November 4, 2017 01:52

ይህ የሙከራ ድምፅ ነው… ይሰማል መቀሌ!

የዛሬው የመቀሌ ሰልፍ መነሻው በነቀምቴ ተገደሉ ስለተባሉ የትግራይ ልጆች መሆኑን ሰምተናል። ሰልፉን ያዘጋጀው በትግራይ ብቸኛው እና ምስኪኑ አረና ነው… (ለምን ምስኪኑ አልከው? ሁሉንም አብራርተንማ አንዘልቀውም… በቃ አረና ዝም ብሎ ምስኪን ስለሚመስለኝ ነው…) እውነቱን ለመናገር በዚህ ግዜ አረና ብቻ ሳይሆን ትግሬ ሆኖ የመንግስት ተቃዋሚ መሆን እንደ ድፎ ዳቦ ከሁለት በኩል እሳት ላይ መጣድ ማለት መሆኑን በተለያየ ግዜያት አረጋግጫለሁ… ተቃዋሚው እምነት አይጥልባቸው መንግስት ደግሞ እንደማንኛውም ተቃዋሚ አበሳቸውን ያበላቸዋል… እኔ የነርሱ እይነት ድፎ ዳቦነት ቢደርስብኝ እስካሁን አርሬ ነበር… (እና ምን ሆነህ ነው የጠቆርከው… ? በል አሉህ ገበየሁ… ተወኝ ብያለሁ አንተ ሰው ሃሳቤን ልግለፅበት…ሃሃ)
እና በዛሬው እለት መቀሌ ላይ የተደረገው ሰልፍ መነሻው አነጋጋሪ ቢሆንም የሙከራ ድምፁ ግን ጥሩ ነው ባይ ነኝ… መነሻው አነጋጋሪ ለምን ሆነ? ያልከኝ እንደሆነ… ያው ታውቀዋለህ አንተስ እንደኔው የፌስ ቡክ ሰፈር ሰው አይደለህ እንዴ…
ባለፈው ግዜ በነቀምት ሰልፍ ላይ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ትግሬዎች ናቸው ተብሏል እናም ስለምን ትግሬዎች ጥቃት ደረሰባቸው? የሚል ነው የሰልፉ መነሻ!
እዚህ ጋ እንደተባለው እንኳ ቢሆን የጥቃቱ መነሻ ትግሬነታቸው ነውን? ብለን ብንጠይቅ መሆኑን እርግጠኛ ለመሆን አይቻልም…
አሁን አሁን በጣም የተቸገርነው ነገር። ምንድነው ያልከኝ እንደሆነ…አንድ አማራ የሆነ ሰው ጥቃት ከደረሰበት ‘አማራነት ወንጀል ሆነ?’ የሚል ትልቅ ግርግር ከአማራ ብሔርተኛ ወዳጆቻችን ይነሳል… አንድ ትግሬ የሆነ ነገር ከሆነ ‘ትግሬ የሆነ ነገር ለመሆን የተፈጠረ ነውን?’ በሚል ሁካታ ከትግሬ ብሔርተኞች ይመጣል። አንድ ኦሮሞ አንድ ጉዳት ከመጣበት ‘ኦሮሞ እስከመቼ መጫወቻ ይሆናል’ የሚል ብጥብጥ ከኦሮሞ ብሔርተኛ ዘመዶቻችን ደመጣል። (ሌሎች ሰማንያ ምናምን ብሔረሰቦች ዝምታችሁ እንዴት እንደሚያስቀና ባወቃችሁልኝ!) ምንም ነገር ይፈጠር መነሻው ምንድነው? ብሎ መጠየቅ ፋሽኑ እያለፈበት ይመስላል… ከመጀመሪያው ኮሽታ በኋላ የሚመጣው ጥያቄ እነማናቸው የተጎዱት… እዛ ውስጥ በተለይ እነዚህ ሶስቱ ብሄረሰቦች ካሉበት… በቃ አለቀልን…! እንደ ሰው ወገን ስለምን ይጎሳቆላል ስለምን ይገደላል ብሎ መጠየቅ ሊቀር ከጫፍ ላይ ነው።
እና የዛሬው የመቀሌ ሰልፍም መነሻው ይሄ መሆኑ ቢደብርም ቅሉ… (የቱ ቅል… ? ሃሃ ኧረ አይዞህ ጨርሻለሁ ሙድ አትያዝ ዝም ብለህ አንብብ…)ህውሃትን በአጠቃላይም ኢህአዴግን በአደባባይ ለመቃወም መድፈራቸው፣ ፖሊስ ተዉ እያላቸው እምቢኝ ማለታቸው፣ እንዲሁም በሰልፉ ላይ ኢትዮጵያዊ አንድነትን መስበካቸው፤ የሚበረታታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ….
ዛሬ ዘነብኩባችሁ!!!
እና እናንተ ግን እንዴት ናችሁ… እሰይ ሰላማችሁ ሞልቶ ይፍሰስ!!!
አበበ ቶለሳ ፈዪሳ

 

[አረና ግን በቢሮው ኮምፑተር እንኩአ የለውም ወይ ደህና የእጅ ፅሁፍ ያለው ሰው የለውም ::የመቀሌ ሕዝብ ግን ገራሚ ነው የአሸንዳ ጭፈራ ቢሆን የሚቀድመው የለም ሃሃሃ ]

ቤትኛዉም አጋጣሚ ከትግራያ ወያኔን የሚቃወም ከተነሳ ጥሩ ጅምር ነው ሊበረታታ ይገበዋል ባይ ነኝ ገና ከጅምሩ የሰው ተግል ማጣጣል ፈታዊ አይመስለኝም ዘረኝነትን እያወገዝን እኛው እራሳችን ዘረኛ ሆነን እንዳንገኝ እሰጋለው

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ሰልፋችን በሰላምና በድል ተጠናቋል። በወታደሮች ጥረት የተሳትፎ ቁጥር ቢቀንስም ብዙ ሰዎች አደባባዩ ዳር

ቁመው እያጨበጨቡ ድጋፋቸውን ገልፀውልናል። የፀጥታ አካላት በኛ ላይ ያደረሱት ችግር የለም። እናመሰግናለን!’

 

Abraha Desta