አዲስ መጽሐፍ

የገጽ ብዛት 457 2010 ዓ.ም

ደራሲ ጌታቸው ረዳ (2010 ዓ.ም)

                                                       

መግቢያ

26 አመት አላላውስ ብለው ጨምቀው የያዝዋት በኢትዮጵያ ገላ የተጠመጠሙት ከጫካ የወጡ አስደንጋጭ የደራጎን እባቦች፤ የመጨረሻውን መርዛቸው በመርጨት ላይ ናቸው። በደራጎኖቹ ላለመነደፍ ሁሉም በሩቅ እየሸሸ ነው። የገዳማት፤ የቤተክርስትያንና የመስጊዶቿ በሮች ሁሉ ተበረጋግደው በሚያሳዝን ሁኔታ አጋንንቶቹ ተቆጣጥሮዋቸዋል፤ ፈጣሪዋም አገር ጥሎ ሄዷል። አማልክቶቿም በብርቱ ሐዘን ላይ ተቀምጠዋል። በምናኔ የሚኖሩ ቅጠል እየበሉ ከእግዚአብሔር ጋር በፀሎት የሚገናኙ የገዳማት አንስት መኖክሲቶች በአጋንንቶቹ መደፈራቸው ነግረውናል። አግዚኦ ተሳሃለነ!!

ላለመሞት ትንፈራገጣለች፤ ደራጎኖቹ ግን አልለቅ ብለው ጨምቀው ሊገድልዋት ይታገላሉ። ልጆቿ ከአጽናፍ አጽናፍ ተደናግጠዋል። አንዳንዶቻችን ከተመደብንበት ከመከላከያው የቀጠና ሰረገላ ወርደናል። ምን እየተደረገ እንደሆነም አናውቅም። አገራችን ጊዜ በሰጣቸው ትግሬዎች እየታመሰች ነች። እናቶቻችን፤ እህቶቻችን፤ ወንድሞቻችን፤ ዜጎቻችን ተደፍረዋል። ደጋግ ሰዎች ያለማቋረጥ ወደ ጭለማ ክፍል እየተገፈተሩ ነው። ይሙቱ ይታሰሩ ይደብደቡ ይዋረዱ እኛን አስካልነካን ጉዳያችን አይመስልም። ለማወቅም ፍላጎት አላሳየንም። ነቢቦቻችን ተለቅመው ጠፍተዋል። የቀሩትም የማያፈሩ የበሰበሱ ዕጽዋት ሆነዋል። 26 አመት ሙሉ ‘ክፉም ሆነ ደግ ሰው መርዝ ሰጪ የሆነበት፤ እገሌ ከእገሌ ሳይባል ማንኛውም ሰው ማንነቱን የሚያጣበት፤ ሰው ሁሉ ቀስ በቀስ ራሱን መግደል የያዘበት አገር ተችሮልናል’። ሰዎች የመሆን ባሕሪ ጥለው ወደ ድራጎን እና አጋንንትነት የተለወጡት የትግራይ ወያኔዎች አገሪቷን እያስጨነቁዋት ናቸው።

ደራሲ ጌታቸው ረዳ

PDF ለማንበብ ይህን ይጫኑ ⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/10/አዲስ-መጽሐፍ-Getachew-Reda20171005.pdf