October 21, 2017

በሰሜኑ ክፍለሀገራችን እየተናፈሱ ያሉ በጠባብነት መርዝ የተነከሩ ኣየሩን እየበከሉት ይገኛሉ ። በኣሁኑ ጊዜ ቀደም ሲል ኢሳእያስ ኣፈወርቅ ካሁን በፊት ያልነበረው መለሳለስ በተለይ ከኣፍሪካ ቀንድ ካሉት ጎረቤት መንግስታት እና ሀገራት የነበረንን ሸካራ ግንኝነት በመሻሻል እንታረቅ ኣለን ብሎ ሲናገር ተደምጧል ።

ኣሁን በቅርብ ደግሞ ከትግራይ ክልል የሚናፈሱ ያሉ ኣስደንጋጭ ወሬዎች ድሮውን ቡዙ ሊሂቃን ዜጎች እንዲሁም የኣገር ኣንድነት ወዳድ ህዝቦች በስጋት ይመለከቱት የነበረ ፣ ኣሁን ያተደብቆ የነበረ ኣገር በታኝ ጠባብነት ወደ በተግባር ለመፈጸም ፣ በኣንድ ኣንድ ፍጡራን ተብዬዎች ኣንቀጽ 39 ህገመንግስት መብታችን ፣ በመጠቀም ተገንጥለን ከኤርትራ ኣንድ በመሆን ጠንካራ የሰሜን ሃይል ለመሆን ኣይሻለንም ወይ በማለት መንደር ለመንደር እየተሽለኮለኩ መርዛቸውን እየረጩ ይገኛሉ ።
በሌላ በኩል ተጀምሮ ሳያልቅ ተቋጭቶ ተንሳፍፎ የሚገኜው የህውሓት ማእከላይ ኮሚቴ ስብሰባም የኣንቀጽ 39 የመተግበር ጉዳይ ተነስቶ ኣጨቃጫቂ በመሆኑ በልዩነት እንደተበተኑ ከፕላኔት የተናፈሱ ምንጮች ይጠቁማሉ ።
ይህ ኣደገኛ የሃገር ለኣላውነታችን በመበታተን የባንዳዎች ተልእኮ ለመፈጸም የሚንቀሳቀሰው ያለው ቡዱን ኣመንጩ ማነው ለማለት ባይቻልም ፣ ሃቁ ግን ወላጆቻችን እንደዚህ ኣይነት ሲነገር ምንጩ ምንድነው ሲሉዋቸው እባካቹ ተውን ገገሩ ስም ይወጣል ከቤት ይቀበላል ጎረቤት ይላሉ ። ኣሁንም እንደዚሁ ነው ነገሮች በደፈናው ።
በመሆኑ የኢትዮጱያ ህዝቦች ሙሁሯኖች ይህ የጠባብነት ማእበል በንቃት መመልከቱ ። በተለይ የትግራይ ህዝብና ሙሁራን ወላጆቻችን ከጥንት ጀምረው ለሁሉም ኢትዮጱያዊ ወነድሞቹ ግንባር ቀደምት ተሰልፎው የቀይባህርን ወራሪዎች በማንበርከክና መንኮታኮት ዘንት እለት እመከቱዋቸው ና እያጠቋቸው እንደመጡ ሁሉ ኣሁንም በባንዳዎች ሳንታለል ተጠንቅቀን ዘብ አንቁም !!!!!!!!!!!
ከኣስገደ ገብረስላሴ
ከመቀለ  11../02 / 2010