November 4, 2017 10:59

እኔ የምለው አረናዎች የትግሬን ሕዝብ “በየመንገዱ ዳር በመውጣት እንድትመለከቱን!” ብሎ ነው እንዴ ጥሪ ያቀረበው??? የትግሬ ሕዝብ በዚህ ወቅት ወያኔ በመላ ሀገሪቱ በአራቱም አቅጣጫ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘርና በብሔረሰብ መሀል የዘር ግጭቶችን፣ ፍጅቶችን በማነሣሣት እርስ በእርስ እያጋጨ እያፋጀ በርካታ ወገኖቻችን በግፍ እንዲገደሉ፣ እንዲፈናቀሉ፣ ቤት ንብረታቸው እንዲወድም እያደረገ ሚገኝበት በዚህ ወቅት የትግሬ ሕዝብ ይሄንን የወያኔን ሰይጣናዊ ተግባር ምድር አንቀጥቅጥ በሆነ ሰልፍ ይቃወማል ተብሎ ሲጠበቅ በሰልፉ ባለመሳተፍና በመንገድ ዳር ተኮልኩሎ የስምንት ሰዎችን የሰልፍ ትርኢት በመመልከት ከማን ጋር እንደቆመ አሳየ፣ የማን ደጋፊ እንደሆነ አረጋገጠ፡፡ በእውነት ነው የምላቹህ ዛሬ የትግሬ ሕዝብ እጅግ ነው የተዋረደው፡፡
በብዛት የሠፈረውን የፀጥታ ኃይል ፈርቶና ጫና ስለተደረገበት ምናምን የሚል ሰበብ አይሠራም!!! እኛ እየሞትን፣ እንደ እባብ እየተቀጠቀጥን፣ እስር ቤት እየተወረወርን አይደለም ወይ የምንቃወመውና በቃኸን ያልነው??? እኔ እኮ የገረመኝ ሕዝቡስ እሽ ይቅር የአረና ፓርቲ አባላት ስምንት ሰዎች ብቻ ናቸው እንዴ?? ያውም እኮ ፈቃድ በተሰጠው ሰልፍ እኮነው መሳተፍ የተሳናቸው፡፡
የትግሬ ሕዝብ ወያኔ ቢመቸው፣ ወያኔን ቢወድ ነው እንጅ እንደተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደኛ ቢመረው፣ እንደኛ ቢያንገሸግሸው፣ እንደኛ ቢያሳስበው፣ እንደኛ ቢያስጨንቀው፣ እንደኛ ትንፋሽ ቢያጥረው ኖሮ እንኳንና ፈቃድ በተሰጠው ሰልፍ የሰልፍ ፈቃድ ሳይጠብቅ ነበረ እንደ ባሕርዳር፣ እንደጎንደር፣ እንደ አዲስ አበባ፣ እንደ አምቦና ሌሎች በርካታ የሀገራችን ከተሞች ሕዝብ ገንፍሎ በመውጣት እየሞተ፣ እንደ እባብ እየተቀጠቀጠ፣ እስር ቤት እየተወረወረ ወያኔን በቃኸን! ባለ፣ የጋለ ተቃውሞውን ባስተጋባ ነበር፡፡ የትግሬ ሕዝብ ሆይ! እጅግ በጣም አፍረንብሀል!!! ቢያንስ በዚህ ጊዜ እንኳ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ትቆማለህ መቆምህንም ታሳያለህ ብለን ጠብቀን ነበር፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com