November 1, 2017 08:01

በግፍ ኣገሳቁለን ለበታተነው የህወሓት ታጋይና ለትግራይ ህዝብ እግር ስር ወድቀን ይቅርታ ንጠይው እሱን በመካዳችን ከመላው የኢትየጱያ ህዝብ ተነጥለናል ፣
ይላል የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ፡ ማእከላይ ኮሚቴ የት ኣለ እና ? ኣሁን ያለው የህወሓት ኢህኣደግ ኣማራር እኮ የውሼት ጋርዲያን (.ዓርሲ ) ነው ። የጋርድያን እና ዓርሲ ትርጉም በመጨረሻ የዚህ ጽሁፉ ተመልከቱ ።
የህወሓት ማእኸላይ ኮሚቴ ዛሬ ከኢትዮጱያ ህዝቦች በኣጠቃላይ ፣ በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ህጻን ሽማግለ ፣ ሙሁር ተማሪ ፣ ነጋዴው ፣ባለሀብት ሳይለይ ፣ ከደደቢት ጀምሮ ተሸክሞ ኣዲስ ኣበባ ኣራት ኪሎ ካስገባው በኃላ ለ17 ኣመት እልኽ ኣስጨራስ ጸረ ደርግ ጦርነት ባደረገው ተጋድሎ ንብረቱ ልጆቹ ኣስጨርሶ ከድል በኃላም ለ26 ኣመት ሙሉ ለውጥ እናመጣለን ፣ ከሰደት ውርዴት እናድናሃለን ፣ ከምዝበራ ፍት እጦት እናድናሃለን ፣ ብለው ቃል የገቡለት ወደ እሳት እየማገዱ ለመሰዋእት ለኣካለ ጉዳተኝነት የዳረጉት በመክዳት ፣ ለራሳቸውና ለቤተዘሞዶቻቸው ጥቅም ሲሉ የሀገራችን ኣንጥሯ ሃብት እየወረሩ (እየመዘበሩ ) በህዝብ ጫንቃ እየጨፈሩ የዝህች ኣገር ልዩ ፍጡራን ሆነው ሲታዩ ገና ከጅምሩ ብለሽወነታቸው ወይ ወራሪነታቸው ኣውቀው እና ነቅተው ለመስተካከል የሞኮሩ በኣስር ሽዎች የሚቆጠሩ ተጋዮች ፣እጅግ ቡዙ ህዝቦች በመላው የሀገራችን ህጋዊና ህቡእ እሱር ቤት በማስገባት ፣በመባረር የበታተኑዋቸው ። ኃላም ኣመለካከትህ ኣባባልህ ፣ የመን ዘርነህ ወዘተ ደስ ኣልበለኝም የሚል የመለስ ዘይናዊ ሌጋሲ ተከትለው የኣንጃ ተላላኪ ፣ የትምክህትና ጠባብነት ጥገኛ የሚል ስም በመለጠፍ እጅግ ቡዙ ለውጥ ፈላጊ ዜጎች ኣጥፍተውና ኣሳድደው ሲያበቁ ዛሬ ብስባሴያቸው ፣፧ወራሪነታቸው፣ ዘረኝነታቸው በመታወቁ በሁሉም ኣቅጣጫ፥ የኢትየጱያ ክልሎች ህዝቦች ሊውጡዋቸው ሲነሱ ሲጨንቃቸው ጉዳቸው ለመደበቅ ቢሄር ከቢሄር፣ ክልል ከክልል ዘር ከዘር ፣ ጎሳ ከጎሏሳ በመጋጨት ለመደበቅና የስልጣን እድሚያቸው ለመራዘም ቢሞኩሩም ፣ ከህዝብ ጥርስና ኣይን እንደገቡ ስለገባቸው የበታተኑትና ያዳከሙት ባገር ውስጥ እና በስደት ላለው የህወሓት ታጋዮች ነበር ፣ እንዲሁም ፈርሰው የነበሩ የህወሓት ደጋፊ የነበሩ ስቢክ ማህበራት ፣ ከህወሓት ኣንጃ ተብለው ወጥተው የነበሩ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ እና ደጋፊዎቻቸው ጭምር ከየኣሉበት ሰብስበን በእግራቸው ወድቀን ለምን አንታርቀም ታርቀን ቨ ህወሓት ኣድነን ወደነበረችበት ደረጃ እንመልሳት በማለት ለሌለችው ( ጋርድያን ) ( ዓርሲ ) ሆና የቀረችው ህወሓት እናድናት በማለት በመለው ትግራይ ፣ በኣዲስ ኣበባ ፣ በኣመሪካ ከናዳ ፣በኣውሮፓ ፣ በሌሎችም ኣህጉሮች እየዞሩ ለምነው ሊያደራጁ ናቸው ። እንዳው በኣሁኑ ጊዜ ኣዲስ ኣለም በሌማ የትግራይ ምክትል ፕረዝዳንት ፣ ኣለም ገብረዋህድ የትግራይ ክልል የፓለቲካ ሃላፊ እና የህወሓት ቢሮ ሃላፊ በኣውሮፓ የሚገኙ ስቢክ ማህበራት እና በዛው ለሚገኙ ታጋይ ነበር እየሰበኩ ይገኛሉ ። በኣመሪካም በተለያዬ መንገደ ኣመሪካ ተሰደው የነበሩ ታጋዮችም ህወሓት እናድናት በማለት እየተዳራጁ ይገኛሉ ።

