ከቅርብ ጊዜ ወዱህ በኢትዮጵያችን የሚታየውን የፖሇቲካ ትኩሳት ተከትል የማጅራት መቺው የሕውሓት ሥርዒት አንዲንድ አሽከሮች ከሥሌጣናችን ‹‹በገዛ ፈቃዲችን›› ሇቅቀናሌ፣ ላልቹ ዯግሞ ከወትሮው የወያኔ ሞግዚት አስተዲዯር ነፃ ነን የሚሌ አንዯምታ ያሇው በሚመስሌ ድፍረት ሲናገሩ በመስማታችን ብቻ፣ የሕወሓት ቀኝ እጅ በመሆን ኢትዮጵያን ሇማፍረስ ሊሇፉት 27 ዒመታት 24/7 ሲሠሩና ሲዘርፉ፣ ሕዝቧን በጭካኔ ያሇመታከት ሲገድለና ወዯር ሇላሇው ስቃይ ሲዲርጉት የቆዩ ጉዶችን እውነተኛ የሕዝብ ሌጆች ሇማድረግና ሇማጀገን የሚዯረገው ጥድፊያ ምን ነካን እንድሌ አስገድዶኛሌ፡፡ ሇዚህም ነው እውነቱን እንዲናስተውሌ ማን አዚም አዯረገብን የሚሌ ጥያቄ ሇርእስነት የመረጥኩት፡፡

በመጣው ማዕበሌ ኹለ ከወዱህ ወዱያ የምንሊጋ፣ በነፈሰው ነፋስ ኹለ ጥርግ ብሇን የምንሄድ፣ በወጀቡ ኹለ የምንወሰድ ከሆነ ሇወያኔ ማምሻም ዕድሜ ነውና ዏረፍተ ዘመኑን ከማራዘም ውጭ የሚፈይዯው አንዲች ነገር የሇም፡፡ የነዚህ አሽከሮች ርምጃ እውነት ሇኢትዮጵያና ሇሕዝቧ ከማሰብ ከሆነ የፖሇቲካ ትኩሳቱን በማጋሌ ወያኔን ሇማስወገድ ሇሚዯረገው ሕዝባዊ እምቢተኝነት በመጠኑም ቢሆን እገዛ ሉያዯርግ ይችሌ ይሆናሌ፡፡ በላሊ በኩሌ የነዚህ ግሇሰቦች ፍሬአቸው ሳይታይ ባንድ ጀምበር የሚታየው የውዲሴ ከንቱ ጋጋታ ሕዝባዊ ተቃውሞውን አዯጋ ሊይ ሉጥሌ እንዯሚችሌ መገመት ዯግሞ ብሌህነት ይመስሇኛሌ፡፡ ወያኔ፣ እኔ አስገድጄ የማሌዯፍራት ኢትዮጵያ መበታተን አሇባት በሚሇው ሌክፍቱ የደርዬውን አገዛዝ ሇመጠበቅ በቆመው ዯኅንነቱ አማካይነት በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የርስ በርስ እሌቂት ዯግሶ ወገኖቻችን እያሇቁ ነው፡፡ ይህ ሰይጣናዊ ድርጊት ሲፈጸም እነዚህ ከፍ ከፍ ያዯረግናቸው ጉዶች ድርጊቱን በማስቀረት፣ ጥፋቱን በመቀነስ ወይም ከተፈጸመ በኋሊ በማውገዝ ረገድ ምን አዯረጉ? አዎንታዊ መሌስ የሇንም፡፡ በእኔ ትሁት እምነት ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው፡፡

