክርስቲያን በራሷገንዘብ በቅኝ ግዛት ቀነብር ውስጥ ተይዛለች» ያሉት።

ዛሬ የማኅበሩ በተለይም በአመራር ደረጃ ያሉት በሙሉ ከመንግሥት ሚኒስተር  መሥሪያ ቤት በምንስትር ደራጃ ካሉት የፓለቲካ ተቀጣሪዎች በላይ እንዲሁም ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሚያገኙት ደመወዝ የላቀ በከፍተኛ ደረጃ ደመወዝ የሚከፈላቸው ናቸው።  ይህም በልዩ ልዩ ምክንያት የሚከፈላቸን ሳይጨምር ነው። የማኅበሩ ከፍተኛ አመራር አባላት በሙሉ በአዲስ እባባ ከተማ ሠርተው የሚንደላቀቁባቸው ቪላዎች እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያላቸው ናቸው።

ይህ በንዲህ እንዳለ በቤተ ክርስቲያን ስም ከቤተ ክርስቲያን አብራክና ጉረሮ በየጊዜው እየሰበሰበ ከሚያገኘው ትርፍ ዶላር በመግዛት ሲያካብት የቆዩ ቢሆንም፤ የወያኔ መንግሥት የራሱን ታማኝ ሰላዩች አስቀምጦ ገንዘቡ ከየት እንደሚመጣ ወዴት እንደሚሄድ በቅርብ እርቀት ሲከታተልና ሲቆጣጠር ነበር። ማኅበሩም ባለሀብት ኢንቨስተር  እንደመሆኑ መጠን ይህ ንብረቱ እንዳይወሰድበት  ለመጠበቅ የወያኔ አንጋች አጎንባሽ ሆኖ ለሃያ አምስት ዓመታት አብረው ተስማምተውና ሰምና ወርቅ ሆነው ተደጋግፈው እስካሁን ዘልቀዋል።

ከፓትርያርኩ ጋር በተጣሉ ቁጥር በማኅበረ ቅዱሳን በኩል አማላጅ ሆነው የሚላኩት አቶ ካሣ ተክለ ብርሃን የሚባለው የወያኔ ሰው ነው። የቤተ ክህነቱ ሰዎች የማኅበረ ቅዱሳን ልዩ አባል በማለት ለአቶ ካሳ  ስም አውጥተውለታል። አቶ ካሳ ተክለብርሃን ሳይገባው በሆነ ባልሆነው  ምክንያት እየፈጠረ በቅድሱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መገኘት ወክሎ ለሚልከው  ለማኅበረ ቅዱሳን የነበረው ጥብቅና ወደር የለውም በማለት ውስጥ አዋቂዎች ይጠቁማሉ።  ለዚህ ነው ብፁዕ ወዱስ አቡነ ማትያስ  ፓትርያርክ የማኅበሩ አባል የሚሆኑት ሀበታሞች እየተመረጡ ነው። በማለት አጋድመው የተናገሩት።

ማህበረ ቅዱሳን በሃያ አምስት ዓመት ውስጥ አምስት ሚሊዮን  በላይ  የቤተ ክርስቲያኗ  እምነት ተከታይ ጠፍቷል ሲባል ድምጹን አላሰማም፤ ድምጹን ካሰማ ከመንግሥት ጋር ይጣላል፤ ሀብትና ንብረቱን ላይ አደጋ ይመጣል። የዋልድባ መነኮሳት መከራቸውን ሲያዩ ድምጹን አላሰማም፤ ድምፁን ካሰማ ከመንግሥት ጋር ይጣላል ሀብትና ንበረቱን ያጣል። በአደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ የወጣ ዜጋ ሕዝብ ሲገደል ማኅበረ ቅዱሳን ድምጹን አላሰማም፤ ድምፁን  ካሰማ ከመንግሥት ጋር ይጣላል  ሀብትና ንብረቱንም ያጣል።  በሰሜኑ ክፍል የወያኔ ወታደሮች አቢያተ ክርስቲያናትን ፈተሹ ታቦታትን በረበሩ ሲባል ማኅበረ ቅዱሳን ድምጹን አያሰማም ድምጹን የሚያሰማ ከሆነ  ያካበተወን ሀበትና ንብረቱን ያጣል። ታዲያ የማኅበረ ቅዱሳን ቅድስና የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪነት ክንፍ እስኪያውጣ መጠበቅ የእኛ ድርሻ  መሆኑ ነው።

