ከይድነቃቸው ከበደ

አሁን ላይ ያልተወደደልህን “ተሳስተሃል የተባልከውን ሃሳብ “ብቻ ሣይሆን፤ የትላንትናው ትክክለኝነትህን እና ብዙዎቻችን የምንወድልህ “ሃሳብ” አሁንም አስታውሳለሁ ፣ ነገም ቢሆን እንደዛው ። ምን ይሄ ብቻ ፤ በአንድ ጉዳይ ላይ በሚኖር አመለካከት ወይም እይታ ብቻ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መመዘኛ አድርጌ ፤ የነገ የአንተነት የብዙ ነገር መገለጫ በማድረግ ” በፈቃዱ ማለት ይህ ነው በቃ ” ብዬ በአንተ ላይ “ነብይ” ለመሆን በፍጹም አልደፍርም። የትላንት ማንነት ለዛሬ ምንነት መስታወትና የጥንካሬ ምርኩዝ እንደሚሆን በማመን ፤ ከስህተት ፈጥነ ለመታረም የዓላማ ስንክሳር’ን ቀድመ ለመገኘት የምትታታር እለህኛ እንደሆንክ ጭምር ብዙም አዳጋች የሆነ የአንተነትህ መገለጫ በህሪ እንደሌለ በቅርብ እርቀት እረዳለሁ ።

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

ወዳጄ! እስከዛሬ ያደረግከውን ጥረትና የከፈልከውን አስተዋፅዖ አርክሼ ፤ ‘’በቃ ለዚሁ ነው ይኽ ሁሉ መባከን?ለካ’ስ ለዚህ ነበር “በማለት አሁን ላይ በምታራምደው የግል ሃሳብ ወይም አቋም ፤ መነሻ በማድረግ “ተሳስተሃል የተባልከውን ሃሳብ “ብቻ ይዤ በአደባባይ የእኔ’ን ጉብዝና እንዲሁም ደፋር የወያኔ ተቃዋሚ ለመሆኔ “የአንተ የግል ሃሳብ ለእኔ ምክንያት ሆኖኝ ጀግና ልሁን አልልም ። በፍቄ አንተን “ወያኔ” በማለት ያለ-ሥራ ስም ሰጥቼ አንተን በማብጠልጠል እኔ ታማኝ ተቃዋሚ ለመባል ህሊናዬን አርክሼ በነውሬ አልዘባበትም። ስለምታነሳው ሃሳብ በቂ ግንዛቤ ሣይኖረኝ ፤ የእኔን ወዳጆች ወይም መህበርተኞች ስለደገፉ እና ስለተቃወሙ ብቻ ፤ እኔ አንተ’ን በማሞካሸት እና በማዋረድ የራሴን አላዋቂነት ከማሳወቅ ሌላ ፋይዳ በሌለው ነገር ላይ እንዲሁ አልኳትንም።


ወዳጄ በፍቄ ! እርግጥ ነው ሰው እንደመሆኑ መጠን ስህተት ሊኖርብ የችላል። በማናቸውም ጉዳይ ላይ የራስህ የግል አመለካከት እንደሚኖር እረዳለሁ ።ነገር ግን በይትኛው ጉዳይ ላይ ከማንም የተለየ የአንተ እውቅት ብቻ ትክክል የሚሆንበት ምንም ነገር እንደሌለ ጭምር በአግባብ እገነዘባለሁ።ወዳጄ ይህን ሰሞን ያነሳው ሀሳብ አንተ በተረዳህው መጠን ወይም በምትፈልገው ልክህ፤ የግለሰብ የሃሳብ ነፃነት ዋንኛ መርህ መሠረተ አድርገ በማህበራዊ ድረገጽ ሃሳቡን አካፍለናል። ነገር ግን ያለ በቂ መረጃ እና ማስረጃ ብቁንጽል ማጣቀሽ የአንድን ማህበረሰብ ሐይማኖት፣ ባህል እና ቋንቋ የቀድሞ ነገር እንዲህ ነበረ ፤አሁን ደግሞ እንደዚህ ሆኖ በማለት ድምዳሜ ላይ መድረስ ወይም የራስ የሆነ መላምት ማስቀመጥ ፣ እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የውይይት መድረክ መክፈት በእኛ ሃገር ነባራዊ ሁኔታ እጅግ በጣም አደገኛ ነገር ነው። በተለይ አንተ ያነሳው ሃሳብ ከአፈታሪክ የዘለለ ወይም እንዲህ ነበር ተብሎ ከመነገሩ ባሻገር የነገሩን እርግጠኝነት የሚያሳይ መረጃም ሆነ ማስረጃ ለሃሳብ ድጋፍ ጠንካራ ሙርኩዝ አለበጀህም። የተደገፍከው ሙርኩዝ በራሱ የአሉሽ አሉሽ የግለሰቦች ምልከታ እንጂ በትክክል አሳማኝ መረጃ አይደለም ።ለዚህም ነው አብዛኛውን ሰው በአንተ ሃሳብ ቁጣውን የገለጸው !! እንደኔ እይታ ወደ አደባባይ ይዘነቻው የምንወጣቸው ሃሳቦች ጠንካራ ምክንያት ልናበጅላቸው እንደሚገባ
ከሰሞኑን የሆነው ነገር ጥሩ አመላካች እንደሆነ እረዳለሁ ። በነገር ላይ ለዚህም ምክንያት በመሆን ለብዙዎች ትምህርት የሚሆን ነገር በመፍጠር ሌላኛው መልካም አጋጣሚ ነው። እናም ወዳጄ ! ይዘኸው ለተነሳው ሃሳብ አይደለም ለሌላው አንተንም የማያስጥል ስስ ምክንያት ነው።