ለመሆኑ ህወሓት እናድናት ብለው ሲያታሉልን የተኛው ህወሓት ለማዳን ነው ????

በኣዴንን ፣ ኦሆዴድም ፣ ዴህደን የሰራ እንዲሁም ሌሎች ተቀጥያ ለምልኣተ ጉባኤ ሟሟያ ተብለው እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሰራቸው ኣጋር ፓርቲዎች ከሆኑ እስከ 1983 ዓ ም በነበረው ጸረደርግ ጦርነት ታሪክ የሰሩና፣ ከዛ በኃላ ከሽግግር መንግስት እስከህገመንግስት ማጽደቅ የነበረ በሸ የሚቆጠሩ ታሪክ የሰሩ ታጋዮች የበላ ህወሓት ከሆነ የሃገር ሉኣላውነት ኣሳልፎ የሰጠ ፣ ሀገራች የጸጥታና ድህንነታ የሚያረጋግጥ፣ የኢኮኖሚያችን ምንጭ የሆነ የባህር በራችን ያጠፋ ህወሓት ኢህኣደግ ከሆነ የክህደት ታሪክ እንጅ ለይህ ትውልድ የሚጠቅም ታሪክ የለውም ። ታሪክ ነው ከተባለ ደግሞ በጥቁር ታሪክነቱ ይህ ትውልድ እንዳይደግመው እየረገመው እንዲኖር ኣስፈላጊ ሊሆን ነው ። በቃ ታሪክ ሆኖ ኣልፏል ። ታድያ ኣሁን ሀወሓት ኢህኣደግ ጠግነን እናድን ስትሉን ለየተኛው ሀወሓት ኢህኣደግ ነው ? የሞተ ይመለሳል ወይ ይህ ኣስተሳሰብ እንደ ቅጀት ነው ኣድርጌ እምመለከተው ።

በእኔ እምነት ትክክለኛ ታሪክ ነ ው ብዬ እማምንበት ባለፉት 43 ኣመታት የተሰሩ ታሪኮች በሁለት ተከፍለው በጥሩ ነታቸው እና በመጥፎነታቸው መታየት ኣለባቸው ።

1
ኛ ህወሓት ከ1967 ዓ ም እስከ 1984 ዓ ም የሽግግር መንግስ የነበረው የትግል የመስዋእት ዘመናት የነበረ ትውልድ ምንም እንኳ በህወሓት ኣማራር እና ተላላኪ ካድሪዎች በሃገር ሉኣላውነት ጉዳይ የማይናቅ የክህደት ድክመት ቢኖሯቸው ፣ በውስጣቸው የሀገር ካሀዲሆች ግለሰዎች ተሸክመው የተጓዙ ቢሆንም ። ቡዙሃኑ የሰሩት ኣመርቂ ታሪክ ግን ኣሁንም ለይህ ትውለድ መተክያ የለለው እና በመልካም ታሪክነቱ በጥሩ ተሞክሮ መተላለፍ ይበገበዋል እላለሁ ።