የወያኔ መንግሥትም  በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የቅዱስ ሲኖዶስን ጩኽት እየሰማ የፓትርያርኩን ልቅሶ እያዳመጠ የዝሆ ጀሮ ይስጠኝ ብሎ  ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳንን በስውር ይከታተላለዋል ይጠብቀዋልም። ይህም የሆነበት ምክንያቱም ወጣቱን በሃይማኖት ስም አፍኖ« ነይ ነይ እምየ ማርያም» እያለ ሲያዘምረው ይወላል በሎ ስለሚያስብ ነው። አንዳንድ ማኅበረ ቅዱሳን ድጋፍ ያልተለያቸው  ሰባክያነ ወንጌልም በሀገር ውስጥ ብቻ  ሳይሆን በውጭ ሀገራት ጭምር እየተዘዋወሩ ይህን የሚያስፈጽሙ እንዳሉ መዘንጋት የለብንም።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳን ያለውን ንብረት እንዲያሳውቅ፣ የሒሳብ ምርምራ እንዲደረግ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲመራ፣ ደርጃውን ጠብቆ የሰንበት ትምህርት ቤት መምሪያ ታዛዥ ሆኖ እንዲሠራ፤ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ላይ ችግር እንዳይፈጥር፣ የቤተ ክርስቲያን ገቢ ሳይገባው እንዳይሰበሰብ፤ በቤተ ክርስቲያን ስም አላግባብ ተጠቃሚ መሆን እንዲያቆም ብለው ትዕዛዝ በመጻፋቸው ብቻ፤ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው እንደ አረማዊ ተፈርዶባቸው፤ አሥራ ሁለት ገጽ በደፍረት የተሞላ የውግዘት መግለጫ አወጡባቸው። አሁንም በማኅበረ ቅዱሳን የሚደርስባቸው ወንጀላና ስም ማጥፋት አልተገታም።

ከዚህ በከፋ እና በሚያሳዝን መልኩ በስደት ያሉትን አባቶች ከፓለቲካ ተቃዋሚ ጎራ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የወያኔ መንግሥትን ለማስደሰት አንደበተ ደፋር የሆኑትን ማለትም እርማት ሳይደረግባቸው ያደጉትን በቤተ ክርስቲያን ስም አሰልጥነው በማሰማራት፤ በካሴት እያሳተሙ ስማቸውን ከማጥፋቸውም በላይ እጅግ በሚያሳዝን እና በሚዘገንንን መልኩ እግዚ አብሔር አቡነ መርቆሬዎስን እንደተቀየመ፤ አቡነ ጳውሎስን እንደመረጠ። አፄ ቴዎድሮስን  እንደተቀየመ ንጉሥ ምኒልክን እንደመረጠ  አድርገው ተአምረ ማርያም አሳትሞ እስከ ማሰራጨት ድረስ በሃይማኖት የተሸፈነ ቃላት ገልጾ ሊጨርሰው የማይችል ከፍተኛ ተንኮል ሸፍጥ  ሲፈጽም ቆይቷል።

ይህ መሰሪ ተግባር በሌላ አቅጣጫ ውስጥ ውስጡን በተቃዋሚ በኩል ጽምጹን አጥፍቶ ሰርጎና ዘልቆ በመግባት እና ካድሬዎቹን ቤተ ክርስቲያን የማታውቃቸውን ምልምል በሰባኪ ወንጌልነት በማሰማራት ከሚያካሄደውን ከፍተኛ ሥውር የሆነ ፓለቲካዊ ንግድ በተጨማሪ በተቃዋሚዎች በኩልም መሀል ሰፋሪ በመሆን የሚፈጽመው ሴራ እንዳይጋለጥ ሃይማኖታዊ መሰል አንደበቱ ሸፍኖለት እንዲቆይ ትልቅ እድል  እድል ሰጥቶት ቆይቷል።

