Skip to content

በረከት ስሞንንም የተቃዋሚ ሀይሉ መሪ ለማድረግ ያቀደ የሚመስለዉ የባዶ ጮህት ፕሮፖጋንዳ:- 

October 19, 2017 

                 ጥያቄ:- የባሪያ ስነልቦና ተላብሰዉ የወያኔን እግር ሲያጥቡ ከነበሩ ሰዎች ድልን አንጋጦ መጠበቅ?

ሸንቁጥ አየለ

————————–

ወያኔን ዙሪያ ዙሪያዉን በሚደረግ ሩጫ እና ጩህት ማዉረድ አይቻልም:: ወያኔን እራሱን የሚመታ ሀይል እንጅ በወያኔ ዙሪያ የተሰበሰቡትን የባሪያ ስነልቦና ተላብሰዉ የወያኔን እግር የሚያጥቡትን ሰዎች በመለዋወጥ አይነቃነቅም::

አንድ ተደጋጋሚ የሞኝ ፕሮፖጋንዳ አለ:: ይሄኛዉ የወያኔ አሽከር ለቀቀ:: ያኛዉ የወያኔ አሽከር እንዲህ ብሎ ፎከረ:: አባ እንቶኔ የህዝቤ ክብር ተነክቶ ከህዉሃት ጋር አልቀጥልም ሲል ተናገረ:: አቶ እንቶኔ ደግሞ እንዲህ ብሎ መቀሌ ላይአሽከሮቹ ፊት ወያኔን አሽሟጠጠ ብሎ መተንተን አስቂኝ ነዉ:: ክብረቢሶቹ የወያኔ አሽከሮች እና የባሪያ ስነልቦና ያላቸዉ ኩልኩሎች እንኳን ስለ ህዝብ ክብር ሊጨነቁ የራሳቸዉም ክብር አያስጨንቃቸዉም::

አንዳንዱ እንደሚለዉ ደግሞ ነገሩን ወደ ፕሮፖጋንዳነት መቀየሩ በራሱ ወያኔን የሚያዳክም ድል ነዉ::ህዝብንም የሚያነሳሳ ስልት ነዉ:: ጦር ከፈታዉ ወሬ የፈታዉ ይባላል እና  የወያኔ አሽከሮች በወያኔ ላይ ፎከሩ: ወያኔን ለቀቁ ወይምወያኔን ከዱ ብሎ ጮክ ብሎ ማስወራቱ መልካም ነዉ ይላል:: ለህዝባዊ ትግሉም ጠቃሚ ነዉ ይላል::

ነገሩ ላይ ላዩን ሲያዩት እዉነት ይመስላል::ግን ህዝቡን በመጨረሻ አታሎ ተቃዉሞ ጎራዉን ለወያኔ አሽከሮች ገባሪ እንዲሆን የሚያደርግ አካሄድ ነዉ::ስዬ አብርሃ ከወያኔ ተጣላ : ወያኔ ሊወድቅ ነዉ: ስዬ አብርሃ ተቃዉሞዉን ይምራ ብሎስዬን የአንድነቱ ቀንደኛ መሪ አድርጎ ግማሽ የተቃዉሞ ሀይላቱን እስዬ ኪስ እንደከተተዉ የተደናበረ አካሄድ ለመድገም መነሳት ቢቀር የበለጠ ጠቃሚ ነዉ::

በርካታ የወያኔ አሽከር የነበሩ ተቃዋሚ መሳይ ሰዎች በዚሁ የተሳሳተ የጩህት ስትራቴጅ አሁን ተቃዉሞን አንቀዉ ይዘዉ ተቃዋሚዉን እርስ በርሱ እያባሉ እና ለወያኔም እየሰለሉ ማን ምንነቱ እንዳይለይ ሆኖ ነገሮች ሁሉ ተተራምሰዋል:: እነዚህን ወያኔ የተነፈሰባቸዉ ተቃዋሚ የሚመስሉ ሰዎች ዛሬ መናገር አይቻልም::ህዝቡ ዉስጥ እንደ ጀግና ገብተዉ ተሰግስገዋል እና::ይባስ ብሎም ዋና የተቃዋሚ መሪ ሆነዉ ጥቅም በሚያመታላቸዉ መልክ ተቃዉሞ የሚመስል ስራንእያከናወኑ ህዝብን ማጃጃል ይዘዋል እና::ህዝብ እነዚህን የወያኔ አሽከር የነበሩ ተቃዋሚ ሰዎች ዛሬ የተናገረበት ሰዉ ጠላቱ ይመስለዋል:: እናም የወያኔ አሽከሮች ከወያናአ ሲለቁ እና ሲጣሉ ያልተጠና የፕሮፖጋንዳ ጮህት ከጥቅሙ ጉዳቱያመዝናል::

እናም ከፕሮፖጋንዳዉ ትርፍ ይልቅ ቀጣይ እና ዘላቂ  በሆነ መልክ የተቃዉሞዉን አመራር በወያኔ አሽከሮች እግር ስር ሊጥል የሚችለዉ አካሄድ ይቁም ብለን እንመክራለን::ሰሚ ካለ ነዉ ታዲያ::አለዚያ ዝም ብለህ ጩህ:: ወያኔን ዙሪያዙሪያዉን በሚደረግ ሩጫ እና ጩህት ማዉረድ አይቻልም:: ወይም የወያኔ አሽከሮች ተጠራርገዉ የወያኔን አዳራሽ ጥለዉ ቢወጡም ወያኔን የመበታተን አቅም የለዉም::

Share this:

  • Click to share on Telegram (Opens in new window) Telegram
  • Click to share on WhatsApp (Opens in new window) WhatsApp
  • Tweet

Like this:

Like Loading...

Your true media source

All rights reserved

%d