2
ኛ ከ1984 ዓ ም እስከ 2010 ዓ ም ያለው 26 ኣመት የተባሸ ስርኣት በጸረ ዲሞክራሲ የሰብኣዊ መብት ጥሰት ፣ በግድያ በእስራትና የዜጎች የስቃይ ምርመራ ፣ የሙሱና እና ምዝበራ ዘመን የነገሰበት ፣ ባለስልጣናት በህዝቦች መካከል ቢሄር ከቢሄር በመጋጨት ክልል ከክል ጦርነት እልቂት በማወጅ ፣ የሀይማኖት የዘር ግጭጥ በመፍጠር የምዝበራ ስርኣታቸው የስልጣናቸው እድሜ ለመራዘም የሚሯሯጡበት ፣ የሃገሪቱ ሃብት ዔበሙሉ የግላቸው እና በገዥ ፓርቲዎች በሞኖፓል በመያዝ እንዲሁም የነሱ ሸሪኮች የታጠቁ ሌቦች በስመባለ ሃብትነት በመደራጀት ያገራችን ኣንጡራ ሃብት የወረሩበትና ብዙሃኑ ዜጎች ለሰደት በዬሄዱበት ለምት የተዳረጉበት የተማሩ ወጣቶች በስራ ኣጥነት በብራነዳ የወደቁበት ፣ ኣጠቃላይ የኣስተዳደር መዋቅራቸው በቤተሰብ በዝምድና ፣በዘር ፣ በጓደኝነት ወይ በኣድርባይነታቸው ብቻ የሚኖሩ ጥቂት በሙሱና የተባለሹ ሙሁራኖች በማዋቀር በሀገራችን የተባላሸ ስርኣታቸው እንዲያንሰራፋ በማድረግ ኣገራችን ወደ ጨለማ በማስገባት እድገታ ከሱማል፣ደቡብ ሱዳን ፣ ኤርትራ ብቻ በልጣ እንድትገኝ ኣድርገዋታል ።

ሀገራችን መልካም ኣስተዳደር ነጻ ዳኝነትና ፍትህ ጠፍቶ የድሮ ህወሓት የቡዙሃን ፓርት (ማልቲ ፓርት ) ስርኣት ተረጋግጦ ዜጎች በመረጡት እንዲተዳደሩ ታሳቢ በማድረግ የኣእላፍ መስዋእት የተከፈለበት ለውጥ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴና እሱ የሰራቸው ቡዱኖቹ በማን ኣለበኝነት ረግጠው የሚሸጡዋት ኣገርና ህዝቦቿ ሆነዋል።
እንግዲህ የህወሓትና ቡዱኖቹ ኣማራር በሁለተኛ ዙር 26 ኣመት አገዛዙ የፈጸማቸው ኣሳፋሪ ተግበር ኣይተናል ።

