October 23, 2017 – ቆንጅት ስጦታው

የአማርኛ ጥላቻ!

ወልቃይት ውስጥ የንግድ ቤቶችን ስምና ማስታወቂያ በአማርኛ ፅፈው የነበሩና ባለፈው ሁለት ወር ውስጥ በትግርኛ እንዲቀይሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው አንቀይርም ያሉ ነጋዴዎች በገፍ ለእስር እየተዳረጉ ነው።
በዳንሻ፣ ሁመራ፣ ማይካድራ በአማርኛ የተፃፈው በትግርኛ እንዲቀይሩ ተነግሯቸው አንቀይርም ያሉ ነጋዴዎች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከአቅማቸው በላይ ግብር የተጨመረባቸው፣ ንግድ ቤታቸው የታሸገባቸው እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

በአማርኛ ተፅፈው የነበሩ የንግድ ማስታወቂያዎችና ስሞችን በትግርኛ እንዲቀየሩ ትዕዛዝ ከተሰጠባቸው ከተሞች መካከል አዲረመፅ ላይ ሁሉም ትዕዛዙን በመቃወማቸውና በነጋዴዎች አንድነት ምክንያት ለተናጠል ጥቃት ባለመዳረጋቸው ህወሃት እርምጃ መውሰድ አልቻለም።

የንግድ ድርጅት ስም እና ማስታወቂያዎችን በአማርኛ ቋንቋ ያደረጉት ለእስር፣ ለእንግልትና ለተጨማሪ ግብር ሲዳረጉ የእንግሊዝኛ ስም እና ማስታወቂያ ያላቸው ምንም አልተባሉም