የሕወሐትን እስትራቴጅ አቃሎ መመልከት አይቻልም። አሁንም በዚህች የመጨረሻ ሰአት አንድ መንግስት በዜጋው ላይ ይሰራዋል ተብሎ የማይገመት ወንጀል እንደሚሰራ ጥርጥር የለም። የሚጠራጠሩ ካሉ በእርግጥም በሕወሐት ላይ ግማሽ እምነት ያላቸው እና የእስከ ዛሬውን ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ አማራ ሴራ ሊደረግ አይችልም ብለው የሚያስቡ የዋሃን ሊሆኑ ይችላሉ። በአዴን/ኦፒዴኦ የወያኔ አጋሰሶች መሆኑ ይሰመርበት። ሁለቱም ታዛዥ እና ለትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች አላማ አስፈጻሚ እንጅ ሌላ ወይንም እራሳቸውን የቻሉ ድርጅቶች ያለመሆናቸውን ተብሎ ያለቀ ጉዳይ ነው። ኦፒዴኦ ሕወሐት ወታደር አሰልፋ ኦሮሞ ዜጎችን በኦጋዴን ሶማሌ ስም ስትጨፈጭፍ እንደሰጎን አንገቱን ከአሸዋ የቀበረ የሙታን ማህበር መሆኑን አይተናል። በአዴን የተባለው ጉድም የወያኔ ሐርነት ትግራይን እቅድ አስፈጻሚ ለመሆኑ በወልቃይት፣ በራያ፣ በጸገዴ፣ በጸለምት የተካሄዱትን ዘር የማጥፋት ስራን አይቶ እንዳላየ ገፋ ሲል እነዚህ ክልልሎች ትግራይ ውስጥ ናቸው ብሎ የሎሌነት ስራውን የሰራ የባንዳ ማህበር ነው።

ወገኖቻችን በተወለዱበት ቀየ በመተከል አገራችሁ አይደለም ልቀቁ ተብለው በግፍ እና በግድያ ተገደው ሲለቁ ይኸው የመጋዦች ጥርቅም አንድ ቃል ያልተነፈሰ እንደነበር የቅርብ ትውስታ ነው። የሩቁን የአርባ ጉጉ፣ በደኖ የዘር ማጥፋት የወያኔ ዘመቻ ትተን በጉራ ፈርዳ በመለስ ዜናዊ እና በሽፈራው ሽጉጤ ትዛዝ በግድያ እና በግዳጅ የተፈናቀሉ ወገኖችን የመላው ኢትዮጵያ፣ የአንድነት እና የሰማያዊ ድርጅቶች ያውም በሌለ አቅም እና እየተሳደዱ ባለበት ሁኔታ ተፈናቃዩን የሞራል እና የማቴሪያል ድጋፍም ሲሰጡ የመጋዦቹ ማህበር በአዴን የተባለው ጉድ ከመለስ እና ከሽፈራ ጎን የተሰለፈ እንደነበር የምናስታውሰው ነው። ለታሪክም የተቀዱ የመለስ ዜናዊን እና የሽፈራው ሽጉጤን ቃሎች ይዘናል። 
በጎጃም በማቻክል እና ጎዛምን ወረዳወች በአዳጊ ሴት ልጆች ላይ የተፈጸመው እና የአለማቀፍ ህግን የጣሰ ወንጀል ልጆችን የማምከን ስራ በአዴኑ አባሪ ተባባሪ እንጅ ገለልተኛ እንዳልነበርም ያየነው ነው። ወንጀሉ እስከ እለተ የሕወሐት እና የስርአቱ ፍጻሜ ይቀጥላል። በመሰረቱ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ለመደራጀት እና አለምአቀፍ የጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎችን ድጋፍ ለማግኘት የቻለውም በመጀመሪያ እና እስከአሁን በቀጠለው መሰረታዊ የድርጅቷ ፕሮግራም አማራን ከምድረ ኢትዮጵያ የማጥፋት አላማ ነው። ይህ ዘመቻ ይቀጥላል።

በዚህ ሦስት ቀናት የሰማነው አሰቃቂው የወገኖቻችን በገጀራ መታረድ ዜና ወያኔ ሀርነት ትግራይ እና የአካባቢ የኦፒዲዮ አባሪ ተባባሪ ስራ እና ተግባር መሆኑን ሲሰማ እጅግ የሚያሳዝን እና ሕወሐት የተነሳውን እና እየተናጠጭ ያለበትን ህዝባዊ ተጋድሎ አቅጣጫ ለማስቀየር እንደዜጋ በማትቆጥረው እና ጠላቴ ባለችው አማራ ላይ የወሰደችው ወንጀል እስከ ወዲያኛው የማይረሳ ማንም የውጭ ጠላት የማይሰራው ዘግናኝ ወንጀል ነው።

የዛሬ የሕወሐት እና ተባባሪ አሽከሮቿ ወንጀል ልክ 1929 አም በእራስ እምሩ ኃይለስላሴ የጎጃም እና የጎንደር ጦር ላይ የተፈጸመውን ታሪካዊ የግራዚያኒ ተባባሪወች ወንጅል ያስታውሰናል። ክቡር አቶ ሐዲስ አለማየሁ በታሪክ ማስታወሻቸው ያስተላለፉልን የዚያን የተጋድሎ ታሪክ በጎሬ፣ በከፋ እና ጅማ የተንቀሳቀሰውን የጎጃም እና የጎንደር አገር አድን ሰራዊት የፈታው የሞሶሎኒ የደቡብ እዝ አዛዥ የጅማውን ገዥ አባጆቢርን ይዞ የአንድ የአማራ እራስ በ30 ጠገራ በመግዛት አዋጅ ነበር። ይህ እጅግ ዘግናኝ ጸረ ሕዝብ ስራ በውጭ ጠላት በጥሊያን የተተገበረ ዛሬ በሕወሐት ሲፈጸም ማየት አዲስ ባይሆንም እጅግ አሳዛኝ መሆኑን መግለጽ ያስፈልጋል። በውጭም ሆነ በውስጥ የሚኖር ዜጋ ይህን ወንጀል ለመታደግ መተባበር ይገባል። በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ የሚያምታቱ እየተፈጸመ ላለው ወንጀል ተጨማሪ ድጋፍ ሊሰጡ የሚችሉ በሕወሐት የፌስቡክ ሰራዊት ሊስተጋባ መቻሉን ሳንረሳ ዜጎችን ለመርዳት መተባበር በየአካባቢው ይህን በተመለከተ የእርዳታ እና የትብብር ግዚያዊ ማህበራትን ልክ እንደጉራ ፈርዳው፣ መተከል ግዜ መጀመር ያስፈልጋል። ሊደርጉ የሚችሉትን ሁሉም በየፊናው በየአካባቢው ይስራ እንጅ የትግራይ ጠባብ ቡድን የዘየደችልንን መስመር መከተል ሳይሆን ማፍረስ ያስፈልጋል። የወያኔ የጥፋት ጎዳና እስከ መጨረሻዋ ሰአት ይቀጥላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

መንግስቱ ሙሴ