October 12, 2017 14:34

በእነ አንቶኔ ቤት በስርዓቱ ላይ አደጋ የሆነ ለውጥ በመጣ ቁጥር የመጀመሪያ ስራቸው ማጣጣል እና ስም ማጥፋት ነው። ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጥ ብአዴን ወይም ኢህዴድ እነሱ የማይፈልጉትን አቋም ካንፀባረቁ የፓርቲውን አቋም ማጣጣል፣ የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ስም ማጥፋት ይጀመራል።
ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በብአዴን እና በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ የተከፈተው የሰም ማጣፋት ዘመቻ ልብ ይሉዋል። ለምሳሌ ከሰሞኑ የጠ/ሚ “ፕሮቶኮል ኃላፊ አሜሪካ ሄደው ከዱ” ሲባል ግለሰቡን አንዴ” አትክልተኛ፥ ሻይ አፍይ፥ …ወዘተ” የስም ማጥፋት (character assassination) ዘመቻ ተከፈተባቸው። ኤርሚያስ ለገሰ ጥሏቸው ወደ አሜሪካ ሲኮበልል እነ ዘፅዓት አናኒያ “ድሮም እኮ የብአዴን ተላላኪ ነው” እያሉ ማሽሟጠጥ ጀመሩ። ከፍተኛ ባለስልጣናትን ቀርቶ ተራ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን ስም የሚያጠፉ ተራ ተሳዳቢዎችን በፌስቡክ እንዳሰማሩ ይታወቃል።

ሰሞኑን አባዱላ ገመዳ ከአፈ-ጉባዔነት በመውረዱ ምን እንዳሉ አልሰማሁም። ዛሬ በወሊሶ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ግን ሰልፈኞች ለአባዱላ ገመዳ እና ለአዲሱ የኦህዴድ አመራሮች አድናቆትና ድጋፋቸውን ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ሰልፈኞቹ ከዚህ ቀደም ያልተለመዱ መፈክሮች አሰምተዋል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የህወሓት/ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችን በስም እየጠሩ “የስኳር ሌባ!” ሲሉ ሰምቻለሁ። ከዚህ በተጨማሪ፣ “የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት “ወያኔ” እንጂ አማራ አይደለም!” የሚል ሰምቼያለሁ።

በዛሬው ዕለት በወሊሶ ከተማ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ (በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ ፊት ለፊት)
Editከሰዓት በኋላ ደግሞ እነአንቶኔ እንደተለመደው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትን ወሳኔዎች እና የተቃውሞ ሰልፉን በማጣጣል ላይ ተሰማርተዋል። በእርግጥ ገና ከጅምሩ ሲያጣጥሉት የነበረው ሕዝባዊ ንቅናቄ እንሆ ዛሬ ላይ እነሱን ሊጥላቸው ደርሷል። ነገር ግን፣ለምን ለውጥን እንደሚያጥላሉ እና የሰዎችን ስም እንደሚያጠፉ ፈፅሞ ሊገባኝ አልቻለም ነበር። ከፍተኛ መጠን ያለው ስኳር ያለ አግባብ ወደ ዉጪ መላኩ ያልገረማቸው ሰዎች “የስኳር ሌባ” እያለ የደረሱበት የሞራል ኪሳራ በይፋ ሲነገራቸው ከማፈር ይልቅ እውነቱን በማጣጣል የህዝቡን ሞራል ለመስለብ የሚያደርጉት ጥረት በጣም ይገርማል። በሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ተሰሚነት ተሟጥጦ ቢያልቅም የሌሎችን ስም ለማጥፋት እረፍት ማጣታቸው ግራ ያጋባል። “ኧረ እንደው ይሄ ነገር ስም ይኖረው ይሆን?” ጎግል ላይ “Moral Corruption and character assassination” የሚሉትን ቃላት ፅፌ ስፈልግ “The social Unconscious in Persons, Groups and Societies” በሚል ርዕስ የቀረበ አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ መጀመሪያ ላይ ወጣ። የሚከተለው አንቀፅ ከፅሁፉ ውስጥ የተወሰደ ነው፡-

“Moral Corruption and character assassination occurred frequently in a political and social groups in the totalitarian state… This process is created and reinforced fear of authority and the system, which is destructive to individual integrity and human dignity and forced the people into helplessness and compliance with the regime.” The social Unconscious in Persons, Groups and Societies, Vol. 2.

