October 4, 2017 21:24

“#የአማራ_ህዝብ_ታሪክ ከጥንት እስከ ዛሬ” በሚል በ2000 ዓ.ም በፕሮፌሰር ባየ ይማም የተፃፈውን መፅሀፍና “#በመንግስት እገዳ ሳይታተም ቀረ” የሚባለውን ይህንን ረቂቅ ለማግኘት በትንሹ ወራቶች ፈጅተውብኛል።
በአንድ ሚስጥር አዋቂ ወዳጀ ጥቆማ ፍለጋየን ተያይዠ እኔም መጨረሻ ተሳካልኝ።መፅሀፉ ባለ 190 ገፅ ገደማ ነው።ሙሉውን አላነበብኩትም።PDFም ስላልሆነ አንዳንድ ገፆችን ሊከፍትልኝ አልቻለም።ያም ሆኖ ግን የገናናውን የአማራ ህዝብና የአማራ አገር ታሪክ አሁን ከመፅሀፉ ውስጥ አለፍ አለፍ እያደረግኩ ሳነበው ውስጤ በደስታ እየተሞላ ወዘ ልውጥ ስሜት መላ አካላቴን እየወረረው ነው።ምክንያቴ ደግሞ በዝቅተኝነት ስሜት የሚሰቃዩ አካላት አማራው ላይ ለካ ወደው አይደለም ፊጥ የሚሉት ገናናው አማራ ውስጥ ባለመፈጠራቸው እንጅ የሚል ድምዳሜ በመደረሴ ነው።ስንቱ አማራ ላይ አፉን ይከፍታል መሰላችሁ።መልሱ ግን ቀላል ነው።
ለማንኛውም ከመፅሀፉ መግበያ ልቀንጭብላችሁ
“….ኢትዮጵያ የብሄሮች ሙዚየም እንደሆነች ተደጋግሞ ይነገራል።ብሄረሰቦቹ ሴማዊ፣ኩሻዊ፣ኦሞአዊ እና አባይ ሰሀራዊ ተብለው በአራት ይመደባሉ።በዚህ በዋናነት ቋንቋ እና መልከአምድራዊ አሰፋፈርን መሰረት ባደረገው አመዳደብ መሰረት አማራ አንዱ ነው።
የሚናገረው #ቋንቋ በስነ ልሳናዊ ባህሪው ሴማዊ፣ራሱን የቻለና ከሌሎች የሴም ቋንቋዎች የተለየ ሆኖ መነገር የጀመረው በበሽሎና በጀማ ወንዝ መካከል በሚገኘናን ዛሬ #ቤተ_አምሃራ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ እንደሆነ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ።ዘመኑም ወደ #ሰባተኛው መቶ ክፍለዘመን እንደሆነ ይገመታል።አማራው በአማርኛ ተናጋሪነቱ ተለይቶ የታወቀው በዚህ ዘመን ነው።ከዚያ በፊት አልነበረም ማለት ግን አይቻልም።ሌላ ቋንቋ ሲናገር ኖሮ ከጊዜ በኋላ አማርኛ ተናጋሪ እየሆነ የመጣ ህዝብ ነው ማለት ይቻላል።
የታሪክና የስነ ሰብ ተመራማሪዎች እንደሚያምኑት ከላይ የተጠቀሰው የበሽሎና የጀማ አካባቢ፣ ከዚያም አልፎ የዛሬው የሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በአብዛኛው አገውኛ የሚናገሩ ህዝቦች ይኖሩበት እንደነበር ይታመናል፡፡ የሴም ቋንቋ የሚናገሩ ሌሎች ወገኖች ወደዚሁ አካባቢ በመምጣት ከህዝቡ ጋር አብረው መኖር ይጀምራሉ፡፡ የሚናገሩት ቋንቋ ለግዕዝ ቅርብ የሆነ ሌላ የሴም ቋንቋ እንደነበር ይታመናል፡፡ የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት የቋንቋና የባህል ቅርርብን እንዳስከተለና ሴማዊው ቋንቋ ከጊዜ ብዛት ጥንተ ባህሪውን እየተወ እንደሄደ ይታወቃል፡፡
በመጨረሻም ከጥንቱ መልኩ የተለየ ይሆንና በአካባቢው ስም አማርኛ ተብሎ መጠራት እንደጀመረ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ፡፡ ከዚህ በመነሳት ዛሬ አማርኛ ተናገሪ የሆነው ህዝብ #የጥንቱን የሴም ቋንቋ ይናገሩ የነበሩት ወገኖች እና #አማርኛ ተናጋሪ እየሆኑ የመጡት አገዎች ተወላጅ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ #ባጭር ቃል ዛሬ #አማራ ተብሎ የሚጠራው ህዝብ መሰረቱ #በከፊል #ሴማዊ በከፊል ደግሞ #ኩሻዊ ነው ብሎ ማጠቃለል ይቻላል፡፡
የቋንቋው ባህሪም ይህን ሁኔታ በግልፅ ያሳያል፡፡ ቃላዊ መሰረቱ ሴማዊ ይሁን እንጅ መዋቅራዊ ባህሪው ከሌሎች የሴም ቋንቋዎች የበለጠ ኩሻዊ ነው፡፡…..እያለ ይቀጥላል።
እና ይህንን ሳነብ ይህ ቅን ህዝብና መሪዎቹ ምን ያህል ታሪካቸው ተንሻፎና ተንጋዶ ለቀማኞች እንደተሰጠ ይህ ረቂቅ መፅሀፍ ማረጋገጫ ነው።
ያ ወዳጀ መፅሀፉ ለሚሊኒየሙ እንዲታተም አቅጣጫ ተሰጥቶ በምሁራኑ በጎ ፍላጎት መፃፉንና መጨረሻ ግን “የአማራ ህዝብ ታሪክ” የሚለው መፅሀፍ አይታተም ይልቁንም “የአማራ ህዝብ ባህልና ወግ” የሚለው ብቻ ይታተም መባሉን ነግሮኝ ነበር።እንዲታተም የተፈቀደው ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ይገኛል።እኔም በሰው በሰው ደርሶኛል።
የአማራ ህዝብ ታሪክ ጉዳይ ግን ለምን አይታተምም? የሚለው ጥያቄ መልሱ ከማን እንደሚገኝ ባላውቅም እኔ ግን የመፅሀፉ ባለቤትን በቅርብ የሚያውቃቸው ካገኘው ፈቃዳቸው ተጠይቆ የመፅሀፉን የህትመት ወጭ እንደሁኔታው ታይቶ ለመሸፈን ሙሉ ፈቃደኛ ነኝ።መፅሀፉም ቢቻል በነፃ መታደል አለበት ላልውለ።
ይህንን ሀሳብ ብዙ ሰው እንደሚያግዘኝም አምናለው።ለአማራ ህዝብ ላበረክተው ከምችለው አንፃር ይህ ብዙም አይደለም።
እኛ የአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመብን በደል ግን የበለጠ መረር እንድንል፤ የውስጥና የግል ስሜታችን እየተቆጣጠርን የጋራ አጀንዳ ላይ እንድንገናኝ የአማራ ህዝብ ጉዳይ ያስገደድናል።