November 5, 2017 18:53

 

በቅድሚያ ይህን ላደረገ ኃያሉ አምላክ እግዚአብሔር ሥሙ የተመሰገነ ይሁን! እንደምን ከረማችሁ አንባቢዎቼ፡፡ ስለ ሰሞኑ የአገራችን ሁኔታ ምን እየተሰማችሁ ነው? እኔን በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ እንደሌላው ብዙም ጥርጣሬ ውስጥ አልገባሁም፡፡  ምክነያቴ ደግሞ ጉዳዩን በትኩረት እከታተለው ነበርና ነው፡፡ ዛሬ ብቅ ያለኩት አሁንም ውዥንብር ሊፈጥሩ የሚሞክሩ ነጋዴዎች ስላየሁ ነው፡፡ለማንኛውም ወደ ጉዳዬ፡፡

የአሊ ቢራን ማልቱ አዳ ኑባሴ በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሁሉ ወክሎ ብዙ የተወደደ ዘፈን ነበር፡፡ የእርግማን ዘሮች መጡና በዘር ከፋፈሉን፡፡ ማልቱ አዳ ኑባሴ አለቦታው እንደገና ለሌላ ሴራ ዋለ፡፡ ከኢትዮጵያ ወርዶ ኦሮሞ ሆነ፡፡ ከዚያ ወዲህ የሚዘፈኑ የኦሮምኛ ዘፈኖች ሌላውን ሊወክሉ አልቻሉም፡፡ በቃ ኦሮሞ ብቻ ሆነ፡፡ የድሮዎቹ እነ ሰሎሞን ደነቀን እነ አብተውን ሌሎቹም ንጹህ የኦሮምኛ ዜማ ስለነበሩ ሕዝብ ዛሬም ድረስ ቋንቋ የማይገባው ሁሉ ያደምጣቸዋል፡፡ እንደውም እንደ አዲስ ቀርበውልን የአብተውን በተለይ አጣጥመውናል፡፡ የአሁኖቹን የኦሮምኛ ዘፋኞችን ምን ያህሉን ሌሎች እንደሚያደምጧቸው አላውቅም፡፡ በአንድ ወቅት ቀመር ጥሩ ነበር፡፡ ታደለ ገመቹ በብዙዎች ተወዳጅ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የሱ ግልጽ ነበር፡፡ ዘፈኖቹ የሕዝብ ናቸውና ሁሉም ወደዳቸው፡፡ ሌሎች ብዙ የሚባሉ ያው የእርግማ ልጆች በዘሩት መርዝ ተታለው (ተበክለው) ድሮ ያ በሬዱ ጂማ፣ ያ በሬዱ ድሬ፣ ሐረር፣ ነጆ፣ ሻንቡ …. በሚል ሁሉንም እንደየ ሥፍራው ሲያሳምሩዋቸው የሰማናቸውን ውበቶች ያ በሬዱ ኦሮሞ በሚል አጨቁን፡፡ አማርኛውም ጀምሮት ነበር፡፡ አሁን አሁን የአማራ ቆንጆ ማለት የተለመደ ነው፡፡ ትንሽ ቢቆይ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ምንጃር፣ ደራ፣ ወሎ ምናምን ይጠፋ ነበር፡፡ ብቻ ይሄም ሁሉ ሆነ አውነታው ግን በእነዚህ ሥሞች ማንነታችንን አጥተን ወርደን ወርደን አደጋ ላይ እንድንውድቅና ለሴረኞች እንድንመች ነው የሆንው፡፡ ልብ በሉ ዛሬ ላይ እጅግ ስለተለማመድንው የምናገረው ነገር ለአንዳነዶች ይከብዳቸዋል፡፡ የአሊቢራ ማልቱ አዳ ኑባሴ በደህና ቀን በመዘፈኑ ሌሎች ለራሳቸው ቢጠቀሙበትም ይሄው ዛሬ ተመልሶ የአማራ አገር ነው ብለው ሴረኞቹ በወሰኑት ምድር ዋና ከተማ ባህር ዳር ላይ ለታሪክ መዘክርነት ተዜመ፡፡ ማልቱ አዳ ኑባሴ ግጥሙን ለምትሰሙት እጅግ ልብ የሚነካ የወንድማማችነት ጥሪ ነው፡፡ ኦቦሉዋን ሰዲ (ሶስት ወንድማማቾች) ዱር ተካ ዱበና(ድሮ አንድ እናወራ ነበር) ወልጂባኒስ ሚቲ(መጠላላት አደለም(አይሁን)) ኮቱ(ታ) ወል ጎርፈና (ኑና እንወቃቀስ፣ እንታረቅ)፡፡ ረቢሞ ነሙማ (እግዚአብሔር ነው ወይስ ሰው) ከን ሴራ ጀሊሴ(ሕጉን ያጣመመው) ከራ ሲሪ ዲፍኔ(አዝናለሁ ይህነ ቃል በትክክል መጻፍ አልቻለኩመ አማርኛ ሶፍተዌር ደቨሎፐርስ እንዴት እስከዛሬ እንዳላስገቡት ፊደሉ ግን አለ) ከራ ሲሪ ዲፍኔ(ቀናውን መንገድ ትተን) ማሊፍ ዴምና ሙጋ(በጠማማው ለምን እንሄዳለን)………