ከላይ የተጠቀሰውን ፅኁፍ እንዳነበብኩ “ለዚህ ነው ላከ!” አልኩ። በሙስና እና አድሏዊ አሰራር ውስጥ የተዘፈቀ ጨቋኝና አምባገነን የሆነ የፖለቲካ ቡድን እና ደጋፊዎች የሌሎችን እንቅስቃሴ በማጣጣል፥ በማጓጠጥ፥ በመሳደብ፥ በማስፈራራት እና የሰዎችን ስም በማጥፋት ላይ የተሰማሩት ለካስ ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ሆኖ ነው። ለካስ ዘወትር ጠዋት ማታ፣ ነገሮችን ሲያጥላሉና የሰው ስም ሲያጠፉ የሚውሉት የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ከድርጅቱ እንዳይወጡ ለማስፈራራት፣ ሕዝቡም የለውጥ እንቅስቃሴውን ተስፋ ቆርጦ እንዲተው ኖሯል።
እነዚህ ወገኖች የለውጥ እንቅስቃሴን የሚያጣጥሉት እና የግለሰቦችን ስም የሚያጠፉት ሕዝቡውን ተስፋ በማስቆረጥና በማስፈራራት ለጨቋኙ ስርዓት ተገዢ እንዲሆን ነው። ብደልና ጭቆናን ተቀብሎ እንዲኖር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስታዊ ስርዓቱ ጨቋኝና አምባገነን ስለመሆኑ ማረጋገጫ እየሰጡ ነው። ስለዚህ አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር ለማጣጣልና ለማንኳሰስ ሲጣደፉ ለምን እንደሚያደርጉት አውቆና ንቆ መተው ተገቢ ነው።
ችግሩ በአብዛኛው የሚስተዋል በህወሓት/ኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ነው። “ታዲያ ይህ አካሄድ ህወሓትን ያዋጣል ወይስ አያዋጣውም?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ እንደ ችግሩን እንደ መፈለግድ ከባድ አይደለም። አንድ የፖለቲካ ቡድን የለውጥና መሻሻል ጥያቄን በማጣጣልና በስም ማጥፋት ለመግታት መሞከር ከጀመረ ራሱን ጠልፎ እየጣለ ነው። ምክንያቱም፣ የለውጥ ጥያቄ ተፈጥሯዊና አይቀሬ ነው። እንዲህ ያለ ፀረ-ለውጥ አቋም ይዞ በስልጣን መቆየት የተፈጥሮ ሕግን እንደ መቀየር ነው። የተፈጥሮ ሕግን ይቀበሉታል እንጂ አይቀይሩትም። በተመሳሳይ የለውጥ ጥያቄ ይቀበሉታል እንጂ አያስቆሙትም። በአጠቃላይ፣ የለውጥ ጥያቄን በማጣጣልና ስም በማጥፋት ማስቆም አይቻልም።

ችግሩ በአብዛኛው የሚስተዋል በህወሓት/ኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ነው። “ታዲያ ይህ አካሄድ ህወሓትን ያዋጣል ወይስ አያዋጣውም?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ እንደ ችግሩን እንደ መፈለግድ ከባድ አይደለም። አንድ የፖለቲካ ቡድን የለውጥና መሻሻል ጥያቄን በማጣጣልና በስም ማጥፋት ለመግታት መሞከር ከጀመረ ራሱን ጠልፎ እየጣለ ነው። ምክንያቱም፣ የለውጥ ጥያቄ ተፈጥሯዊና አይቀሬ ነው። እንዲህ ያለ ፀረ-ለውጥ አቋም ይዞ በስልጣን መቆየት የተፈጥሮ ሕግን እንደ መቀየር ነው። የተፈጥሮ ሕግን ይቀበሉታል እንጂ አይቀይሩትም። በተመሳሳይ የለውጥ ጥያቄ ይቀበሉታል እንጂ አያስቆሙትም። በአጠቃላይ፣ የለውጥ ጥያቄን በማጣጣልና ስም በማጥፋት ማስቆም አይቻልም።