October 8, 2017VOA Amharic News

“ግራ ቀኙን ያለውን ሁኔታ ስከታተለው ነበር። አሁን አገሪቱ የጭንቅ አማላጅ የምትፈልግበት ሰዓት ነው። በፖለቲካውም ጎራ ከዚህ ቀደም ያልተለመዱ ሁኔታዎች እያየን ነው።” ዲያቆን ዳንኤል ክብረት። “ኢትዮጵያ በጣም ፈታች ሁኔታ ላይ እንዳለች ይሰማኛል። የአለቃ አያሌውን ግግግር ተውሼ፣ መልህቋን የምትጥልበት አጥታ ማዕበል ከወዲህ ወዲያ በሚያላጋት በውል ለመለየት ከሚቸግር አደገኛ ሁኔታ ላይ እንዳለች ይሰማኛል።” አቶ ሃብታሙ አያሌው።

► ሙሉውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ

“የአገር ጉዳይ”… ተመልሶ መጥቷል። የአንድ አገርና ሕዝብ ፈተናዎች፥ የመውጫ መንገዶችና ተሥፋ።

ትላንትናችንን፥ ዛሬንና ነገን፤ መንታ መንገድ ላይ ያለች በምትመስለው ሃገር ሰሞንኛ ይዞታ ውስጥ የሚደረግ የሃሳብ ቅኝት ነው።

የራዲዮ መጽሔት ከዚህ ቀደም ይህን መሰል ሁኔታ ሲፈጠር በተለየ ትኩረት ያሰልስ እንዳደረገው ሁሉ አነጋጋሪ፥ አሳሳቢና ሁነኛ መላ ለሚሹት አንገብጋቢ የአገርና የሕዝብ ጉዳዮች ዛሬም የራዲዮ ገጾቹን ገልጧል።

በኢትዮጵያ ጉዳዮች የሚጽፉ፥ በተለያዩ መንገዶች በንቃት የሚሳተፉና በሚጠበቡባቸው የሞያ መስኮች ለብዙዎች ጥቅም የሚውሉ ሥራዎቻቸው የሚታወቁ፤ በአጭሩም የሕዝብ ጉዳይ ግድ የሚላቸውን የማኅበረሰብ አባላት ማነጋገሩን ቀጥለናል።

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ባተኮሩ ምሁራዊ ጽሁፎቹ በሥፋት የሚታወቀው መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው በርካታ መጽሃፍት ደራሲ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና በፖለቲካ ተሳትፎው ለበረታ እንግልት ቢዳረግም ዛሬም ከኢትዮጵያ ጉዳዮች ያልራቀው
የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ ይወያያሉ።

እርሶም የዚህ ተከታታይ ውይይት ተሳታፊ እንሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል። በያላችሁበት ከምታደርጉት ውይይት በተጨማሪ ለአገርና ለሕዝብ ይበጃሉ የምትሏቸውን አዎንታዊ ሃሳቦች አድርሱን።

ውይይቱን ከዚህ ያድምጡ