ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ዛሬ ከእስር ተፈቷል

ከእስር ከወጣ በኃላ ከወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ጋር

 

 

 

የፍትሕ ዋና አዘጋጅ ከዝዋይ እስር ቤት ተፈታ

15 October 2017 ታምሩ ጽጌ

የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከሦስት ዓመታት የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠዋት ከዝዋይ እስር ቤት ተፈታ፡፡

የዛሬ ሦስት ዓመት ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. የታሰረው ተመስገን የተከሰሰው ለአመጽ የሚያነሳሱ ጽሑፎችን በመጻፍና የባለሥልጣናትን ስም በማጥፋት ነበር፡፡ ተመስገን እስሩን የጨረሰው ከትናንት በስቲያ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ማረሚያ ቤቱ ታራሚውን ሊፈታው ፈቃደኛ አልነበረም፡፡

በዚህም የተነሳ ተመስገን የረሀብ አድማ ጀምሮ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ጠዋት ላይ ግን እንዲፈታ ተደርጓል፡፡ የጋዜጠኛ ተመስገን ክስ የተጀመተው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸው በፊት ቢሆንም፣ እርሳቸው ሲሞቱ ክሱ ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ነበር፡፡

ሆኖም ዓቃቤ ሕግ ክሱን በድጋሚ አስነስቶት ነው ተመስገን የሦስት ዓመት እስር የተፈረደበት