Skip to content
‘ጫካ ውስጥ አስቀምጠው ለተከታታይ ቀናት ደፍረውኛል”- BBC
18
ኦክተውበር
2017
የተፈናቃዮች በሐማሬሳ መጠለያ ውስጥ
ኢብራሂም አሊ አብደላ በኢትዮጵያ
–
የሶማሌ ክልል ቀብሪ ደሃር ከተማ ከ
20
ዓመታት በላይ የኖረ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ነው። የተከሰተውን ሲያስታውስ፤ በወቅቱ እነደለመደው በጠዋት ተነስቶ ነበር።
”
በድንገት መጥተው በዱላና በድንጋይ ሲደበድቡኝ ወደ ሥራዬ ለመሄድ ፈረሶቼን አዘጋጅቼ ነበር
”
ይላል።
በዚያን ዕለት የክልሉ ወጣቶች በልዩ ፖሊስና በአካባቢው ባለሥልጣናት እየታገዙ ኦሮሞዎች ላይ ድብደባ መፈፀም እንደጀመሩ ይናገራል።
”
ህይወታችንን ለማትረፍ ጋሪዬን ጥዬ ከቤተሰቦቼ ጋር ወደጫካ ሸሸሁኝ
”
ይላል ኢብራሂም።
ኢብራሂም አሁን የሶማሌ ክልልን ለቀው በተለያዩ መጠለያዎች ካሉት
119
ሺህ ከሚደርሱ ተፈናቃዮች መካከል አንዱ ነው። ይህ ቁጥር የተገኘው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአደጋ መከላከል ኮሚሽን ነው።
በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በኦሮሚያ በኩል ከ
450
ሺህ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ይህ ቁጥር በፍጥነት ወደ
600
ሺህ እየተጠጋ መሆኑን ኮሚሽኑ ይናራል።
ኢብራሂም በአሁኑ ጊዜ በሐረር ከተማ በሚገኘው ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው የመጡ ከ
4000
በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ባስጠለለው ሐማሬሳ በተባለ ጣቢያ ውስጥ ነው።
በጣቢያው ውስጥ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ አስቸጋሪ እንደሆነና አንዳንዶችም ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በመጠለያው ውስጥ ያለ ክሊኒክ
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት የሚያብራሩ አምስት ነጥቦች
የመጠለያ ኑሮ፡ ስቃይና ተስፋ
በሐማሬሳ ጊዜያዊ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በሚገኘው ክሊኒክ ውስጥ ሙሉ ፊቷ የቆሰለ ሴት ተኝታለች። እሷ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት ናቸው በምትላቸው ሰዎች ለቀናት መደፈሯን ትናገራለች።
”
መጀመሪያ ከባለቤቴ ጋር ሆነን ያዙን
”
ትላለች።
”
ወደ ጫካ ወስደው አስረው ክፉኛ ደበደቡኝ። ከዚያም ለተከታታይ ቀናት የሚፈልጉትን ከፈፀሙ በኋላ መንገድ ላይ ጥለውኝ ሄዱ። ከአማራ ክልል የመጣ አንድ ሰው አግኝቶ ነው ወደ ሃኪም ቤት በመውሰድ የረዳኝ።
”
የምትለው ይህች ሴት እስካሁን ባሏ የት እንደደረሰ እንደማታውቅ ትናገራለች።
ሐማሬሳ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ለንግድ ተብሎ በብረት የተሠራ ትልቅ መጋዘን ነው።
አንዳንድ ተፈናቃዮች ሲናገሩ እዚህ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ልጅ ይዞ መጠለል እጅጉን ከባድ ነው፤ የምናገኘው ምግብ እና መጠጥ በቂ አይደለም ይላሉ።
የመፀዳጃ እና መታጠቢያ ስፍራ ጉዳይም እጅግ አሳሳቢ ነው።
“
አሁን ላይ የምግብ እጥረት የለም። ነገር ግን ተፈናቃዮቹ እንደለመዱት ማቅረብ በጣም ከባድ ነው
”
ይላሉ የምስራቅ ሓረርጌ ዞን አደጋ መከላከል ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቶሌራ።
በሌላ በኩል እያደገ የመጣውን የተፈናቃዮች ቁጥር መመገብ እጅግ ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ግርማ ዋታሬ ያስረዳሉ።
ከእነዚህ ተግዳሮቶች አለፍ ሲል ተፈናቃዮቹ ከወታደሮች የሚደርስባቸው ማስፈራራት እና ዛቻ ፈተና እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ይናገራሉ።
የተፈናቃዮች ጣቢያውን ተዘዋውሮ የጎበኘው የቢቢሲ ሪፖርተር እንደታዘበው ጣቢያው በኦሮሚያ ፖሊስ ጥበቃ ስር ቢሆንም ሌሎች ወታደሮችን በዙሪያው መመልከት ችሏል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ስለጉዳዩ ለቢቢሲ ሲያስረዳ
“
ተፈናቃዮቹ ስለየትኛው ማስፈራራት እንደሚያወሩ መረጃው የለንም
”
ብሏል።
እናቶችና ህፃናት በመጠለያው ውስጥ
በቀጣይ
. . .
በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ብቻ ወደ
72
ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ ላይ በትምህርት ቤቶች እና ጊዜያዊ የመጠለያ ሥፍራዎች ነበር የሚገኙት።
አሁን ግን ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ክፍት በመሆናቸው ቅርብ ዘመድ ያላቸው ተፈናቃዮች ወደዚያ ሲያመሩ፤ የተቀሩት ደግሞ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ።
ወ
/
ሮ ራዉላ አዩብ በቀብሪ በያህ ከተማ ለ
12
ዓመታት በነጋዴነት ተሰማርተው ቆይተዋል። ግጭቱ ከመከሰቱ በፊት ራውላ የኢትዮጵያ
–
ሶማሌ ክልል ጎረቤቶቻቸው ጋር በሰላም ይኖሩ እንደነበር ያስውታውሳሉ።
“
በክልሉ ልዩ ኃይል የሚደገፉ ሰዎች ቤት ንብረታችንን አቃጠሉብን። ከዚህ በፊት እንደማያውቁን ሆኑብን
”
ይላሉ።
ወ
/
ሮ ራዉላ በአሁኑ ወቅት ከባለቤታቸው እና ከሰባት ልጆቻቸው ጋር ፈዲስ አካባቢ እህታቸው በሰጠቸቻው አነስ ያለ ቤት ውስጥ ይኖራሉ። ነገር ግን እንደተፈናቃይ ተስፋ እየቆረጡ እንደሆነ ያስረዳሉ።
የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አደጋ መከላከል ቢሮ እንዳስታወቀው ለተፈናቃዮቹ በፊት ከሚሠሩት ሥራ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሥራ ለማመቻቸት ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ጥቅምት
3/2010
ድረስ ለተፈናቃዮች የተሳበሰበው ገንዘብ መጠን
166
ሚሊዮን ብር ደርሷል።
Share this:
Telegram
WhatsApp
Tweet
Like this:
Like
Loading...
%d