የሰባክያንን ስብከት እንዴት እንደጠላሁ አትጠይቁኝ! የምሬን ነው የምላቹህ! እስኪ እባካቹህ መላ በሉኝ? እንደምታውቁት ከአረማውያን ጋራ ነው አብረን ተቀላቅለን የምንኖረው፡፡ እኛን ክፉ በሚያስቡብን ላይ አንዳች ክፉ ነገር እንዳናደርግ ጭራሽም ክፉ ላደረገብን እንኳ ክፉ ብድራት እንዳንመልስ የሃይማኖታችን ሕግ፣ ያለን የሞራል (የቅስም) ሕግና የሠለጠነው ባሕላችን አጅ እግራችንን አስረውናል፡፡ አብረውን የሚኖሩት አረማውያኑ ደግሞ በእነኝህ ገመዶች ያልታሰሩና ያሻቸውን የማድረግ ነጻነት ያላቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም እኛ ዘወትር ታራጅ ሰዎቻችንን ለመሥዋዕት እንዳቀረብን አለን እነሱም የሰውን ልጅ እንደ እንስሳ አጋድመው ለማረድ እንደጎመጁና እንዳረዱን አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት እኛ ለበርካታ ኪሳራዎችና ሽንፈቶች ስንዳረግ እነሱ ደግሞ ለበርካታ ትርፎችና ድሎች በቅተዋል፡፡

ወይ ክርስቲያኖች ነን ብለን ክርስትናው የሚያዘውን መንፈሳዊ ሕይዎት በትክክል ኖረነው ጠላቶቻችንን፣ አራጆቻችንን እግዚአብሔር እንዲዋጋልንና እንዲያጠፋልን ማድረግ አልቻልን ወይ ደግሞ ሥጋዊ ዓለማዊ ሆነን አራጆቻችንን እንዳመጣጣቸው በማስተናገድ ሰላማችንን አላስጠበቅን፣ ደኅንነታችንን አላረጋገጥን ከቶ ምን ይሻለናል ትላላቹህ??? እርግጠኞች ናቹህ በዚህ መልኩ መቀጠል ያዋጣናል ትላላቹህ??? እየጠፋን እየጠፋን እየከሰምን መምጣታችን አይታያቹህም??? ወይ አራጆቻችን እንደኛ ሆነው በሦስቱ ገመድ አልታሠሩ ነገር እንዴት ልንቋቋማቸውና ህልውናችንን ልናስቀጥል እንችላለን???

ክርስቲያናዊውን ሕይዎት ወይ እንኑረው ወይ እንተወው!!! ሰባክያኖቻችን እንደጥንቶቹ የገባቸውና የበቁ አይደሉምና ኃጢአት ነው ሳይባል ክርስትና ለዚህም መንገድ እንዳለው አውቀው ሊያሳዩን አልቻሉም እንጅ አራጆችን እንዳመጣጣቸው ማስተናገድና ማጥፋት የሚቻልበት መንገድም ነበረው፡፡ እነሱ ግን ይሄንን ተረድተው መንገድ በመጠቆም ችግራችንን የሚቀርፉ አልሆኑም፡፡

እንግዲህ ክርስትናውን የማንኖረውም የማንተወውም ከሆነ አረማውያን አራጆቻችንን እስክናጠፋ ድረስ ይሄንን ክርስትናችንን ቆልፈንበት ብናቆየው ምን ይመስላቹሀል??? አረማዊ አራጆቻችን ለማጥፋት አረማዊነቱ የግድ ያስፈልገናልና!!!

ድል ለመሥዋዕቱ በግ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com