የላሸቀው ፨ የህወሓት ኢህኣደግ ኣመራር ደግሞ ስርኣቴ እሞቶ ስላለ ከሞት ኣፍ እንዲሞሉሱኝ ከድሮ ጀምሬ የበተንኩት ታገጋይ እና በትግል ጊዜ እንደ ኣሳ ባህር ሆኖ ሂወቴ የነበረ ህዝብ በድዬህ ነበርኩ እና ኣሁን ከሞት ኣፍ ኣድነኝ በማለት ታርቄ ስልጣኔ ኣጠናክራሉ እያለ የሌለው የህወሓት ጋርድያን ( ዓርሲ ) እንደጣኦት ልናመልካቸው ሽርጉድ ሽርጉድ ይላሉ ። እኔ እሚገርመኝ እነዚዚ በባዶ ታሪክ የተባላሹ ኣታለዮች ማን ነው የነሱ የታሪክ ሌጋሲ የሚከተል ?
በእኔ እምነት በለፉት 26 ኣመታት የኣፈና እና የፋሽዝም ስርኣታቸው የኢትየጱያ ህዝቦች በተለይ የትግራይ ህዝብ የተጎዳ በመሆኑ ለነዚህ ፍጥራን ለምን እናድናቸዋለን እነዚ ሰው መሰል ፍጡራን እግዚኣቤሄር ያጠፋቸው ኣይመልሳቸው ። ይህ እምነት የእኔ እምነት ብቻ ኣይደለም ፣ የኣንድ ሞቶ ( 100) ሚሊዮን የኢትዮጱያ ህዝቦች ነው ። እንግዲህ ካሁን ጊዜ ጀምሮ ይህ ትወልድ የራሱ ኣዲስ ታሪክ ይስራ ። ከእንግዲ ወዲህ ህወሓት ሊገኝና ሊታደስ ኣይችልም ።
ኣንድ ነገር ግን የህወሓት ታጋዮች የነበራችሁ የህወሓት መሪዎች ባደረሱባችሁ ግፍ ተበታትናችሁ ባገር ውስጥም በውጭ ኣገር የከፋ የስደት የድህነት ንሮ እየገፋችሁ የምትኖሩ ሁሉ በ17 እና 18 ኣመታት እልህ ኣስጨራሽ ጸረ የደርግ ትግል ፋሽዝም የፈጸማችሁ የፈጸምነው ኣኩሪ ገድል የተወሰኑ ልነሰራቸው ይገባ የነበረ የሚጎድሉን ቢኖሩም በኣጠቃለይ ግን የማይፋቅ ኣኩሪ ታሪክ ሰርተናል ።መላው ህዝባችንም የማይፋቅ ኣኩሪ ታሪክ ሰርቷል ። በመሆኑም ባለፈው ጊዜ የሰራነው ታሪክ ታሪክ እንጻፈው ራሳችንም ታሪክ ነን ።ኣሁን ለሌለው ህወሓት ድሮ ጋርድያን ( ዓርሲ ) መሆኑ ኣረጋግጧል ።ስለዚዚህ ኣትድከሙ ሙቶ የተቀበረ ኣመለስም ።

ለዚህ ትውለድም እማስተላልፍለት መልእክት ጥቂት የዚህ ቡዱን ተጠቃሚ የሆናችሁ ከህወሓት መሪዎች ተሻርካቹሁ ለቡዙሃኑ የተማረ ማህበረ ከመጉዳት ታገሱ ።ወጣት ሙሁራን ናችሁና እስቡበት ። እናንተ ከሁሉ ንጹህ የሆናችሁ ሙሁራን ወጣቶች ፣ተማሪዎች ወዘተ ፍራቻ ስጋት ጥላችሁ የዚሁ ጊዜ የታሪክ ባለቤቶች ስለሆናች ለሞተው የህወሓት ከማጀብ የራሳችሁ ታሪክ ስሩ !!!

ከኣስገደ ገብረስላሴ

መቀለ
17 / 02 / 2010

ትርጉም
ጋርድያን በኣማርኛ ላም ትወዳለች ጥጃዋ ስትሞት ላማን ኣታልለው ለማለብ ሲፈልጉ የሞተው ጥጃዋ ቆዳው ገፈው በጥጃዋ ቅርጽ ገለባ ሞልተው ይደርቃል ከደረቀ በኃላም የውሼት ጥጃዋ እያላሱ ወተታቸው ይምጋሉ ።ይህ የውሼት ጥጃ ጋርዲያን ይባላል ።

በትገርኛም የውሼት የሞተው ጥጃዋ ገለባ ሞልቶ ላማ የውሼት ጥጃ እየላሰች ወተት ትሰጣለች ዓርሲ ይባላል ።

ስለዚህ ኣሁን ያለው ህወሓት ኢህኣደግ ። 26 ኣመት በውሼት ስም ገዝቶናል