http://oromp3.com/index.php?a=track&id=260&name=ali-birra-guitar-maaltu-addaan-nu-baase

ተመስገን እላለሁ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ለኢትዮጵያ መፍረስም መገንባትም ወሳኝ መሆኑን ለመገንዘብ ምሁርነት የሚጠይቅ ረቂቅ ነገር አልነበረም፡፡ በሴረኞች ስብከት ልባችን ታወረ እንጂ፡፡ ሴረኞቹ ብዙ ለፉ፡፡ አገሪቱን የሰሩትን አባቶቻችንን እንድንረሳ አረጉን፡፡ መርሳት ብቻም አደለም እንድን ረግም አደረጉን፡፡ ግን የቅን አባቶች አጥንትና ደም በረገምንበት ልክ ወግቶ እኛንው አደቀቀን፡፡ ጀግናው ጎበና ዳጬ የኦሮሞ ሥም መሰደቢያ ሆነ፡፡ የጎበና ዘር መባል ክብር መሆኑ ቀርቶ ሥድብ ሆነ፡፡ የሚኒሊክ ታሪክ የኦሮም ብልህ አባቶች በዋናነት እንደመሩትና ያመጣው ታሪካዊ ሥኬት ለኦሮሞ አዲስ ትውልድ ሲኦል ተደርጎ ተሳለለት፡፡