ወዳጄ በፍቄ ! ያነሳው ሃሳብ ብዙዎችን ቅር አሰኝቷ ፤ ለምን እና እንዴት በማለት እራስን በመጠየቅ ፤ ልጥያቄውም በእውነት እና በምክንያት ላይ የተመሰረተ ፤ ሁሌም በማይለይህ መልካም ባህሪ በመታገዝ ምላሽ መስጠት አለብ። አብዛኛውን ሰው ቅር ካሰኘው ጽሁፍ በኋላ “ግማሽ እንቶኔ” እና ሌሎችም…” በሚል በድጋሚ በገለጽከው ሃሳብ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ለደረሰብህ ” ስድብ፣ ሽሙጥ፣ ዘለፋ፣ ፈር የለቀቀ ትችትና ነቀፋ፣ እንዲሁም ስም ማጥፋት…” የሰው ሰውኛ ባህሪ ገፍቶ ለእነዚኞቹ ምላሽ ሰጠ እንጂህ፤ በዋናነት ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነውን ቁም ነገር አውቀ ዘንግተዋል ! አሁንም ቢሆን ከአንተ ተገቢውን ምላሽ ይጠበቃል።በፍቄ እነዚህኞቹ ሰዎች ሣይሆን መመልከት ያለብህ ፣ከአንተ ጋር እውነተኛ የሃሳብ ፍትጊያ በማድረግ የተሻለ ሃሳብ እንዲመጣ የሚሹ ወገኖች እንዳሉ ጭምር ታሳቢ ማድረጉ አርቆ
አሰተዋይነት ጭምር ነው። አንተ እራስ “ለአገራችን አዎንታዊ ለውጥ ተስፋ እንዳላጣ የሚያደርጉኝ ቀና ሰዎች “አሉ ማለትህን አትዘንጋ፤ ስለነዚህ ሰዎች በማለት አሁንም ቀድመ ባነሳው ሀሳብ ዙሪያ ስድብ እና ሽሙጥን ወደጎን በመተው፣ የአንተ ሃሳብ ስህተት መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች እና ማስረጃቸውን በማጣቀስ ምላሽ የሱጡ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች አሉ፤ የእነሱ ምላሽ አስቀድሞ በነበረ እውቀት እና መረጃ ላይ ምን ያህል የጨመረልህ ነገር አለ ?! አዎ ! ተሳስቼ ነበር አሁን ግን በዚህ ፣ በእንደዚህ ምክንያት ያኛው ሃሳቤ ትክክል አልነበረም ለማለት የሚያስችል አመክንዮአዊ በሆነ መንገድ የአንተን ሃሳብ የሞገተ ወይም ውድቅ ያደረገ የለም ሆይ ?! ወዳጄ በፍቄ እነዚህን እና መሰል ነገሮች በአንተ በኩል ምላሽ ቢሰጥባቸው መልካም ነው። እዚህ ማህበራዊ ድረገጽ ላይ የምናነሳቸው ሃሳቦች ለእውቀት ሽግግር እንዲረዳን በአብዛኛውን ትክክል የሆነውን “ትክክል” እንዲሁም ስህተት የሆነውን “ስህተት” መባሉ ቢጠቅም እንጂ አይጎዳም!! ወዳጄ በፍቄ እጅግ በጣም የወደድኩል ምን እንደሆነ ነግሪ ለዛሬ ላብቃ እሱም ምን መሰለህ “እምቢ፣ ዘር አልቆጥርም”


(ይድነቃቸው ከበደ)

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!