ሰንደቅ ዓላማ እና አገራዊ መግባባት?

 Saturday, 07 October 2017

ሰንደቅ ዓላማ እና አገራዊ መግባባት?

አለማየሁ አንበሴ

የዘንድሮው አሥረኛ የሰንደቅ አላማ ቀን ጥቅምት 6 ቀን 2010 .ም ይከበራል፡፡ የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ አማኑኤልአብርሃም ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤የዘንድሮ በአል “ራዕይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል” በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዋል።“የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ታሪክና የኢትዮጵያህዳሴ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሰነድም ላይ የፓናል

ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡“ሰንደቅ አላማውን የማክበር ጉዳይ የሁሉም ዜጎች ሃላፊነት ሊሆን ይገባል” ያሉት አቶ አማኑኤል፤ ሰንደቅ አላማን በተመለከተ ጉድለቶችና እጥረቶች ካሉ፣ እንዲፈቱ የማድረግ ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ ነው ብለዋል፡፡ የሰንደቅ አላማን ምንነትና ክብር በወጣቱ ዘንድ ለማስረፅ ዘንድሮ በት/ቤት በተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ የተሻለ ግንዛቤ ተፈጥሯል ያሉት አቶ አማኑኤል፤ከዚህ የበለጠ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያሻም ተናግረዋል፡፡የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ በተመለከተ በሶስት ንኡስ አንቀፆች የሚደነግገው የህገ መንግስት አንቀፅ 3 የመጀመሪያው ንኡስ አንቀፅ፤ “የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሃል ቢጫ፣ከታች ቀይ ሆኖ በመሃሉ ብሄራዊ አርማ ይኖረዋል”ይላል፡፡ መንግስት፤ ይህን የህገ መንግስቱን ድንጋጌ ለማስከበር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንቅስቃሴ እያደረገመሆኑም ተገልጧል፡፡
በአንፃሩ በሀገሪቱ ከሚታዩ ተቃውሞዎች ጋር በተገናኘ አርማ የሌለው ሰንደቅ አላማና ሌሎች የቀድሞ ዘመን ሰንደቅ ዓላማዎች በስፋት ሲውለበለቡ ይስተዋላል፡፡ ለመሆኑ በሰንደቅ አላማ ጉዳይ አገራዊ መግባባት ለመፍጠር ያልተቻለው ለምንድን ነው
? እንዴትስ ነው አገራዊ መግባባት መፍጠር የሚቻለው? ይህ አለመግባባት በሀገር አንድነት ላይ ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን?

የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤በሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ ላይ አንጋፋ ተቃዋሚፖለቲከኞችን አነጋግሮ ሃሳባቸውን እንደሚከተለው
አጠናቅሮታል፡፡ ለፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሄው ፖለቲካዊ ውይይት ነው፡፡_

PDF ለማንበብ ይሕን ይጫኑት⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/10/almayohe.pdf