አንዲቱ አኖሌ አገር ለመገንባት በተሰለፉና  አልገብርም ባሉ መካከል የተደረገ ጦርነት እንደነበር ግልጽ ሆኖ ሳለ በሚኒሊክና በኦሮሞ መካከል የተደረገ ጦርነት በሚል ኦሮሞን ሁሉ የአባቶቹ ከሆነው የሚኒሊክ ታሪክ አስጣሉት፡፡ አርሲ አገር ለመገንባት ኣላማ በያዙት ሲሸነፍ አሸናፊዎቹ ጮቤ አልነበረም የረገጡት፡፡ ይልቁንም በመግባባት አብሮ መሆን ባለመቻሉ በሆነ ጦርነት ብዙ ሕዝብ በመጎዳቱ እጅግ ሀዘን ነበር እንጂ፡፡ ጦርነቱም ኦሮሞ የተባለ ሕዝብ ላይ የተደረገ ዘመቻ አልነበረም፡፡ አገርን ለመገንባት የተንቀሳቀሱት እኮ በአብዛኛው የኦሮሞ ልጆች ነበሩ፡፡ ጂማም፣ ወለጋም፣ሸዋም፣ ሁሉም ከአርሲ በቀር እኮ በጦርነት አልተጠቃለሉም፡፡ ያ ጦርነት የትኛውንም ሕዝብ ኢላማ ያደረግ ሳይሆን የተቃወመን ማንኛውም በወቅቱ የሚደረግበት ነበር፡፡ አላማውም አንድና አንድ አገርን አንድ ማረግ እንጂ አንድም ሌላ አላማ የለውም፡፡ ይልቁንም የአርሲ ሕዝብ በመጎዳቱ በአገር አንድ እናደርጋለን ባሉት ወንደሞቻችን ተጎዱ በሚል ሀዝን ነበር እንጂ፡፡ እውነታው ሕዝቡ በጦርነት ስለተጎዳ ወታደሩ አሸነፍኩት ብሎ ከመሬቱ እንዳያፈናቅለው ሌላም በደል እንዳያደርስበት የሚያስጠነቅቅ አዋጅ ታውጆ እንደነበር አንድም ዘመንኛ ታሪክ ነጋሪዎች ትንፍሽ አይሉም፡፡ ያልተደረግ ድርጊት ተደርጓል በሚል ለሴራቸው እንዲያመች ሊያዉም ጦርነቱ በተካሄደበት ቦታ ሳይወሰን በሰፊው በኦሮሞ ላይ ሁሉ የጥላቻ መንፈስ ለማሳደር ተጠቀሙት፡፡ የውጭ ጸሀፊያን አንዳነዶቹ እውነታውን ቢናገሩም ሌሎች በሚኒሊክ የታሪክ ስኬት ስለሚበሳጩ ያልተደረገን ድርጊት እንደጻፉም እናያለን፡፡ ጦርነቱም በመጻፈ ቅዱስ የተጠቀሰው የቢኒያም ነገድና የቀሪው የእስራኤል ነገዶች መካከል የተደረገውን አይነት ነበር የሚያስታውሰው፡፡ አስራ አንዱ የእስራኤል ነገድ ከወንድማቸው ከቢኒያም ጋር ተዋግተው ከቢኒያም ነገድ ብዙ ሕዝብ አለቀ፡፡ እስራኤሎች ጦርነቱን አሸንፋው እጅግ አዘኑ፡፡ ወደ እግዚአብሔርም አምላከ ሆይ ከእስራኤል ነገድ አንድ ጎደለ ቢኒያም ወንድማችን ጠፋ አሉ፡፡ ያም ሆኖ ከአርሲ ውጭ እንድም ቦት የኦሮሞ ሕዝብ በሚኖርበት ጦርነት አልተደረገም፡፡ ጨለንቆ ራሱን የቻለ ከሐረሪው ኢሚር ጋር የተደረገ ጦርነት ነው፡፡ እሱንም በመደባለቅ የኦሮሞ ሕዝብን ኢላማ ነው እየተባልነት ተሴረ፡፡ ሁሉም ጦርነቶች አንድን ሕዝብ ኢላማ አላደረጉም፡፡ ይሄ አልነበረም፡፡

ባሌ ሙከራ የተደረገባቸው ቦታዎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ግን ታሪኩ ጦርነት ሳይጀምር ነው የቆመው፡፡ ሂደቱ እንደውም መሳጭ ታሪክ አለው፡፡ የሚኒሊክ ወታደሮች ባሌ ሲደርሱ አንድ ወንዝ ጢም ብሎ ይጠብቃቸዋል፡፡ ባሌዎች ደግሞ ከማዶ ዋና ስለሚችሉ ተሻግረው ጦርነት ለመግጠም ይሰበሰባሉ፡፡ የሚኒሊክ ወታደሮች አንዳነዶች ቆመህ ጠብቀኝ ስለነበራቸው ከማዶ ሆነው በተኩስ አንድ ሁለት ሰው ይመታሉ፡፡ ባሌዎች እንደዛ ያለ መሳሪያ እንዳለ ምንም ፊንጭ አልነበራቸውም፡፡ ግን የሆነ ኃይለኛ ድምጽ ከተሰማ በኋላ የሆነ ሰው ሲወድቅ ያያሉ፡፡ ከዛ ደንግጠው ሲላ በከካ ዳን(ይህ ቃል አሁንም ልክ አደለም) ኑፊጣ ጅረኒ(እንዴ በመብረቅ እየፈጁን ነው?)  ብለው ሸሹ አሉ፡፡ እንደማለት  ይሄው ነበር ታሪኩ፡፡ ይሄን ታሪክ የምንሰማው በቀጥታ ከአባቶቻቸው ሰምተው እኛ ከደረስንባቸው የእድሜ ባለጠጎች ነው፡፡