አቶ ኤርምያስ የሚባል  አሁን በኢሳት ቴሌቭዝን የሥራ ባልደረባ የሆነ ጎልማሳ፤ ቀደሞ ሲል የወያኔ ባለሥልጣን በዳንኤል ክብረት ወያኒያዊነት ላያ ማውጣት የጀመረው ምስጢር  መቶ በምቶ ትክክል መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ፤ ዳንኤል ክብረትን በደፋር አንደበተኝነት በቀዳሚነት ይጠቀሰ እንጅ፤ ሴራው ግን ሁሉንም የማኅበረ ቅዱሳን በተለይም አመራር አካላት በሙሉ የሚመለከት የወያኔዊነት ተግባር መሆኑን በቅድሚያ እናስገንዝበን ወደ ዜናው እናልፋለን።

የአርዕስተ ዜናው ሀተታ፤

ማኅበረ ቅዱሳን ከላይ በተጠቀሰው ማስገንዘቢያ መሠረትነት መጠነ ሰፊ ገንዘብ ዶላር  እየገዛ ከአካበተው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት  መካከል አንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን ዶላር አንድ የማሀል ሀገረ ተወላጅ በሆኑ ኢየሩሳሌም ድርጅት ኃላፊ ታምኝ ሰው አድርገው አስቀመጥው ነበር። ወያኔ በስውር በቅርብ እርቀት ሲጠብቀው የቆየውን ይኸው ዶላር ጠርቀም ማለቱን ሲያረጋግጥ፤  ይህ ግብር ያልተከፈለበት ዶላር ከየት መጣ ብሎ ይጠይቃል።  የኢየሩሳሌም ድርጅቱም ኃላፊም ገንዘቡ ከማኅበረ ቅዱሳን በኩል በአደራ የተቀመጠ ነው የእኛ አይደለም በማለት ያረጋግጣሉ። ማኀበረ ቅዱሳን ሲጠየቅ፤ ገንዘቡ የእኔ ነው በማለት ቃሉን ይሰጣል። ገንዘቡ ግብር ያልተከፍለበት ሕገወጥ ነው ሲባል፤ ገንዘቡ ግብር ያልተከፈለበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በመሆኑ ነው በማለት የእምነት ክህደት ቃላሉን  ይሰጣል። ወያኔም ሁሉን ነገር እንደማያውቅ ሆኖ፤ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ከሆነ ከቤተ ክርስቲያን ካዝናና ባንክ መቀመጥ አለበት እንጅ እዚህ ምን ያደርጋል የሚል ምክንያት ተጠቅሞ በስውር እየተንከባከበ ሲጠብቀው ሲያሳድገው የቆየውን ገንዘብ  ግብር ያልተከፈለበት ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ሕገ ወጥ ገንዘብ የሚል ስያሜ ሰጥቶ እንቅ አድርጎ ይይዛል። ማኅበረ ቅዱሳን የሚገባበት ቀድዳ ይጠፈዋል። የመጨረሻ አማራጭ ሲያጣ አቤቱታውን ለብፁዕ ውቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ገንዘባችን ተያዘ ያድኑን የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ነው ብለው ይመስክሩ ብሎ እንደጠየቀ የደረሰን ዜና በስፋት ያትታል።

