ነዋይ ደበበ ታማኝ ዕድል ነፈገኝ እንጅ ይቅርታ ለመጠየቅ እፈልጋለሁ!” እያለ ነው አሉ! ታማኝን ጎሽ ደግ አርገሀል ልለው እወዳለሁ፡፡ ታማኝ ከማናችንም በላይ ነዋይን አሳምሮ ያውቀዋል ብየ አስባለሁ፡፡ ነዋይ ማለት የሱቅ ዕቃ ማለት ነው፡፡ ገንዘብ ያለው ሁሉ የሚገዛው ወይም የፈለገውን የሚያሠራው፡፡ ነዋይ ሲበዛ ገንዘብ አምላኪ ነው፡፡ ስምን መልአክ ያወጣዋል!” የሚለው ብሒላችን ነዋይ ላይ እና ታማኝ ላይ እንደሠመረ ሌላ ሰው ላይ ሠምሮ አላየሁም፡፡ ኅሊና የሚባል ነገር የላውም፡፡ ነዋይ ገና ለገና አላሙዲን ገንዘብ ይሰጠኛል ወይም ይሸልመኛል ብሎ ኅሊናውን ሸጦና ቃሉን በልቶ ለወያኔ ያደረ የሰው ቆሻሻ ነው፡፡

ራሱን በዚህ ደረጃ ካረከሰና ካዋረደ በኋላ የተመኘውን ገንዘብ አላሙዲን እንደሰጠው ቢነገርም ነዋይ ግን አምስት ሳንቲም አላየሁም እያለ ነው፡፡ አላሙዲን ነዋይን በነፍሱ ነው የተጫወተበት፡፡ ገንዘብ ገንዘብ ያለ ሰው መጨረሻው ይሄው ነው፡፡ ነዋይ የተባለውን ገንዘብ ለማግኘት ቢጠብቅ ቢጠብቅም ሊያገኝ ስላልቻለ፣ በሕዝብ ስለተጠላም የጨረሰውን አልበሙን ለገበያ አቅርቦ መሸጥ ስላልቻለና የወያኔ ጀምበር እየጠለቀች እንደሆነ ሲገባው አጉል ሆኘ ልቀር ነው!” የሚለው ሥጋት ሲያስጨንቀው ነው አሁን አሜሪካ ገብቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ!” እያለ ያለው፡፡

እኔ በግሌ እንደ ነዋይ ደበበና ሰሎሞን ተካልኝ ላሉ ኅሊና ቢስና ለከት የለሽ ብልጠትን የሕይዎታቸው መርሕ አድርገው ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች ፈጽሞ ይቅርታና ምሕረት ይገባል ብየ አላምንም፡፡ እነኝህ ሰዎች ተሠርቶ መለወጥ በሚቻልባት የተስፋይቱ ምድር (Land of opportunity) አሜሪካ እየኖሩ እዚህ ሀገር ቤት እንዳለ ሰው ለመኖር ኅሊናቸውን ለመሸጥ ሳይገደዱ ሠርተው መኖር እየቻሉ ነው በሀገርና በሕዝብ ላይ ክህደት የፈጸሙት፡፡

ለእነኝህ ዓይነት ሰዎች ይቅርታና ምሕረት ቁልፍ የማታለያ መንገዳቸው ወይም ዘይቤያቸው ናቸው እንጅ ትልቅ ዋጋና ክብር ያላቸው ባሕላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች አይደሉም፡፡ ይቅርታ ሲደረግላቸው ማታለል ስለቻሉ ይቅርታ እንደተደረገላቸው አስበው የማታለል ችሎታቸውን ያደንቃሉ እንጅ ሐዘኔታ ተደርጎላቸው ይቅርታውን እንዳገኙ አያስቡም፡፡ ስለዚህም በተደጋጋሚ ይቅርታና ምሕረት ቢደረግላቸውም በተደጋጋሚ ክህደት ከመፈጸም አይመለሱም፡፡

እነኝህ ዓይነት ሰዎች የጥቅም አሳዳጅነት ሰብእና ስለሆነ ያላቸው የኅሊና ጥያቄ የሚባል ነገር አያውቁም፡፡ ከሞቀበት ሁሉ መዝፈን የተካኑበት ችሎታቸው ነው፡፡ ለራሳቸው ክብር የላቸውም፡፡ ጥቅም ለማግኘት ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ ስለሆነም ለነዋይ ደበበ እና ለሰሎሞን ተካልኝ እንዲሁም ለቢጤዎቻቸው መቸም ቢሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታና ምሕረት ሊያደርግ አይገባም!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com