ይህ መሌእክት ቀጣፊው ወያኔ በሳይበር ሚዱያው ያሰማራቸው ጀላዎቹን አይመሇከትም፡፡ ምክንያቱም ተሌኳቸው ነውና ይህንን የማዯናገሪያ ስሌት ሉጠቀሙ እንዯሚችለ ይገመታሌ፡፡ በመሆኑም መሌእክቱ ዑሊማ ያዯረገው 1ኛ/ ባሇማወቅ/በየዋህነት እንዱሁም የኔ ጎሣ የኔ ቋንቋ ተናጋሪ ነው በሚሌ አስተሳሰብ በስህተት ሰሇባ ሇሚሆኑ ወገኖች፤ 2ኛ/ ኢትዮጵያ በአስጨናቂ ምጥ ሊይ በምትገኝበት በዚህ ፈታኝ ወቅት የወያኔን አሽከሮች በማስዯንበር ሉፈጸም የሚችሇውን የርስ በርስ እሌቂት ሇመቀነስ ከማሰብ ወይም እነዚህ ተሊሊኪዎች ከሌብ ስሇማድረጋቸው እርግጠኛ ባይሆኑም አምኖ የመቀበሌ በሩን ሊሇመዝጋት (to give them the benefit of the doubt) ወይም ሇተቃውሞው ፖሇቲካ ፍጆታ ጠቀሜታ እንዯሚኖረው በማሰብ ከቅንነት ክስተቱን ሇሚያራግቡ ወገኖች፤እና 3ኛ/ በተቃዋሚው ጎራ ተሰሌፈናሌ የሚለ አንዲንድ በስመ ‹አክቲቪስትነት› የሚንቀሳቀሱ ግሇሰቦችን ይመሇከታሌ፡፡ ሁለንም በጅምሊ መኮነኑ ተገቢ ባይሆንም (ሇሕዝባዊ ተቃውሞው የማይናቅ አስተዋጽኦ በማድረግ የሚታወቁ አለና) ከእነዚህ ግሇሰቦች መካከሌ አንዲንዶች በሚያሠራጯቸው የተሳሳቱ መረጃዎች ምክንያት ቊጥራቸው ቀሊሌ የማይባሌ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን እያጡ መሆኑን በውሌ መገንዘብ ይኖርብናሌ፡፡

ስሇሆነም በሕዝባዊ ተቃውሞ ወያኔን እረፍት የመንሳቱን እንቅስቃሴ ከመቀጠሌ ጎን ሇጎን በወያኔና በየቦታው ባሰማራቸው አሽከሮቹ አማካይነት የሚዯረገውን መሠሪ ዯባ በንቁነት መከታተሌ የሁለም ኢትዮጵያዊ ኃሊፊነት ነው፡፡ ወያኔ ባዘጋጀሌን የጎሣ፣ የክሌሌ፣ የቋንቋ፣ የሃይማኖት ወዘተርፈ መከፋፈያ ወጥመድ ውስጥ ሊሇመግባትና ይህንንም ሊሌነቁ ወገኖቻችን በማስረዲት የእሌቂትና የባርነት ዘመኑን ማሳጠር ይኖርብናሌ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ታናሽ ወንድማችሁ ሇመምከር የምፈሌገው ወያኔ የዯገሰውን እሌቂትና ኢትዮጵያን የመበታተን ሤራ የሚያስፈጽመው ከራሱ ጎሣ በሆኑ አባሊቱ ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚጠቀምባቸው ክሌሌ ብል በሠራው የውስጥ ቅኝ ግዛት አጥር ባሰማራቸው፣ የኛን ቋንቋ በሚናገሩ የኛው ጎሣ አባሇት በሆኑ አድርባይ አሽከሮቹ አማካይነት መሆኑን በሚገባ ተገንዝበን ጸጉረ ሌውጡንም ሆነ በእኛ መካከሌ ያለ አሽከሮቹን በጥብቅ መከታተሌና ማጋሇጥ፣ ከተቻሇ ዯግሞ በፀረ ወያኔ ትግለ ተሳታፊ ማድረግ ይጠበቅብናሌ፡፡

ሇወያኔ ዯኅንነት አባሊት፣ ሇሠራዊቱና አድርባይ አገሌጋዮቹ
ወያኔ ሕወሓት የተፈጥሮ ሞት መሞቱ ሳይታሇም የተፈታ ነው፡፡ በዚህ ቀውጢ ሰዒት ታሪክ ሁሇት ምርጫ አቅርቦሊችኋሌ፤

1ኛ/ ወገናችሁ ከሆነውና ከአብራኩ ከወጣችሁበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ባንድነት በመቆም ኢትዮጵያዊ ኹለ አክ! እንትፍ! ብል የተጸየፈውን ይህን የበሰበሰ ‹ሥርዒት› ወዯ ታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት በማስገባት ከወገናቸሁ ጋር ሇነፃነት፣ ሇሰሊም፣ ሇእኩሌነትና መንግሥተ ሕዝብ ሇመመሥረት በሚዯረገው ሂዯት ተሳታፊ መሆን፡፡ ምርጫችሁ ይህ ከሆነ ሆዯ ሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሕረትና ይቅርታ እንዯሚያዯርግሊችሁ አትጠራጠሩ፡፡ ፈጣሪ ይህን ቀና መንገድ እንዱያሳያችሁ ጸልቴና ምኞቴ ነው፡፡