ከአሁን በኋላ ማንም እየተነሳ ለጥላቻ በሚያመች መልኩ ታሪክ አይነግረንም፡፡ የአኖሌውን ሀውልት ዛሬ ሴረኞች በሚፈልጉት መልኩ ግንብተውልናል፡፡ በወቅቱ አገርን ለመገንባት በተነሱት አርሲ ላይ ስለሕዝቡ መጎዳት ሀውልት ቢያቆሙ አይከፋቸውም፡፡ ግን እንዲህ እንዳሁኑ ለሴረኞች በውሸት ታሪክ ላይ ጥላቻን ለዘለቄታው ለማኖር አደለም፡፡ ማንም በሉት ማንም ሁለት አመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ በጦርነት የተዋጉት ወንድማማቾች ወደ አንድ አላማ መጥተውና ተግባብተው ሌላ የማይረሳ ታሪክ አደዋ ላይ እንዳቆሙ አንክድም፡፡ አርሲም፣ ወላይታም፣ ሁሉም አደዋ ላይ ነበር፡፡

 

አሁምን ገና የጥላቻው ሰንኮፍ ከጭንቅላታቸው ያልወጣ በሴረኞች የተመረዙ ብዙ አሉ፡፡ ከበደኖ-እስከ ኢሊ አባቦራ ቡኖ ከባቢሌ እስከ ሞያሌ እኛን እያጫረሱ እነሱ ሊኖሩ ሴረኞቹ አረመኔያዊ ሥራቸውን ፈጸሙብን፡፡ ይህ ሁሉ ኦነግና ወያኔ እንደሰሩት አንረሳም፡፡ ልዩነታቸው ወያኔ በበላይነት ቀጠለ ኦነግ ለወያኔ ዋና መሳሪያ ሆነ፡፡ በደኖ ላይ ኦነግ እየገደለ ወያኔ ትቀርጽ ነበር፡፡ አንሸፋፍነው፡፡ ሰሞኑን ኢሊባቡር ላይ ኦነግ ባይኖርም ወያኔ ብዙ ሌላ ቦታ እንዳደረገቸው ኦነግን ሥሙን ስለተከራየች ተጠቀመች፡፡ እስከዛሬ እል የነበረው እውነት እንደነበር አሁን እየሆነ ያለው ነገር ምስክር ነው፡፡ ኦነግ መቼም ቢሆን ከወያኔ ያልተናነሰ ጠላታችን ነው!!! አንረሳውም፡፡ ኦነግ በደኖ ላይ አማራ በሚል ከጨረሰው ሕዝብ በላይ በኦሮሞ ሕዝብም ላይ አረመኔያዊ ድርጊተ ፈጽሟል፡፡ በቀጣይም እስከዛሬም ድረስ በኦነግ ሥም የስንቱ ኦሮሞ ልጅ የደረሰበት እንኳን ሳይታወቅ ጠፍቷል፡፡ የኦነግ መሪዎች ግን በቦሌ በአውሮፕላን መሸኘታቸውን፡፡ ከዛም አንዳንድ መሪዎቹ ጭራሽ የታሰሩ ጓደኞቻቸውን ለማስፈታት መለስ ዜናዊ ጋር በአካል መደራደራቸውን አንረሳም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ልጅ በኦነግ ሥም ያልቃል፡፡ የኦነግ መሪዎች ግን ወዳጆች ሆነው እስካሁንም ከወያኔ ጋር ይደራደራሉ፡፡ አሁን ሁሉም ሊነቃ ይገባል፡፡

ሌላው ድራማ የኦሮሞ አክቲቪስት ነን የሚሉት ነው፡፡ ይህ ቡድን በተለይ የጎንደሩ ወገንተኝነቱን ለወንድሙ ኦሮሞ ሕዝብ ያሳየበት ሰላማዊ ሰልፍ ከወያኔ ባልተናነሰ እጅግ አስደንግጦት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የተፈጠረውን አንድነት መልሶ ማፍረስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት መኖር የለበትም፣ ኢትዮጵያን ማፈራረስ ብቻ ነው መፍትሄው፣ የሚኒሊክ ሰፋሪዎች፣ ሌላላም አዲስ ዘመቻ የሚቻላቸውን ሁሉ አደረጉ፡፡