ዜና ዘጋቢያችን እንዳቀናበረው እንደ አቡነ ጳውሎስ በስጦታ የማይደለሉት አማኙና ታምኙ ካህን ብፁዕ ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ እኔ ስትሰብስቡ አልነገራችሁኝ። ያላቸሁን ንብረት ለቤተ ክህነት አታሳውቁም። እሪፓርት አድርጋችሁ አታውቁም። ሒሳባችሁን አታስመረምሩም። እናንተ እኮ ከቤተ ክርስቲያን አቅም በላይ ናቸሁ። እኔ ከየት እንዳመጣችሁት የትስ ንዳስቀመጣችሁት አውቄ ነው  ዓይኔ ያላየውን እጄ ያልቆጠረውን ገንዝብ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ነው ማለት የምችለው። እኔ በዚህ ጉዳይ እጀን ጣልቃ አላስገባም፣ አንደበቴም አያልፍም ተውኝ እባካችሁ!  በማለት መልስ የሰጡ መሆናቸውን  የዜና ምንጫችን  አጥናክሮ ያብራራል ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ማኅበረ ቅዱሳን ከየአቅጣጫው የሚደርስበትን ነቀፌታ እያደገ የመጣ መሆኑን በመገንዘብ፤ ሃያ አምስ ዓመት ሙሉ በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም በእንቢተኝነት  ያካበተው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ  በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀበትና ገንዘብ በማን እጅ እንዳለ መጠኑ ምን ያህል ንደሆነ ገቢውና ወጪው የማይታውቅ ከመሆኑ አጻር በቅርቡ «ግብር የማያውቀው ሕገ ወጥ ገንዘብ» ነው ተብሎ የተወረሰበትን ገንዘብ ለመሸፈን ለ36ኛው የመጪው የጥቅምቱ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ በአቋራጭ እሪፓርት ማድረግ አለብኝ እያለ ቅዱስ ፓትርያርኩን መውጪያ መግቢያ እንዳሳጣቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ለቤተ ክህነቱ ቅርበት ያላቸው ኃላፊዎች መግለጫ እየሰጡን ነው።

የዜና ምንጫችን አጠናክሮ  እንደዘገበው ማኅበረ ቅዱሳን ይህ እንዳይሰማበት  የውሽማ ሞት አድርጎት በከፍተኛ ምስጢር  ሲጠብቀው የቆየ ቢሆንም፤ ጉዳዩ ቀስበቀስ ሰው ጀሮ እየተዳረሰ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያዎችም እየደወሉ ሲጠይቁት በአውሮፓ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮቹን ጨምሮ በከፍተኛ ስብሰባ ላይ ተጠምዶ የቆየና ይህን ገንዘብ የሚሸፈንበት ሪፓርት አዘጋጅቶ በአቋረጭ ለማቅረብ ፓትርያርኩን ለሚመጣው 36ኛው የጥቅምት ጉባኤ ሪፓርት ማቅረብ ይፈቀድልኝ ብሎ ውጥር አድርጎ የያዘበት ምስጢሩ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሰራው ደባ እንዳይጋለጥ ባደረበት ከፍተኛ ሥጋት መሆኑን በአጽንዖት ያብራራሉ።

ይህ የማይታመን እንግዳ ነገር መሆኑን  የተረዱት ቅዱስ  ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ፤ ሃያ አምስት ዓመት ሙሉ አንድም ሪፓርት ሳታስደርጉ፣ ምን ያህል የሚንቀሳቀስና ማይንቀሳቀስ  ንብረትና ተቀማጭ ገንዘብ እንዳላችሁ ሳታሳውቁ አሁን በድንገት ይህ ነገር እንዴት ለፈጠር ቻለ። ባላችሁበት ቆዩ ሕግ ይለየናል በማለት በቁጣ መልስ በምስጠታቸው ማኅበረ ቅዱሳን  ዘንድ የፓትርያርኩን ስም ማጥላላቱን በሰፉው የተያያዘው መሆኑን ለማወቅ ተችላል።

አንዳንድ የቅርብ አዋቂዎች እንደሚሉት አሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ  በክፍተኛ ፍጥነት መቀሌ ውስጥ የተሰራው በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው ትልቁ የብረት ታውር መስቀል የተሠራው በዚሁ ግብር በማያውቀው ሕገወጥ ተብሎ በተያዘው በማኅበረ ቅዱሳን ዶላር   ወጪ ነው በማለት ሐሳባቸውን አጠናክረ ያቀርባሉ። የዜና ምንጫችን ይህን በሚመለከት ዝርዝር ሁኔታው ክትትል እየተደረገበት ስለሆነ ወደፊት በማስረጃ አስደግፈው በሰፊው አጠናክረው እንደሚያቀርቡልን ቃል ገብተዋል።

