ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ውጥንቅጡ ወጥቷል ።

የዮኒቨርስቲው ፕሬዝዳንቱ በሙስና ወንጀል ተጠርጥሯል ተብሎ በስብሰባ ላይ ቢነሳም መፍትሄ ማግኘት አልተቻለም በዚህ የሙስና ተግባር ላይ የጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለማሪያም ደስለኝ ወንድም እጅ አለበት የሚሉ ተጨባጭ ማስረጃዋች እንዳሉና ዮኒቨርስቲው ጊቢ ግን በሙስና ወንጀል ተጨመላልቋል ተብሎ ይሄ ነገር እንደ ሀሳብ በሰራተኞች ቀርቦል ነገሩን ግን አደባብሰውት አልፈዋል እናም በአሁኑ ወቅት በሁለት ግሩፕ በሙከፈል በውስጥ ሽኩቻ የአረካ_ልጆች እና የቦዲት_ልጆች ተብሎ የስልጣን ክፍፍል እየተደረገ ሲሉ የመረጃ ምንጮቼ ጠቁመውኛል

አዲስ የተሾመው ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሚ የፕሬዝዳንቱ ጥላት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ዶ/ር ሰንበቴ ቱማ እሱንም በሙስና አፍን እንዲዘጋ አድርጎታል ሲሉ ትዝብታቸውን ይገልጣሉ ሁኔታው ወደ አልሆነ አቅጣጫ በማምራት የሌላ ሀገር ተወላጅ የሆኑ የየኢትዮጵያ ልጆች ላይም ጥቃቱ ቀጥሎ እናንተ መጤ ናችሁ ሎካል አይደላችሁም እየተባለ ከስልጣን እያወረዷቸው መሆኑን ምንጫችን ገልጠዋል ።

ይህ_በእንዲህ_እንዳለ

በሙስናው ዶ/ር ሰንበቴ እና ግብራበሮቹ 2 መቶ ሺህ ብር የተረጋገጠ ሲወስዲ ለተባበራቸው ለአስደዳደር ሰራተኛው ለአቶ ወጣቱ …50 ሺህ ብር ቢሰጡትም አልቀበልም እግዚአብሔር አይፈቅደውም ብለው እንደመለሰ በስብሰባው ላይ እራሳቸው ምስክርነት ሰጥቷል

በዮኒበርስቲው ውስጥ ያለው ሽኩቻ እንደቀጠለ ሲሆን 204 አራት የሚሆኑ መምህራንና የአስተዳድር ሰራተኞች በስብሰባ ላይ አልተገኛችሁም በማለት እስከዛሬ ደሞዝ አለመሰጡትንም ጭምር አስረድተዋል