October 5, 2017

ቆንጅት ስጦታው

የአርበኛ መንግስቱ ወልደ ስላሴ የትግል ታሪክ – የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ)

የኢህአግ ታጋይ አርበኛች አስባሳቢ ኮሚቴ

በዶ/ር ብርሃኑ ትዕዛዝ በኤርትራ በርሃ ታስሮ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት የሚገኘው አርበኛ መንግስቱ ወልደ ስላሴ
አርበኛ መንግስቱ ወልደ ስላሴ በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ) 1995 .ም ጀምሮ ሲታገል የኖረ ታግሎ ያታገለ ቆራጥ እና ጀግና ውድ የአማራ ልጅ አርበኛ ታጋይ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በ2006 ጀምሮ ከግንቦት ሰባት ራስወዳድ አመራሮች ጋር በሚደረገው ግንኙነትና ውህደት ጉዳዮ በጥንቃቄ እንዲታይና ስምምነቱ የአንድ ወገን የበላይነት እንዳያሰፍን በጠንካራ አቋም ሲታገል የነበረ አባት አርበኛ ወንድማችን ነው።
አርበኛ መንግስቱ ወልደስላሴ በባለፈው አመት 2009 ጥቅምት ወር ከነ ዘመን ካሴ ጋር በጋራ በመሆን ራስ ወዳድና ብልጣብልጥ የግንቦት ሰባት አመራሮችን ከተግባር የራቀ የኢንተርኔት ትግል አያስፈልገንም በአሁኑ ሰሃት ህዝባችን አመጽ ላይ ነው ልንደርስለት ይገባል ብሎ የሞገተና የታገለ ጀግና የህዝብ ልጅ ነው። አርበኛ መንግስቱ ወልደስላሴ ከዚህ የጥቅምት ወር 2009 .ም ተቃውሞና ትግሉ በኋላ ነበር በግንቦት ሰባቶች ጥርስ ውስጥ የገባው ዘንዶውና የአማራ ህዝብ ጠላት የሆነው ራስ ወዳድ አንባገነኑ የኤርትራው በርሃ መሪ ብርሃኑ ነጋ አትመራንም እስከማለት ድረስ በጥብቅ የተቃወመ ያሰማ ጀግና አባት አርበኛ ነው። አርበኛ መንግስቱ በነበረው ጠንካራ አቋምና ህዝባዊ ወገንተኝነቱ ምክንያት አይንህን ላፈር ያለው የግንቦት ሰባት አጭበርባሪ ማፈያ ቡድን በዚሁ አመት ከፍተኛ የጤና መታወክ ደርሶበት አትታከምም ተብሎ በህመም ሲሰቃይ የቆየ ጀግና አርበኛ የህዝብ ልጅ ነው።

መንግስቱ ወልደ ስላሴ ከአቋሙ ፈቀቅ ሳይል ግንቦት ሰባት አመራሮች በሚያካሂድት ተንኮል የተሸረበበት ሴራ ስብሰባ ላይም ባለመካፈል ይታወሳል። አርበኛ መንግስቱ ወልደስላሴ በአግ7 ህዝብ ግንኙነትና በንቅናቄው ቃል አቀባይነት እንዲሁም በፓለቲካ ጉዳይና በከፈተኛ ወታደራዊ አዛዥነት ያገለገለ ወንድማችን ነው። አርበኛ መንግስቱ ወልደስላሴ መስከረም ወር ላይ ብርሃኑ አካሄድኩት ባለው የአግ7 ቅድመ ጉባየ ስብሰባና በጉባየው ወቅትም ከነማእዛው ጌጡና ከሌሎች ታጋይ አርበኛች ጋር በመሆን የኢህአግ ከግንቦት ሰባት ጋር መቀጠል እንደማይችል በግልጽ የተናገረና ሁሉም የኢህአግ ታጋዮችና አመራሮች ራሳቸው እንዲያገሉ የራሱን አቋም ይዞ የታገለ ጀግና አርበኛችን ነው። በአሁኑ ሰዓት ጸረ አማራ ህዝብና ራስ ወዳድ በሆነው ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ቀጥተኛ ትእዛዝ የድርጅታችን “ህገደንብ ጥሰሃል” በሚል ተልካሻ ሰበብ አሳስሮ በሃሬና እስር ቤት እያስቃየው ይገኛል፣ የመኖር ያለመኖሩም ጉዳይ ስጋት ገብቶናል። አርበኛ መንግስቱ ወልደስላሴን ከብርሃኑ ነጋ ጋር እንዲህ አይጥና ድመት አድርጎ አርበኛ መንግስቱን አሳድኖ ለስቃይ የዳረገው አቋሙ

            1. ግንቦት ሰባት በአማራ ታጋዮች ላይ ያለው ማግለልና መድሎ በመቃወሙ፣

  1. የግንቦት ሰባት የአንድ አካባቢ ሰዎችን ያማከለ አመራርነት ፍትሃዊ አይደለም በማለቱ፣
    3.
    በአርበኛች ግንባር አላማ መሰረት ትግሉ አርበኝነታዊ ትግል እንጅ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚደረግ ትግል አይደለም በማለቱ፣
    4.
    ትግል በአመራሩ መስዋትነት ተምሳሌት ሊደርግ ይገባዋል እንጅበኡንተርኔት የሚደረግ ውጊያም ሆነ ትእዛዝ አንቀበልም በማለቱ፣
    5.
    በአማራ ተወላጆች ላይ ያለው መገለልና መድሎ ይቁም የማናውቃቸውና ያላየናቸው የግንቦት ሰባት አመራሮች አይመሩንም በማለቱ፣
    6.
    ይህ ችግር ካልተፈታ ኢህአግ አርበኛች ግንባር ከግ7 ተለይቶ የራሱን ትግል በነበረበት ህብረ ቢሔራዊ የአንድነት ትግል ለመቀጠል ይገደዳል በማለቱ፣
    ይህ ውሳኔውና እርምጃው ያስፈራቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆቹ እነ ብርሃኑ ነጋ አርበኛ መንግስቱ ወልደስላሴን አሲረውና ሸርበው በእስርቤት እያስቃዮት ይገኛል።
    ከአርበኛ መንግስቱ ወልደስላሴን በተጨማሪም አርበኛ ክፈተው አሰፋ እና በተከታታይ ስም ዝርዝራቸውን የምናወጣቸው አርበኞች ከ15 አመት በላይ ህወሃትን ሰሜን ላይ እየተፋለሙ ወንድሞቻቸውን መስእዋትነት ከፍለው ትግሉን ያቆዮን ወንድሞቻችን ብርሃኑ ነጋ ከህወሃት ውድቀት በኋላ ዳግም የአማራን ህዝብ ረግጦና ጨፍጭፎ ለመግዛ ባወጣውና በነደፈው ፓሊሲው በአንድነት ስም ዳግም ህዝባችን ላይ መከራ አናመጣም በማለቱ አባት አርበኛቻችን በአሁኑ ስሃት ከሞት አፋፍ ላይ ናቸው።
    የኢህአግ ታጋይ አርበኛች አስባሳቢ ኮሚቴ
    መስከረም 24.01.2010..
    ሰሜን በርሃ