ግብር ያልተከፈለበት ሕገ ወጥ ገንዝበ በመባል በወያኔ የተወረሰውን አንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን ዶላር የማኅበረ ቅዱሳን ገንዘብ አስመልክቶ መረጃው የደረሳቸው ነጻ የሚዲያዎች ፤ ለአማራሩ ከፍተኛ አካላት እየደወሉ መግለጫ እንዲሰጡ ቢጠየቁም.፤ መግለጫ እንድንሰጥ በዋናው የማኅበሩ ሊቀመንበር ካልተፈቀደልን በስተቀር ይህን በሚመለከት ምንም መግለጫ ለመስጠት ፈቅደኛ አደለንም በማለት መልስ ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ አርቶኦድክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም የሰበሰበው የሚንቀሳቅስና የማይንቀሳቅስ ገንዝብ በሙሉ ከቤተ ክርስቲያኗ ከአብርኳ የተገኘ ከጎተራዋ የወጣ እንደመሆኑ መጠን አንድ በአንድ ተቆጥሮ ለቤተ ክርስቲያን ካዝና በሕጋዊ መንግድ ገቢ መሆን አለበት፤ ማህበሩም በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓትን ጠብቆ የቅዱስ ሲኖድስን መመሪያ አክብሮ መመራት አለበት የሚሉ የሊቃነ ጳጳሳት የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎችና ጽሐፊዎችን ያቀፈ አካል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን በመደገፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ ለቤተ ክርስቲያን ቅርበት ያላቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ዝርዝር መግለጫ እየሰጡ መሆናቸው ተረጋግጧል ማህበረ ቅዱሳንም  የዚህ ሥጋት እንዳጋጠመው ታውቛል።

የአድባራትና የግዳማት አስተዳዳሪዎች በየጊዜዎ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በቅዱስ ፓትርያርኩ ሰብሳቢነት በሚደረገው አጠቃላይ ስብሰባ፤ በማኅበረ ቅዱሳና ሕገወጥ ጣልቃ ገብነት መከፋፈልና ልዩነትን በማስፋት ከፍተኛ  ደረጃ ለመፈሳዊ የአስተዳደር ሰላማዊ አሠራር ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን በምሬት በሰፊው ሲገልጹ የቆዩ መሆናቸው  በሁሉም ዘንድ የሚታውቅ ነው። አስተዳዳሪዎቹ ማኅበረ ቅዱሳን በሚያዝባቸው ድህረ ገጾች ወይም ዌብ ሳይቶች እንደ ሀራ ዘተዋህዶ፣ ደጀ ሰላምና የመሳሰሉት በማህበሩ ውስጥ ያልታረመና ያልተገራ አንደበት ባላቸው ጋጠወጥ አባልቱና ግለሰቦች ያለስማቸው ስም እየሰጡ የሚደርስባቸው ስም ማጥፋትና ስድብ ሃይማኖታቸውን የሚፈታተን ሰቆቃ እንዳደረሰባቸው  በከፍተኛ ሀዘኔታ ሲያቀርቡ እንደቆዩ በሁሉም ዘንድ የሚታወስ እወነት ነው። የዕለቱ በማኅበረ ቅዱሳን ዙሪያ የተጠናከረው የዜና ሀተታ በዚህ አበቃ።
ከዚህ ጋር በተያያዙ ሌሎች ዝርዝር ዜናዎችን በሚደርሱን ተጭባጭ ማስረጃዎችና የዜና ምንጮች ላይ ተመሥርተን ሁኔታውን እየተከታተልን አጠናክረን በመዘገብ ይዘን እንቀባለን።