2ኛ/ ላሊኛው የጥፋት ጎዲና ሲሆን ከወያኔ ጋር በአገር ዝርፊያው እና ወገናችሁን በመግዯሌና በማሰቃየቱ በመግፋት በባርነት ሳሊችሁ ከወያኔ ጋር መቃብር መውረድ ዕጣ ፈንታችሁ ዕድሌ ተርታችሁ ይሆናሌ፡፡ ዋስትናችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ዛሬ ፍርፋሪ/ዲረጎት የሚጥለሊችሁ ሥጋ የሇበሱ አጋንነት አይዯለም፡፡ የትግራይ ወያኔ ቁንጮዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ዯም እንዯተጨማሇቁ በሌጆቻቸው፣ በዘመዶቻቸውና በታማኝ ጓዶቻቸው ስም ያሸሹትን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ሇመቀራመት ሽሽት መጀመራቸው የአዯባባይ ምሥጢር መሆኑ ከናንተ የተሠወረ አይመስሇኝም፡፡

ላሊው በውስጥም በውጭም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ከ27 የግፍና የሰቆቃ ዒመታት በኋሊ የወያኔን ባህርይ አሇማወቅ የተያዝንበት አዚም ከላሇ በስተቀር በእጅጉን ያስተዛዝበናሌ፡፡ ወያኔና አሽከሮቹን እስከ መጨረሻው ባሇማመን መጽናት በየትኛውም መመዘኛ ከጉዲቱ ጥቅሙ እንዯሚያመዝን በግላ አምናሇሁ፡፡ በተሇይ ጥቂት በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን አገር ቤት ያሇና መድረሻ ያጣ ወገናችሁን በተሳሳተ መረጃና በ‹ጽሑፍ› ሱስ ብቻ ወዯ ወያኔ የእርድ በረት አትምሩት፡፡ አዯራ በሰማየ አዯራ በምድር፡፡

በመጨረሻም የብዙ ፍሌጥ ማሰሪያው ሌጥ እንዱለ አበው፣ ሁለም ኢትዮጵያዊ ከባርነት ሇመሊቀቅ በሚያዯርገው ትግሌ የአቅሙን አስተዋጽኦ ከማድረግ ጎን ሇጎን እንዯ እምነታችን (ወያኔ በቤተክህነትና በቤተመስጊድ/በየቤተ እምነቱ ባስቀመጣቸው እና የጥፋት ተሌእኮው አስፈጻሚዎች ትእዛዝ ሳይሆን) ሇሁሊችን እናት ኢትዮጵያ ህሌውና እና ሇሕዝባችን ዯኅንነት ስንሌ ከሌባችን በኅብረትና በተናጥሌ አጥብቀን ቀን ከላት ሌንጸሌይ እግዚኦ ሌንሌ ይገባናሌ፡፡ ታዱያ ጸልታችን ከዯመና በታች እንዲይቀር ሰው ሠራሽ በሆኑት ጎሣ፣ ቋንቋ፣ አካባቢ በመሳሰለት ሳንከፋፈሌ እንዯ አንድ ሌብ መካሪ እንዯ አንድ ቃሌ ተናጋሪ መሆን ያስፈሌጋሌ፡፡ ቢቻሇን እንዯ ነነዌ ሰዎች ሕፃናትና ከብቶቻችን ሳይቀሩ በጾም ተጠምዯን፡፡ ምክንያቱም ታሊቁ መጽሐፍ እንዯሚሇው እንዱህ ዒይነቱ ‹ዘመድ› (ጋኔን)/ሌቡሳነ ሥጋ ወያኔ ያሇ ጾምና ጸልት አይርቅምና፡፡ ሌዐሌ እግዚአብሔር ጸልታችንን ሥሙር አድርጎ አገራችን ኢትዮጵያን ከጥፋት፣ ሕዝቧንም ከመሪር አገዛዝ ይታዯግሌን፡፡