የተማሪዎቹ ውሎና አዳር

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪዎችየባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪየባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪዎች ምሽቱን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪአጭር የምስል መግለጫየባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪዎች ምሽቱን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪዎች ዛሬም አዲስ ነገር የለም ይላሉ። የተቋሙ አመራሮችም የተቀየረ ነገር የለም ብለዋል።

ዛሬ በስልክ ያነጋገርናቸው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች በሃገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ጥያቄያችን ምላሽ እንዳገኘ ተደርጎ እንደተዘገበው ሳይሆን ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም፤ ከዩኒቨርሲቲውም በኩል የሰማነው የለም ብለዋል።

ትናንት በሰራነው ዘገባ ላይ ያነጋገርናቸው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ንጉስ ጋቢዬ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨውን ዜና እንደተመለከቱት ነገር ግን በዩኒቨርሲቲው በኩል እስካሁን ድረስ ምንም የተለወጠ ነገር እንደሌለ ነግረውናል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ1400 በላይ ተማሪዎችን ከግቢው አስወጣ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪዎችየባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪተማሪዎቹ ውሎ እና አዳራችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ይላሉ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪአጭር የምስል መግለጫተማሪዎቹ ውሎ እና አዳራችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ይላሉ

የተማሪዎቹ ውሎ እና አዳር

ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ከወጡ ሦስት ቀናትን ያሳለፉት ተማሪዎች አብዛኞቹ አዳራቸውን በቤተክርሰቲያን ግቢ ውስጥ አድርገዋል።

ተማሪዎቹ እንደነገሩን ብዙዎቻችን ማክሰኞ ምሽትን በጊዮርጊስ ቤተክርሰቲያ ግቢ ውስጥ እና አዳራሽ ውስጥ ሸራ አንጥፈን በመተኛት ነው ያሳለፈነውብለዋል። አቅም ያለው ተማሪ አልጋ ተከራይቶ፣ ሌሎች ደግሞ በከተማው ነዋሪዎች ቤት እና በዩኒቨርሲቲ መምህራን ቤት ተጠልለው እንደሚገኙ ነገርውናል።

የከተማው ነዋሪዎች ምግብ ሲያዘጋጁየባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪየከተማው ነዋሪዎች ምግብ ሲያዘጋጁ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪአጭር የምስል መግለጫየከተማው ነዋሪዎች ምግብ ሲያዘጋጁ

በምግብ በኩልም የከተማዋ ነዋሪዎች የገንዘብ መዋጮ አሰባስበው በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦችን በማስተባበር እያበሰሉ እየመገቧቸው መሆኑን ተናግረዋል።

BBC