አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲGETTY IMAGES

በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ኢትዮጵያዊ ዜግነት የለንም ብለው ስለሞሉ እስከ አሁን ድረስ ወደ ማንኛውም ዩኒቨርስቲ እንዳልተመደቡ በተለያዩ መገናኛብዙሃን መገለፁ ይታወሳል።

መንግሥት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የለኝም ብለው ለሞሉ ተማሪዎች በሃገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች የመመደብ ግዴታ የለብኝም ይላል።

በሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነትና የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤

ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌላቸው ተማሪዎች በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የመማር መብት የላቸውም፤ ኢትዮጵያዊ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው። የሌላ ሃገር ዜግነት ካላቸው ደግሞ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያሳይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ ይዞ መቅረብ ይኖርባቸዋልብለዋል፤ አቶ ረዲ ሽፋ።

የተማሪዎቹን ቅፅ በየትምህርት ቤቱ የተመደቡና ሶፍትዌሩን የተረዱ የመረጃና የቴክኖሎጂ ሙያ ያላቸው ሰዎች ናቸው የሚሞሉት፤ ያሉት አቶ ረዲ ቢሆንም ግን ተማሪው ማረጋገጥ አለበት ይላሉ።

ለዚህም ሲባል ተማሪዎች ልክ እንደተፈተኑ የሚፈልጉትን ዩኒቨርስቲና የትምህርት ዓይነት ምርጫ ይሞላሉ፤ ቀጥለውም ውጤታቸውን መሰረት አድርገው ምርጫቸውን የማስተካከል መብት አላቸው።

በእነዚህ ጊዜዎች ሁሉ የተሳሳቱ ነገሮች ካሉ ቅፁን የማስተካከል ዕድል ያለ ሲሆን፤ ይህ ሳይሆን ከቀረ ደግሞ ለሦስተኛ ጊዜ ቅሬታቸውን አቅርበው እንዲያስተካክሉ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊው ይናገራሉ።

ተማሪዎች ቅሬታዎቻቸውን ለኤጀንሲው ሰራተኞች ሲያቀርቡተማሪዎች ቅሬታዎቻቸውን ለኤጀንሲው ሰራተኞች ሲያቀርቡ

አቶ ረዲ ተማሪዎቹ ሆን ብለው ኢትዮጵያዊ ዜግነት የለኝም ብለው ይሞላሉ ብዬ አላምንም፤ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብለው ቢሞሉ መብታቸውን ነው የሚያጡትሲሉ ጉዳዩ ፖለቲካዊ አንድምታ እንደሌለው ያስረዳሉ።

ችግሩ በዜግነት ጉዳይ ብቻም ሳይሆን አይነ ስውር ሆነው እያሉ፤ ማየት እችላለሁ በሚለው የቅፁ ክፍል ላይ ከሞሉ ወይም ፆታቸውን ካሳሳቱ ማግኘት የሚገባቸውን የተለየ ጥቅምና መብት ያጣሉ።

ይህ ደግሞ በራሳቸው ምክንያት የተፈጠረ ስህተት ስለሚሆን የዩኒቨርስቲ ምርጫቸውን ላያገኙ ይችላሉ ሲሉ አቶ ረዲ ሽፋ ያስረዳሉ ።

የተለያዩ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ቅሬታቸውን ሲያቀርቡና የኤጀንሲው ሰራተኞችም ቅሬታቸውን ሲያስተናግዱ የቢቢሲ ዘጋቢ ተመልክቷል፤ ተማሪዎችና ወላጆችንም አነጋግሯል።

በጉራጌ ዞን ያበሩት ወልቅጤ በሚባለው ትምህርት ቤት የተፈተነችው ተማሪት ዘነበች ጌታቸው በስህተት ነው የሞላሁት። በዚሁ ምክንያት እንደማልመደብ ነግረውኝ ነበር፤ እኔም ነሐሴ 17/2009 .ም የይቅርታ ደብዳቤ ፅፌ ኢሜይል አደረግኩኝ።

ዛሬ ደግሞ በአካል መጥቼ ኢትዮጵያዊት መሆኔን የሚገልፅ መታወቅያዬን አቅርቤያለሁ። የራሴ ጥፋት ስለሆነ የመረጥኩት ዩኒቨርስቲና የትምህርት ክፍልን ባይሰጡኝ ምንም ማድረግ አልችልም።ስትል ለቢቢሲ ገልፃለች።

ሌላው ተማሪ የሱፍ ኑረዲን ቅፁ ላይ የኢትዮጵያ ዜግነት እንደሌለው ስለሞላ አልተመደበም ነበር። ዜግነቱ ጣልያናዊ ነው። ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ እናቴ ጣልያናዊት አባቴ ደግሞ ኢትዮጵያዊ። የውጭ ዜግነት ቢኖረኝም የመኖርያ ፈቃድ መታወቂያ አለኝ። የቅሬታ ቅፅ አስሞልተው የምፈልገው ዩኒቨርሲቲና የትምህርት ክፍል አስመርጠውኛልሲል ይናገራል።

ተማሪዎች ውጤት ሲመለከቱ

Image copyright

GETTY IMAGESትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑት ተማሪዎች የድጋፍ ደብዳቤ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስፅፈው በማቅረብ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ይመደባሉ። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ መረጃና ጥናት ዳይሬክቶሬት ለተማሪ የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤን በወቅቱ ይቀበሉ የነበሩት የኤጀንሲው ሰራተኞች ለቢቢሲ አሳይተዋል።

የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ ሃገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 270/1994 አንቀጽ 5(6) መሰረት የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በመጠቀም ረገድ በውጭ ዜጎች ላይ የተጣሉ የህግ፣ የመመሪያ ወይም የአሰራር ገደቦች በትውልድ ኢትዮጵያዊ በሆኑ የውጭ ዜጎች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆኑ በግልፅ ተደንግጓልሲል የድጋፍ ደብዳቤዉ ያትታል።

በዚህም መሰረት ተማሪው በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ መታወቂያ እና የተያያዥ ሰነዶች ቅጂዎችን አያይዘን መላካችንን እንገልፃለን በማለት ተማሪው መብቱን ማግኘት እንደሚኖርበት ያስገነዝባል።

ይህ ዓይነት ችግር በየዓመቱ እንደሚያጋጥምም ኤጀንሲው በተጨማሪ ይናገራል።

BBC