እግዚአብሔር ግን ይመለከት ነበር፡፡ ያላስተዋሉት እሱን ነው፡፡ በኦሮሞና አማራ መካከል ልዩ ጥላቻ ለመፍጠር ብዙ የሰራውን የወያኔ ተላላኪ ሻቢያ የሕዝብ ጠላት የሆነውን ተስፋዬ ገብረአብን የኦሮሞ ሕዝብ ልዩ ማዕረግ የሆነውን አባ ገዳነት በመስጠት አነገሱ፡፡ አባ ጋዳ የሚኒሊክ ወዳጆች በተባሉት ቦረናና ጉጂ፣ የሸዋው ኦሮሞ እንደቆየ አስተውሉ፡፡ አባ ገዳን ለሌላ የሚሸጡት ከነጭረሱም የማይመለከታቸው  ናቸው፡፡ ነጋዴ መሆናቸው ሳያንስ በሕዝብ እልቂት መነገዳቸው ያሳዝናል፡፡

ሌላ ደግሞ ቡድን አለ ከላይ የጠቀስኳቸው ሸኔ ብለው ይተሯቸዋል፡፡ እነዚህ ደግሞ ለየት ያሉ ናቸው፡፡ ብዙም ባይገቡኝ ግን የኦነግ ወና ነን ባዮች ይመስላሉ፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ በሚከተሉት ድምር ውስጥ ታገኟቸዋላችሁ፡፡

ለመሆኑ ግን ማነው ጤነኛ? የሚከተሉትን ሁሉ ታዘብኩ፡፡ እንዳትደነግጡ አንዳንዶቹ ከቶውንም የማታስቧቸው ናቸውና

ኢሳት፡- እውን የሕዝብን ጉዳይ የሚዘግብ ነው ወይስ የነጋዴዎች ወይስ ከነችርሱ የጠላቶቻችንን ሴራ የሚዘራ? ለወያኔው ጻድቃን ሴራዊ ጽሁፍ ትልቅ ስፍራ የሰጠው ኢሳት፣ በቀደመው የወያኔ አገልጋይ በየቀኑ በፖለቲካ ትንተና ሥም የሚነዛቸው መረጃዎች፣ ምሁር በአገሩ የሌለ ይመስል በተደጋጋሚ የኢሳት መደበኛ ቃለ ምልልስ አድራጊዎች የተቆጣጠሩት፣ ዓላማው ወይ ንግድ ወይ የወያኔ መሳሪያ የሆነውን ግንቦት 7ን የሚደሰኩርልን ኢሳት፡፡ ምን አለፋችሁ ኢሳት በሌሎች እጅ እንዳለ አስተውሉ፡፡

ኦኤም ኤን፡- ኦሮሞ ስልሆንክ ብቻ የኦኤም ኤን ደጋፊ አትሁን፡፡ በእርግጥ ሚዲያው የሕዝብ ነው ከላይ የጠቆምኩትን በተለይ ከጎንደሩ የአንድነት ሰልፍ በኋላ እንድነቱን ለማፍረስ ሴረኞች አዘውትረው የሚጠቀሙበት ነው፡፡ ለኢሳት የተነሱት እዚህም ይሰራሉ፡፡

ሌሎች ለዘመናት ኦሮሞ ነን በሚል የሚቆምሩትን እነ ሰይፈ ነበልባልን ጨምሮ ኦኤንኤን ሌሎች ጥቃቅንን ታዘቡ፡፡

እንደነ አይጋ ፎረም መሆን ብቻ አደለም ዛሬ ጠላት እየተጠቀመ ያለው በእኛው ገንዘብ የሚደገፉትን ሚዲያዎች ነው፡፡

በድርጅት ደረጃ ወለ ግ7፣ ንቅናቅ ምናምን ሁሉም ንግድ ይመስላል፡፡ ንግዱ ደግሞ በኢትዮጵያውያን እልቂት ነው፡፡

ከዚህ በተቃራኒ ሊመሰገኑ የሚገቡ የመንግስተ የሆኑት የቪኦኤ፣ ዶቼቪሌ፣ ኤስቢኤስ መጠቀስ አባቸው፡፡ ከግሎች የሙስሊም ወንድሞችችን የሆነው ቢቢኤንና ሌላ ሕብር ሬዲዮ መመስገን አለባቸው፡፡

በተረፈ ሁሉም ይንቃ፡፡ ታማኝ በየነ ታማኝ እንደሆነ አምናለሁ ግን ታማኝ ታማኝ ነው ማለት ኢሳት ታማኝ ነው አልሆነም፡፡ ሌላውም እነደዚያው ነው፡፡ ውስጥ በመሰግሰግ ነው ሥራ እየሰሩ ያሉት ጠላቶቻችን፡፡

አሁን አገር ቤት እየተካሄደ ያለው ጉዳይ ስጋት የሆነባቸው አልፎም የጨነቃቸው ብዙ ናቸው፡፡ ንግድ ሊቀር ነዋ!
ምክር አገር ቤት የህዝብን ጥያቄ እየመለሱ ላሉ የኦፒዲዮና በአዴን መሪዎች

1.በተለይ ኦፒዲዮ በግልጽ እነ በቀለ ገርባ የሕዝብን ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ እንደታሰሩ ይፋዊ መግለጫ መስጠት አለበት፡፡ የወንበዴዎች ፍርድ ቤት በሕዝብ ታማኝ ልጆች ላይ እየፈጸመ ያለውን ቁማር ማስቆም አለባቸውዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የተባሉት ሰው አልተመቹኝም፡፡ በሚኒስቴር ደረጃ የሰጡትን መግለጫ በሌላ ተራ የክፍል አላፊ ሲጣጣል ዝም ከማለት አልፈው ሰሞኑን በቢቢሲ የሽብር አዋጁን እስመልክቶ ለቀረበላቸው መጠይቅ ሕጎ ለሁሉም ይሰራል ስለዚህ ሰዎችን እያሰርን ያለንው በሕጉ መሠረት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ኦፒዲኦ ግለሰቡን (በእርግጥ በሚኒቴር ደረጃ የሚሰጡትም መግለጫ የግል አስተያየት ተብሏል) ሊመክር ወይም ሊያሰወግድ ይገባል፡፡

2.ሕዝብ የሚጠይቀውን ሁሉ መመለስ፡፡ ሕገ መንግስት ተብዬው የኦነግና የወያኔ ሴራዊ ድርሰት እንደሆነ ታውቆ ሕገ ምነግስት የሚለው ታፔላ ከሰላማዊ ሕዝብና የሕዝብን ጥያቄ ከሚያስተጋቡ እንዲነሳ፡፡ ሕገ መንግስት የሚባለው የኢትዮጵያን ሕዝቦች አይመለከትም፡፡ እኛን የመለስ የጥንቆላ ሰነድ እኛን አይመለከተንም፡፡

3.ፌደራል ከሚባለው መዋቅር ፈርሶ ሙሉ በሙሉ መተካት አለበት፡፡

4.በክልሉ ያሉ የደኅንነትና የፖሊስ ሰራዊቱን ኃይል ማጠናከር

5. በድፍረት ሕዝብንና የሕዝብ አጋሮችን በዘለፍ ተግባር የተሰማሩ የወያኔ ሚዲያዎችን ለሕግ ማቅረብ፡፡ የነገሪ ሌንጮ ሥራ ይሄ ነው፡፡ በሽብር ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል

በመጨረሻም ሰርጸ ደስታ ከዚህ በፊት ከጻፋቸው ሁለቱን ለናሙና እንሆ

https://ethiobook.net/%E1%8B%A8%E1%8A%A6%E1%88%AE%E1%88%9E-%E1%88%95%E1%8B%9D%E1%89%A5-%E1%8C%89%E1%8B%B3%E1%8B%AE%E1%89%BD-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8C%B8-%E1%8B%B0%E1%88%B5%E1%89%B3/

http://ayyaantuu.net/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%88%88%E1%88%9B%E1%8D%8D%E1%88%A8%E1%88%B5%E1%88%9D-%E1%88%86%E1%8A%90-%E1%88%88%E1%88%98%E1%8C%88%E1%8A%95%E1%89%A3%E1%89%B5-%E1%8B%A8/

ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ! ይባርክ!

ሰርፀ ደስታ